2012-05-01 17:43:34

መስቀል እጅግ ሲከብድ ምርጥ ሰዓት ደረሰ ማለት ነው፣ ወጣቶች የእግዚአብሔር ድምጽ ለመስማት ጠንቃቃዎች ሁኑ፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለዘጠኝ የሮማ ሰበካ ዲያቆናት ክህነት በሰጡበት ወቅት ነው፣ በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ግጻዌ መሠረት የትናንትና እኁድ የዘመነ ፋሲካ አራተኛ እኁድ ሆኖ በሰንበት ዘኖላዊ ወይንም የመልካሙ እረኛ እኁድ በሚል ስም ይታወቃል፣ የጌታን መልካም እረኝነት በመመርኮዝ ደግሞ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጌታን የሚመስሉ መልካም እረኞች እንዲሰጧት ስለ ክህነት ጥሪ ለመጸለይ ዓለም አቀፍ የጥሪ ቅን ብላ ስለወሰነቻት ሁሉ ካቶሊካዊ ለጥሪ ጸሎት አሳርገዋል፣ በትናንትናው እኁድ ቅዱስነታቸው ለዘጠኝ የሮማ ሃገርስብከት ዲያቆናት መዓርገ ክህነት ለመስጠት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲልካ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉት ስብከት “የመስቀሉ ክብደት እጅግ ከፍ ባለ መጠን ያች ሰዓት ክብር የሞላባት ምርጥ ወቅር ትሆናለች” ሲሉ መዓርገ ክህነት የመስቀል መንገድ መሆኑን አሳስበው፣ በእኩሉ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከንጋድያንና ከም እመናን ጋር የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ደግሞ ዘወትር እንደሚያደርጉት የዕለቱን ቃለ ወንጌል ተመርኵዘው በሰጡት ትምህርትም “ወጣቶች ሁላቸው የእግዚአብሔር ዽምጽ በጥንቃቄ አዳምጠው እንዲችሉ ይሁን” ሲሉ አደራ ብለዋል፣
ስለመልካሙ እረኛ ባቀረቡት ስብከትም፣ “መልካሙ እረኛ ለበጉቹ ሕይወቱን ይሰጣል፣ ኢየሱስ በዚሁ እርሱ ራሱ በሆነው የእውነተኛ መሠረታዊ ባህርይ ይገልጣል፣ እንደ ላኪው እግዚአብሔር አብ ፈቃድ፣ እረኛነትን እንደ ኢየሱስ በአካል እተግባር ላይ ለመዋል የሚጥር እረኛን ብቁ የሚያደርገውም ይህ ነው፣ ካህን ማለት በምሥጢራዊ መንገድ በኢየሱስ መሥዋዕት የሚጨመር ከእርሱ ጋር አንድ በመሆን ደግሞ የደህንነት ተል እኮን የሚቀጥል ነው፣ ይህ አንድነት በምሥጢረ ክህነት ይሰጣል፣ ሁሌ በካህኑ ለጋስ ውይይትም ይህ አንድነት ጸንቶ እንዲኖር ይጠይቃል፣ ካህን መሆን ማለት እንደ ማንም ባለመዋል በየዕለቱ ቅዳሴ ማሳረግ ሳይሆን ሙላትና ጥልቀት ባለው ሁኔታ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ ክርስቶስ ጋር አንድ በመሆንና ከቤተ ክርስትያኑ ጋር በመዋሃድ የአዳኙን መሥዋዕት እውን ለማድረግና ለመቀጠል የሚፈጸም ተልእኮ መሆን አለበት፣ የቅዱስ ቍርባኑ መሥዋዕት ከሐዋርያዊ ግብረ ተል እኮ የሚለይ ሳይሆን ከእርሱ የሁሉ ተግባር ብቃት እያገኘ የደህነንት እውነትና ኃይል ማእከል ነው፣ በሥነ አ እምሮ አዊና በኅብረተስብ አዊ አመለካከት ብቻ ሳይሆን ሕያውና አምራች በሆነው ሁኔታ በሰው ልጅ ደረጃ የእግዚአብሔር እውን በሆነው ጌታ መኖር ነው፣ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ ተግባሮችዋ የምትፈጽማቸው ነገሮች ስብከትም ይሁን ሌሎች ተግባሮች ከክርስቶስ መሥዋዕት ቢለዩ ኖሮ ትርጉም አልባና ፍሬ አልባ በሆኑ ነበር፣ ለዚህም ነው የክርስቶስ መሥዋዕት ሥር ዓት መፈጸም ለካህናት የተሰጠው፣ እያንዳንዱ ካህን በግል በኢየሱስ ያጣጣመውን ለመኖር የተጠራ ነው፣ ማለትም በሙላት ለስብከተ ወንጌል እና የሰው ልጅን ከሥጋዊና ከመንፈሳዊ ሕመም ለማዳን የኢየሱስ ዘለዓለማዊ ፋሲካዊ ተዝካር በሆነው በምሥጢረ ቍርባን በሚገለጠው ተግባር ሕይወቱን ለሰው ልጆች መሥዋዕት እስከ መሥጠት በሙላት ለመኖር የተጠራ ነው፣
ውድ አዲስ ካህናት የእግዚአብሔር ቃላ ሕይወታችሁን ያብራ፣ የመስቀል ክብደት እጅግ በከበደ ጊዜ ያች ሰዓት ለእናንተም ይሁን ለእናንተ አደራ ለተሰጡ ክቡር ጊዜ መሆንዋን ማወቅ አለባችሁ፣ በማለት አለስጋት በኢየሱስ ተማምነው መልካም እረኞች ሆነው እርሱን መከተል እንዳለባቸው አሳሰብዋቸዋል፣
ከቅዳሴ በኋላ ዕለቱ ዓለም አቀፍ ለጥሪ የሚጸለይበት ቀን መሆኑን በማስታወስ ጥሪው ይበልጥ ወጣቶችን ስለሚመለከት ወጣቶች “በልባቸው ውስጥ ሆኖ የሚናገራቸውንና እርሱን ለማገልገል ሁሉን ትተው እንዲከተሉት ለሚጠራቸው የእግዚአብሔር ድምጽ ጠንቅቀው እንዲያጣምጡ ይሁን” ሲሉ አስተምረዋል፣
እንደ እውነቱ ከሆነ ጌታ ሁል ጊዜ ይጠራል፣ ሆኖም ግን ብዙውን ግዜ አንሰማውም፣ አፍአዊ በሆኑ ድምጾች በብዙ ነገሮች ትኩረታችን ስለሚሳብ እንዲሁም ነጻነታችንን የሚነጥቀን ስለሚመስለን የጌታ ድምጽን ለመስማት እንፈራለን፣ እንደ እውነቱ እያንዳንዳችን የፍቅር ፍሬ ነን፣ እርግጥ ይህ የወላጆቻችን ፍቅር ነው ሆኖም ግን ከዚህ የላቀው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ያፈራን፣ በቤተ ክርስትያን ውስጥ የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት አንድ የፍቅር ታሪክ ነው፣
ውዶቼ እንደተለሳለሰ የእርሻ ስፍራ እግዚአብሔር በብዛት የሚዘራቸው የጥሪ ዘሮች እንዲበቅሉና እንዲበስሉ ስለቤተ ክርስትያን እና ስለእያንዳንዱ ማኅበራችን እንጸልይ፣ በማለት ካስተማሩ በኋላ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አሳርገው ሕዝቡን በተለያዩ ቋንቋዎች በማመስገንና ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.