2012-05-02 14:50:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ “ለልኡካነ ወንጌል እንጸልይ”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “ቅድስት ድንግል ማርያም የዓለም ንግሥትና የአስፍሆተ ወንጌል ኮከብ ሁሉንም ልጅዋን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚያበስሩ ልኡካነ ወንጌል ትሸኝ ዘንድ” በሚል መንፈሳዊነት መርህ ሥር እ.ኤ.አ. ትላንትና የተገባው የማርያም ወር ተብሎ በሚጠራው ግንቦት ወር RealAudioMP3 በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ስለ ልኡካነ ወንጌል እንዲጸለይ ሐዋርያዊ ውሳኔ ሰጥተዋል።
ግንቦት ወር የማርያም ወር የተባለበት ምክንያት፣ የማርያም አገልጋዮች ማኅበር አባል ጳጳሳዊ የሥነ ማርያም ተቋም ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ሳልቫቶረ ፐረላ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በምሥራቅም ይሁን በምዕራቡ ዓለም ማኅበረ ክርስትያን አንድ ቀን በሳምንትም ይሁን አንድ ወር ለቅድስት ድንግል ማርያም በማዋል፣ ለእርሷ አማላጅነት እና ጥበቃ መጸለይ የተለመደና የቆየ ቅዱስ ልምድ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ግንቦት ወር የአበባ የጸሐይ ወር እርሱም የዳግም መወለድ ሂደት የሚይታይበት በመሆኑ ማኅበረ-ክርስትያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ያለው አክብሮት በመገንዘብ የማርያም ወር የሚለው ክርስትያናዊ ቅዱስ ልምድ ዳግም ያረጋግጠዋል። ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ “ማርያም፦ ማክበርና መወደስ ቤተ ክርስትያናዊ እና ክርስትያናዊ ግዴታ ነው” በማለት ይገልጡታል።
ለክርስትያን ሰብአዊና ቅዱስ አብነት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነች። ማርያም መጸለይ እንደ ማርያም መጸለይ ከማርያም ጋር አብሮ መጸለይ የሚለው ጥልቅ ማርያማዊ መንፈሳዊነት በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤና እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 1974 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. “Marialis cultus-ማርያማዊ አምልኮ” በተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ የተብራራ መሆኑ አባ ፐረላ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ ድንግል ማርያም የመጀመሪያ ሐዋርያ፣ ቃል አክባሪና ጸላይ በመሆንዋም የክርስትና እናት በማለት ገልጠዋታል። የጌታ እናት የቤተ ክርስትያን እናት በእናትነት ባህርያዋ አማካኝነትም ሁሉንም ልጆችዋን የምታማልድ ነች። ቅዱስነታቸው ባላቸው ጴጥሮሳዊ ሥልጣን አማካኝነት “Porta Fidei - የእምነት በር” በተሰኘው የውሳኔ ሰነድ አማካኝነት ስለ እውነተኞች የእምነት መስካርያን እንዲጸለይና ማርያም የእምነት ምስክር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ተገቢነቱ እርሱም የሰላም የመከባበር በተለይ የማንነት መለያ መሆኑ በፍቅር የመሰከረች መሆንዋ በማብራራት የእምነት አብነት በማለት ሰይመዋታል። የልጅዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በመሆናችን የእርሷ ልጆች ነን ካሉ በኋላ እውነተኛው አምልኮና አክብሮት ከእውነተኛው እምነት የሚመንጭ ለእግዚአብሔር ልባዊና ቀልባዊ ጥምረት ያለው ሙሉ ተከትሎ የሚገለጥበት ቅዱስ ተግባር መሆኑ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ይገልጠዋል። ስለዚህ ይኽ ደግሞ እምነት እና አእምሮን የሚያጠቃልል ትክክለኛና የተገባ ፈጣሪንና ፍጥረቱን በሚገባ በመለየት የሚቀርብ አምልኮ እዲኖር የሚል መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት ማብራሪያ በማስታወስ ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.