2012-05-08 09:54:06

የር.ሊ.ጳ የንግሥተ ሰማያት ጉባኤ አስተምህሮ (06.05.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ በዛሬ ዕለት የዘመነ ትንሣኤ አምስተኛ እሁድ የሚቀርብልን ወንጌል ኢየሱስ እውነተኛ የወይን ግንድ መሆኑን በሚገልጽ ምሳሌ ይጀምራል፣ “ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ! እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ= አትክልተኛውም አባቴ ነው፣” (ዮሐ 15:1) ብዙ ጊዜ በቅዱስ መጽሓፍ እስራኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆና በምትገኝበት ጊዜ እንደ ለም የወይን አትክልት ትመሰል ነበር፣ ከእርሱ የራቀች እንደሆን ደግሞ መካን ሆና መዝሙረ ዳዊት 104:15 የሚዘምረውን “የሰው ልብ የሚያደስተውን ወይን” ለማፍራት አትችልም ነበር፣ እውነተኛው የእግዚአብሔር የወይን አትክልት፣ በፍቅር መሥዋዕቱ ያዳነንና የወይን ተክሉ አካል እንድንሆን መንገዱን የከፈተልን ኢየሱስ እውነተኛው የወይን ግንድ ነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ፍቅር አንድ እንደሆነ ሐዋርያቱም በመምህሩ ቃል በጥበብ ተገርዘው ከእርሱ ጋር ጥልቅ በሆነ መንገድ አንድ የሆኑ እንደሆነ ብዙ ፍሬ የሚያፈሩ ለም ቅንርጫፎች ይሆናሉ፣ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘሳለስ እንዲህ ጽፈዋል፣ “ከግንድ ጋር የጠበቀና አንድ የሆነ ቅርንጫፍ ፍሬ የሚያፈራው በገዛ ራሱ ሳይሆን ከግንዱ በሚያገኘው ሕይወት ነው፣ እኛ አሁን አካል ከራስ ጋር እንደሚተባበረው በፍቅሩ ከመድኃኒታችን ጋር አንድ ሆነናል፣ … የምናደርጋቸው መልካም ሥራዎች ኃይል ከእርሱ እያገኙ ዘለአለማዊ ሕይወት ያስገኙናል” (ትራታቶ ደል አሞረ ዲ ድዮ - የእግዚአብሔር ፍቅር ሐተታ መዝ.9 ቍ. 6 ሮማ ላይ በ2011 የታተመ ገጽ 601)፣
ምሥጢረ ጥምቀት በምንቀበልበት ቀን ቤተ ክርስትያን እንዲዳቀል ከጉቶ ጋር እንደሚጠብቅ ቅርንጫፍ ኢየሱስ ራሱ በሆነው በምሥጢረ ፋሲካው ታጥብቀናለች፣ ከዚህ ጋር በመለኮታዊ ሕይወት የሚያሳትፍ ክቡር ሥር እናገኛለን፣ የኢየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን እኛም በቤተ ክርስትያን እረኞች እርዳታ በፍቅሩ ታሥረን በጌታ የወይን ግንድ እናድጋለን፣ “የምናፈራው ፍሬ ፍቅር ከሆነ ይህንን ለማድረግ ቅድመ ሁኔታው ከእርሱ ጋር አንድ ሆነን መኖር ነው፣ ይህም ጌታን በማይተው እምነት የጠበቀ ሥራ አለው” (የናዝሬቱ ኢየሱስ በጠልያንኛ ሚላን በ2007 የታተመ ገጽ 305) በእርሱ መኖር የግድ ነው ምክንያቱም ካለ እርሱ ምንም ማድረግ አንችልም (ዮሐ 15፡5)፣ በ5ኛው ክፍለዘመን በምድረበዳ ይኖር የነበረው ነቢይ ለወጣቶች በጻፈው መልእክት፣ አንድ ም እመን የሚከተለውን ይጠይቀዋል፣ “የሰው ልጅ ነጻነት እና ካለ እግዚአብሔር ምንም ማድረግ አለመቻልን እንዴት ልናያይዘው እንችላለን፧ መነኮሱም እንዲህ ሲል ይመልሳል፣ የሰው ልጅ ልቡን ወደ በጎ ነገር ካዘነበለና የእግዚአብሔር እርዳታን ከጠየቀ፣ ሥራውን ለመፈጸም የሚያስፈልገውን ኃይል ያገኛል፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ነጻነትና የእግዚአብሔር ችሎታ አብረው ይጓዛሉ፣ ይህ የሚቻልበት ምክንያትም በጎ ነገር ከእግዚአብሔር ስለሚመጣ ነው ሆኖም ግን እተግባር ላይ የሚውለው በም እመናን ነው፣ ይላል፣ ሲታው መነኮስ ብጹዕ ጐሪኦ ዲⷝ እንደሚለው “ጌታ ኢየሱስ ሆይ … ካላንተ ምንም ማድረግ አንችልም፣ አንተ እውነተኛው አትክልተኛ ፈጣሪ የአትክልትህ ዋናና ጠባቂ አንተ ነህ፣ በቃልህ ትተክላለህ በመንፈስህ ትመግባለህ በችሎታህ ደግሞ ታሳድጋለህ” ስለሆነ እውነተኛ ከጌታ ኢየሱስ ጋር መኖር ለጸሎት ችሎታ ዋስትና ይሰጣል፣
ውዶቼ እያንዳንዳችን በየዕለቱ ጸሎት በማሳረግ ምሥጢራት በመሳተፍ እና ምግባረ ሠናይ በማዘውተር ከጌታ ጋር አንድ በመሆን ያደገ እንደሆነ ብቻ ለመኖር እንደ ሚችል ቅርጫፍ ነን፣ እውነተኛ የወይን ግንድ የሆነው ኢየሱስን የሚያፈቅር መንፈሳዊ ፍሬ የሆነ አመርቂ የእምነት ፍሬ ያፈራል፣ ከኢየሱስ ጋር በጠበቀ ትሥሥር አንድ ኣንድ ሆነን ለመኖር እና እያንዳንዱ ተግባረችን በእርሱ ጀምሮ በእርሱ እንዲፈጸም ጸጋ እንድታስገኝልን እንማጠናት፣








All the contents on this site are copyrighted ©.