2012-05-04 17:21:59

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (02.05.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ በመጨረሻው ትምህርተ ክርስቶስ እንደተመለክትነው የቅዱስ መጽሐፍ ንባብና አስተንትኖ በግል በምናሳርገው ጸሎት ይሁን በኅብረት በምናሳርገው ጸሎት ለሚናገረንና ያለነውን ሁኔታ ለመረዳት ብርሃን የሚለግስልን የእግዚአብሔር ቃል ለመስማት ልባችንን እንዴት እንደሚከፍቱ አይተናል፣ ዛሬ ስለመጀመርያው የቤተ ክርስትያን ሰማዕት ምስኪኖችን ለመርዳት ከተመረጡ ሰባቱ ዲያቆናት አንዱ ስለሆነ ስለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ምስክርነትና ጸሎት ለመናገር እወዳለሁ፣ ግብረ ሐዋርያት እንደሚተርከው በሰማዕትነቱ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃልና የጸሎት ፍርያም ግኑኝነት እንደገና ይገለጣል፣
ቅዱስ እስጢፋኖስ ተከሶ ወደ ሸንጎ ይወስዱታል በሊቀ ካህናት ፊት አቁመውም ይህንን ክስ አቀረቡለት፣ “ይህ ሰው የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ።” (ግሐ 6፡14) ኢየሱስ በዚህ ዓለም ሳለ ስለ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መፍረስ ተናግሮ ነበር፣ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ” (ዮሐ 2፡19) ብሎ ነበር፣ ይሁን እንጂ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንደሚያመለክተው “እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።”(ዮሐ 2፡21-22)
በግብረ ሐዋርያት ከተመለከቱ ንግግሮች ረዥም የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በችሎት ያደረገው ንግግር በዚሁ ኢየሱስ ራሱ አዲስ ቤተ መቅደስ በመሆን የኦሪት መሥዋዕቶችን ራሱ በመስቀል መሥዋዕት በማድረግ በመተካት አዲስ አምልኮ የተጀመረበት የኢየሱስ ትንቢት ይመረኰዛል፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የቀረበለት ክስ መሠረት እንደሌለው ለማስረዳት በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ስለሚያስረዳው ሕገ ሙሴን ለመቀልበስ ሳይሆን ስለደህንነት ታሪክ ያየውን ለማስረዳትና ትክክለኛነቱን ለመከላከል ይሞክራል፣ በዚህም በቅዱስ መጽሐፍ የተነተነውን ታሪክ እንደገና በማቅረብ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወሳኝ ቦታ ወደሆነው ቤተ መቅደስ እንድሚመራና እርሱ ራሱ በሕማማቱ በሞቱና በትንሣኤው ያኛው ቤተ መቅደሱ መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራል፣ በዚህ አጋጣሚ ቅዱስ እስጢፋኖስ እርሱ ራሱም የኢየሱስ ሐዋርያ መሆኑና እስከ ሰማዕትነት እንደሚከተለው ያመለክታል፣ በቅዱስ መጽሓፍ ማስተንተን ተል እኮው ሕይወቱና ያለው ሁኔታን ለመረዳት ይረዳዋል. በዚህ ሁኔታ ቅዱስ እስጢፋኖስ ራሱ ከጌታ ካለው ጥብቅ ግኑኝነት ባገኘው ብርሃነ መንፈስ ቅዱስ ይመራል፣ የሊቀ ካህናቱ ሸንጎ አባላት ይህንን ለማየት በቁ “በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት” (6፡15)፣ ይህ የመለኮታዊ እርዳታ ምልክት በደብረ ሲና ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኝቶ የወረደ ሙሴ ት እይንትን ያሳስባል (ዘጸ 34፡29-35 እንዲሁም 2ቆሮ 3፡7-8 ተመልከት)፣
ቅዱስ እስጢፋኖስ ባደረገው ንግግር ከአብርሃም ይነሳል፣ አብርሃም እግዚአብሔር ያመለከተውን መሬት ለማግኘት የተነሣ እና ይህንን ቦታ በተስፋ ብቻ የወረሰው ሲሆን ከእርሱ በኋላ ይህ ምድረ ተስፋ በወንድሞቹ ለተሸጠ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር ለተረዳና ለዳነ ዮሴፍ ይተላለፋል፣ በመጨረሻም ሕዝቡን ነጻ ለማውጣት የእግዚአብሔር መሣርያ ለሆነው ለሙሴ ይተላለፋል፣ ሆኖም ግን ሙሴ በሕዝቡ ተቋውሞ ያገጥመዋል፡ ይህም ለብዙ ጊዜ ነበር ያጋጠመው፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ እነኚህን የቅዱስ መጽሐፍ ታሪኮች ሲተርክና ሲሰሙት የሰው ልጆች ሲቋወሙትና ሲያሳድዱት የማይደክመው እግዚአብሔር ይገለጣል፣ ይህም ባለፉት ዘመናት ሆነዋል ዛሬም እየተደረገ ነው ለወደፊትም ይደረጋል፣ ስለዚህ ቅዱስ እስጢፋኖስ የሚያሳየው በጠቅላላው ብሉይ ኪዳን ሥጋ በለበሰው በኢየሱስ አምሳል በአበው የተገለጠው ሆኖ ግን ተቃውሞ ክህደትና ሞት ያጋጠመዉን ጌታ ይገልጣል፣ በዚህም ቅዱስ እስጢፋኖስ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሱት እያሱ ዳዊትና ሰሎሞንን የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስን ለመስራት በተሰማሩ አበው ካቶኰረ በኋል በትንቢተ ኢሳያስ 66፡1-2 የተባለው “ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።” (ግሐ 7፡49-50) ይላቸዋል፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ እግዚአብሔር በደህንነት ታሪክ ስላደረገው ሥራ ባቀረበው አስተንትኖ ዘለአለማዊ የሰው ልጆች የክህደት ፈተናንና የእግዚአብሔር ሥራን በመግለጥ ኢየሱስ በነቢያት የተነገረለት ጻድቁ መሆኑንና ጌታ በእርሱ ለአንዴና ልዩ በሆነ መንገድ በመሃከላችን ህያው እንደሆነ አብራርቶ እውነተኛው የአምልኮ ቦታ ኢየሱስ መሆኑን ገልⶏአል፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ግዝያዊ የቤተ መቅድስ አስፈላጊነትን አይቃወምም ሆኖም ግን “ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም” በማለት ያሠምርበታል፣ እግዚአብሔር የሚኖርበት አዲስ ቤተ መቅደስ የሰው ልጅ ባህርይ የለበሰ ከሙታን ተለይቶ በመነሣት ሁሉን ሕዝብ በሥውና በደሙ ምሥጢር የሰበሰበና አንድ ያደረገ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ ይህ በሰው እጅ ያለተሠራ በማለት የሚገለጠው ቤተ መቅደስ በዕብራውያን መል እክትም ተጠቅሶ እናገኘዋለን፣ ይህም ኃጢአትን ለማስተሰረይ እንደ መሥዋዕት ለማቅረብ የለበሰው የኢየሱስ ሰውነት ነው. የኢየሱስ ሰውነት አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፣ ሕያው እግዚአብሔር በእውነት የሚገኝበት ቦታ እውነተኛ ሰውና እውነተኛ አምላክ በሆነው በእርሱ እግዚአብሔርና ዓለም ተንገናኝተዋል፣ ኢየሱስ የሁሉን ኃጢአት በአጠቃላይ በራሱ በመሸከም በፍቅሩ ያቃጥለዋል፣ ወደ መስቀሉ መጠጋት፣ ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ማለት በዚህ ፍቅር መለወጥ ማለት ነው፣ ይህ ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ወደ እውነተኛ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው፣
የቅዱስ እስጢፋኖስ ሕይወትና ንግግር በድንጋይ ድብደባ ይቋረጣሉ፣ ሆኖም ግን ሰማዕትነቱ ራሱ የሕይወቱና የመልክእክቱ ፍጻሜ ናቸው፣ እርሱ ከኢየሱስ ጋር አንድ ይሆናል፣ በዚህም እግዚአብሔር በታሪክ የሠራውን በማሰላሰል ያደረገው አስተንትኖ እንዲሁም በኢየሱስ ሙሉ ፍጻሜ ባገኘው መለኮታዊ ቃል በማስተንተን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ካሳረገው ጸሎት ጋር ይሳተፋል፣ ከመሞቱ በፊት የመዝሙረ ዳዊት 31 ቃላት የእርሱ በማድረግ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ነፍሴን ተቀበል” (ግሐ 7፡59) በማለት ይጮሃል፣ እንዲሁም ኢየሱስ በቀራንዮ ያደረገው የመጨረሻ መግለጫ በማስታወስ “አባቴ ሆይ! ነፍሴን በእጆችህ አማጥናለሁ” (ሉቃ 23፡46) ይላል፣ በመጨረሻ ልክ እንደ ኢየሱስ በድንጋይ በሚወግሩት ፊት በታላቅ ድምጽ “ጌታ ሆይ! ይህንን ኃጢአት አትቍጠርባቸው” (ግሐ 7፡60)ይላል፣ በዚህ ሁኔታ ቅዱስ እስጢፋኖስ የኢየሱስን ጸሎት ሲደግም ብናይም የሚጠየቀው ሌላ ነው፣ ምክንያቱም ጸሎቱ የሚቀርበው በእግዚአብሔር አብ ቀኝ እጅ በክብር ቦታ ላለው ኢየሱስ ነው፣ “እነሆ ሰማይ ተከፍቶ፣ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ (ኍ 55)፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ የቅዱስ እስጢፋኖስ ምስክርነት ለጸሎታችንና ለሕይወታችን አንዳንድ መመርያዎች ይሰጠናል፣ የክርስትያን የመጀመርያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ የሚያሳድዱትን ለመጋፈጥና ራሱን መሥዋዕት እስከማድረግ ያስቻለውን ኃይል ከየት አገኘው፧ ብለን ለመጠየቅ እንችላለን፣ መልሱ ቀላል ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ከነበረው ግኑኝነት ነው፣ ይህ ማለት ከክርስቶስ ጋር ክነበረው አንድነት፣ ያደርገው ከነበረው የደህንነት ታሪክ አስተንትኖ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጻሜ ላይ የደረሰውን የእግዚአብሔር ሥራ ከማየት ይህንን ኃይል አገኘ፣ ጸሎታችንም ከኢየሱስን ከቤተ ክርስትያኑ ጋር አንድ በመሆን በእግዚአብሔር ቃል መስማት መመገብ አለበት፣
ሌላው የቅዱስ እስጢፋኖስ ምስክርነት የሚያመለክተልን ነገር ደግሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ስላለው የፍቅር ግኑኝነት የኢየሱስ መልክና ተል እኮ አስቀድሞ በዓይነ ኅሊናው ያያል፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ “በሰው እጅ ያልተሠራው” ቤተ መቅደስ ሆኖ በእርሱ የእግዚአብሔር ህልውና እጅግ ቅርብ ይሆናል፣ ሰብአዊነታችንን ወደ እግዚአብሔር እንዲያደርሰውና የሰማይ በሮችን እንዲከፍትልን በሰብአዊ ሥጋችን በመግባት ቀረበን፣ ስለዚህ ጸሎታችን ኢየሱስን እንደ ዕለታዊ ህልውናየ ጌታ በመረዳት በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ መኖሩን ማስተንተን መሆን አለበት፣ በመንፈስ ቅድሱ መሪነት በእርሱ ወደ እግዚአብሔር መማጠን እንችላለን፣ ከእግዚአብሔር ጋር እውነተኛ ግኑኝነት ማድረግ እንችላለን፣ በመተማመን ባባታቸው እንደሚማጠኑ ልጆች በዘለዓለማዊ ፍቅሩ ወደ ሚያፈቅረን እንማጠን፣ እግዚአብሔር ይስጥልን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.