2012-05-01 17:48:10

3 ሰንበት ዘፋሲካ፤ ኤማሁስ (ሉቃ 24፡13-32)


ር.ሊ.ጳ ስለ ትንሣኤ ያስተማሩት፣ ከዕለተ ትንሣኤ የመጀመሪያ ቀን ማምሻ እንነሣ፣ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አይሁድን ስለ ፈሩ ተሰብስበው የነበሩበት ቤት ደጁ ተቈልፎ ነበር (ዮሐ. 20፤19)፣ ፍርኃት ልብን በማኰማተር ሕይወትንና ሌሎችን ለመገናኘት የሚደረገው እርምጃ ያግዳል፣ እንግዲህ መምህራቸው የለም፣ የሕማማቱ ትውስታዎች ዳግም ለነበራቸው ጥርጣሬ ከፍ እንዲል ያደርጋል፣ ሆኖም ኢየሱስ የእርሱ የሆኑትን በልቡ በማኖር በመጨረሻው እራት “ወላጅ አልባ ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁም፣ ወደ እናንተ እመጣለሁ።” (ዮሐ. 14፤18) ሲል የገባው ቃል ለመፈጸም ይነሣል፣ ዛሬ ለእኛም ግዝያቱ ቢደምንም “ወላጅ አልባ ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁም” ይለናል፣ የደቀ መዛሙርት የትካዜው ሁኔታ በኢየሱስ መምጣት ከሥር መሠረቱ ይለወጣ፣። የነበሩበት ቤት ደጁ ተቈልፎ ሳለ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አላቸው” (ዮሐ. 29፤19)፣ ይህ ተራ የሆነው የሰላምታ ልውውጥ፤ ውስጣዊ ለውጥ የሚያስከትል ደቀ መዛሙርቱ ማንኛው ዓይነት ፍርኃት እንዲያሸንፉ የሚያደረግ የፋሲካ ሰላምታ ተግባር በመሆን አንድ አዲስ ትርጉም ይጎናጸፋል፣ ኢየሱስ የሚሰጠው ሰላም ያ ከደቀ መዛሙርቱ ሲሰናበት “ሰላምን እትውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፣ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደ ሚሰጠው አይደለም፣ ልባችሁ አይደነግጥ አትፍሩም፣ (ዮሐ. 14፡27) ሲል ቃል የገባው የድህነት ጸጋ በውስጡ የያዘ ነው። በዚያች የትንሣኤ ዕለት ሰላምን በሙላት በመስጠት፤ ይኽ ሰላም በማኅበረሰብ ዘንድ የደስታ ድል አድራጊነት፤ በእግዚአብሔር መጠጊያነት ላይ ላለው እርግጠኛነት ምንጭ ይሆናል፣ እኛንም “ልባችሁ አይሸበር፤ ፍርኃት አይኑራችሁ” (ዮሐ 14፤1) ይለናል፣
ከዚህ ሰላምታ በኋላ ኢየሱስ የማይሻረው ድል አድራጊው በሰብአዊነቱ ላይ ጠባሳ ጥሎ ባለፈው የሆነውን የሚያረጋግጡ የእጆቹና የጎኑን ቁስሎች ያሳያቸዋል (ዮሐ. 20፤20)፣ የዚህ ተግባር ዓላማም የትንሣኤ አዲስ ገጽታው ማረጋገጥ ነው፣ እርሱም በደቀ መዛሙርቱ መካከል የተገኘው ክርስቶስ በተጨባጭ ከሦስት ቀናት በፊት በመስቀል የተሰቀለው ሰው መሆኑ ያረጋግጣል፣ በዚህ ብርሃን በሚያንጸባርቀው ፋሲካ አማካኝነት ደቀ መዛሙርቱ የሕማማቱና የሞቱ መድኅናዊ ትርጉም ይገነዘባሉ፣ ስለዚህ ከትካዜና ከፍርሃት ወደ ሙሉ ደስታ ይሸጋገራሉ፣ ሐዘኑና ቍስሎቹ የደስታ ምንጭ ይሆናሉ፣ በልባቸው የሚወለደው ደስታ “ጌታን ከማየት” (ዮሐ. 20፤20) የሚወለድ ነው፣ ዳግም እንዳዲስ “ሰላም ለእናንተ ይሁን (ዮሐ. 20፡19) ሲል፤ ይህ ዓይነት ሰላምታ ተራ ሰላምታ እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል። ጸጋም ነው፣ ይህ ጸጋ የተነሣው ጌታ ለጓደኞቹ የሚሰጠው በመሆኑ፤ የሰጠው ሰላም ኃላፊነት ጭምር እንደሆነም ያሰማል፣ ይኽ ደግሞ ወደ ዓለም ሁሉ የሚያደርሱት ለእነርሱ እና ለሁሉም መሆኑ ከደመ ክርስቶስ የሚጎናጸፈውን ያለው ተልእኮአዊ ትርጉሙን የሚገልጥ ነው ብለዋል፣ ከሞት የተነሣው ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ተገኝቶ፤ እነርሱንም ለመላክ፤ “አብ እኔን እንደ ላከኝ እንዲሁ እኔ እናንተን እልካችኋለሁ” (ዮሐ. 20፤20) ይላል፣ ተልእኮው በዓለም እስከ ፍጻሜ በማድረስ በሁሉም ልብ ውስጥ፤ ያወቀውና ያፈቀረው የተበታተኑትን ልጆቹን በአንድ ጥላ ሥር በሚያሰባስበው አብ ላይ እምነት እንዲያኖሩ የሚያበቃው እምነት መዝራት ይጠበቅባቸዋል፣ ሆኖም ኢየሱስ አሁንም በደቀ መዛሙርቱ ፍርኃት እንዳለ ያውቃል፣ ስለዚህ በእራሳቸው ላይ እፍ በማለት በእነርሱ ላይ መንፈሱን ያኖራል (ዮሐ. 20፤22)፣ ይህ ምልክትም የአዲስ ፍጥረት ምልክት ነው፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የአንድ አዲስ ዓለም ጅማሬ ነው፣ ለደቀ መዛሙርቱ በሚሰጠው ተልእኮ አማካኝነትም በእርሱ እና በእርሱ የማዳን ተግባር የሚያምን የትንሣኤ እውነት የሚመሰክር የአዲስ ቃል ኪዳን ሕዝበ ዓለም ጉዞ በይፋ ይጀመራል፣ በሰው ልጅ ልብ ያለው የሚያደማው የኃጢአት እሾክ ፈንታ ኃጢአትና ሞትን ለሚያሸንፈው የእግዚአብሔር ሕላዌና ፍቅር ለሚያፈራው ጸጋ ቦታ መተው በሁሉም ሥፍራ እንዲስፋፋ የሚያረጋግጠው በፋሲካ የተገኘው ማብቂያ የሌለው የሕይወት ሕዳሴ በሁሉም ሥፍራ መስፋፋት አለበት ብለዋል።
አንዳንዴ በሮቹ ቢዘጉም ከሞት የተነሣው ጌታ ዛሬም በቤቶቻችንና በልቦቻችን እየገባ ነው፣ ለሰብአዊና ለመንፈሳዊ ዳግመ ልደታችን የሚያስፈልጉን ስጦታዎች ደስታና ሰላም ሕይወትና ተስፋ እየሰጠ ይገባል፣ አብዛኛውን ጊዜ የሰው ልጅ በስሜቱ ብግኑኝነቱና በጠባዩ የሚያኖራቸው የመቃብር ድንጋዮችን ለመገልበጥ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፤ እነኚህ ሞትን የሚያመጡ የመቃብር ድንጋዮች መከፋፈል ጥላቻ ቂመ በቀል ቅናት አለመተማመንና ግድ የለሽነት ናቸው፣ ሕያው የሆነው እርሱ ብቻ ለሕይወታችን ትርጉም ሊሰጥ ይችላል፤ የደከመውና ያዘነ እምነተቢስና ተስፋቢስ ለሆነ ጉዞውን ዳግም እንዲጀምር ሊያደርግ ይችላል፣ በፋሲካ ቀን ከኢየሩሳሌም ወደ ኤማሁስ ይጓዙ የነበሩ ሁለቱ ሐዋርያት ይህንን ነው ያጣጣሙት፣ (ሉቃ 24፤13-35) እነርሱ ስለ ኢየሱስ ይነጋገሩ ነበር፤ ፊታቸው ግን በኃዘን ሞልቶ ነበር (ኁ 17)፤ ይህም የደበዘዘን ተስፋ እርግጠኛ አለመሆንና ጥርጣሬን ያመልካታል፣ ኢየሱስን ከጓደኞቹ ጋር ለመከተል አገራቸውን ትተዋል፤ ምሕረትና ፍቅር ቃላት ብቻ ሳይሆኑ ህልውናቸውን ተጨባጭ በሆነ መንገድ የሚያሳስቡ መሆናቸውን የሚያሳይ አዲስ ነገርም አግኝተዋል፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሁሉም ነገር አሳደሰ፤ ሕይወታቸውን ለውጦ አል፣ ሆኖም ግን አሁን እርሱ ሞተ ሁሉም ያበቃለት ይመስላል፣
ድንገት እንደ አጋጣሚ በኤማሁስ ይጓዙ የነበሩ ሁለት ሳይሆኑ ሶስት ሰዎች ነበሩ፣ ኢየሱስ ከሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይጠጋል ከእሳቸውም ይጓዛል፤ ሆኖም እነርሱ ሊያውቁት አልቻሉም፣ እርግጥ ነው ከሞት ስለመነሣቱ ሰምተው ነበር፤ ለኢየሱስም እንዲህ አሉት፤ “ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ ሥጋውንም ባጡ ጊዜ። ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር።” (ኁ 22-23) ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ሊያስተማምናቸው አልቻለም፤ አያይዘውም “ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።” (ኁ 24) ይሉታል፣ ኢየሱስም ት ዕግሥት በሞላበት መንገድ “ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።” (ኁ 27) ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ለሐዋርያት የቅዱስ መጽሐፍ መሠረታዊ የንባብ መፍቻ በመለገሥ ቅዱስ መጽሐፍን ይግለጣል፤ የቅዱስ መጽሐፍ ይዞታም ኢየሱስ ራሱና የእርሱ ምሥጢረ ፋሲካ ነው፤ ለዚህም ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ቅዱሳት ጽሑፎች ሁሉ ለእርሱ ይመስክራሉ ይላልና (ዮሐ 5፡39-47 ተመልከት)፣ የሁሉ ትርጉም ማለት የኦሪት ሕግ የነቢያትና የመዝሙራት ትርጉም ድንገት ግልጥ ይሆንላቸዋል በዓይኖቻቸው በፊትም ሁሉ ጥርት ብሎ ይታያቸዋል፣ ኢየሱስ ቅዱሳት ጽሑፎችን እንዲረዱ አ እምሮ አቸውን ይከፍትላቸዋል (ሉቃ 24፡45 ተመልከት)፣
የሆነ ሆኖ ሐዋርያቱና ኢየሱስ ወደ መንደሩ ምናልባትም ከሁለቱ ሐዋርያት ባንዱ ቤት ይደርሳሉ፣ እንድግዳው ጉዞውን ለመቀጠል እንደፈለገ “እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው” (ኁ 28) ሆኖም ግን “እነርሱ። ከእኛ ጋር እደር፥” (ኁ 29) ብለው ስለለመኑት ከእሳቸው ጋር ይቆማል፣ እኛም ጌታን ደግመን ደጋግመን በጋለ ፍላጎት ከእኛ ጋር እደር ብለን ልንለምነው ይገባናል፣ “ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው” (ኁ 30) ይህ ድርጊት ጌታ በመጨረሻ እራት ያደረገውን እንዲያስታውሱ አደረጋቸው፣ “ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤” (ኁ 31) የኢየሱስ ከእርሳቸው ጋር መኖር መጅመርያ በቃሉ ቀጥሎም በቅዱስ ቍርባን ሐዋርያት እንዲያውቁት ያስችላቸዋል፣ ወዲያውኑ ከእርሱ ጋር በመንገድ ሲጓዙ ይሰማቸው የነበርውን እንደገና ማጣጣም ጀመሩ “እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።” (ኁ 32) ይህ ፍጻሜ ሕይወታችንን የሚለውጥ ከሞት የተነሣ ጌታን ለማግኘት የምንችልባቸው ሁሉት እጅግ የከበሩ ቦታዎች ያመለክታል፣ ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን ቃሉን ማዳመጥና ቅዱስ ቍርባን መሥራትን፤ እነኚህ ሁለት ቦታዎች አንዱ ካለ ሌላው ትርጉም ሊኖረው ስለማይችል ቃልና ቅዱስ ቍርባን ጥልቅ በሆነ መንገድ የተወሃዱና የተሳሳሩ ናቸው፣ ቃለ እግዚአብሔር በቅዱስ ቍርባን ሥር ዓት ምሥጢራዊ ሥጋ ይሆናል” (የቃለ እግዚአብሔር ‘ቨርቡም ዶሚኒ’ ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ቃለ ም ዕዳን 54-55)፣
ከዚህ ግኑኝነት በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት “በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም። ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው።” (ኍ 33-34) እነርሱ በኢየሩሳሌም የኢየሱስ ከሞት መነሣት ብሥራት ያገኛሉ፤ እሳቸውም በበኩላቸው ልባቸውን ወደር ለሌለው ደስታ ስለከፈተላቸው ከሞት በተነሣው ፍቅር ተቃጥለው በኤማሁስ መንገድ ያጋጠማቸውን ይተርካሉ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደሚለው “ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋ ዳግም ተወልደዋል” (1ኛ ጴጥ 1፡3)፣ በዚህም ለእምነት የነበራቸው ጉጉት ለማኅበሩ የነበራቸው ፍቅር እና መላካሙን ዜና ለሌሎች ለማስተላለፍ የነበራቸው ፍላጎት ዳግም ተወለደ፣ መምህሩ ከሞት ተነሣ ከእርሱም መላው ሕይወት እንደገና ተነሣ፤ ይህንን ፍጻሜ መመስከር የማይታመቅ ግዴታ ሆነባቸው፣
ውዶቼ፧ ዘመነ ፋሲካ የእምነት ምንጭ የሆነውን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ በመካከላችን መገኘትን በደስታና በጉጉት ዳግም ለማግኘት እንድንችል ዘንድ ለእኛ ለሁላችን ምርጥ ጊዜ ይሁልን፣ ይህም ማለት የእግዚአብሔር ቃልንና ቅዱስ ቍርባንን እንደገና በማግኘት፡ ኢየሱስ በኤማሁስ መንገድ ይጓዙ የነበሩት ሐዋርያት ጋር ያደረገውን ጉዞ ማድረግ እንደ ማለት ነው፣ ለቅዱስ መጽሐፍ እውነተኛ ትርጉምና እንጌራ በመቍረስ የእርሱ እውነትኛ ኅልውና አይተን ለመቻል ዓይኖቻችንን እንድከፍትልን ከጌታ ጋር መጓዝ አለብን፣ ያኔም እንደ ዛሬ የዚህ ጉዞ ጽንፍ በቅዱስ ቍርባን ከእርሱ ጋር አንድ መሆን ነው፣ በዚሁ ውኅደት ኢየሱስ በሕይወታችን እንዲኖር እንዲያድሰንና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሕይወት እንድናገኝ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ይመግበናል፣
ለማጠቃለል ያህል የሐዋርያት ተመኵሮ የፍሲካ ትርጉም ለመረዳት እንድናሰላስል ጥሪ ያቀርብልናል፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ እንዲያገኘን እንፍቀድለት፣ እርሱ ሕይውና እውነተኛ ነው፤ ሁል ጊዜ በመካከላችን አለ፤ ዓይኖቻችን ለመክፈትና ሕይወታችን ለመምራት ከእኛ ጋር ይጓዛል፣ ከሙታን ተለይቶ የተንሣው ሕይወት እንዲሰጠን እንደ እግዚአብሔር ልጆች ዳግም እንድንወለድ እንድሚያደርገንና ለማመንና ለማፍቀር እንዲያስችለን ችሎታ እንዳለው እንመን፣ በእርሱ ያለን እምነት ሕይወታችንን ይለውጣል፤ ከፍርኃት ነጻ ያወጣታል፤ ጽኑ ተስፋ ይሰጣታል፤ ለሕይወታቸው ሙሉ ትርጉም በሚሰጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይንከባከታል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.