2012-04-30 14:00:57

ፈደራላዊ የኢጣሊያ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ማኅበር


“ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሐምሳ ዓመት በፊትና ከሐምሳ ዓመት ብኋላ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የኢጣሊያ ፈደራላዊ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ማኅበር 61ኛው RealAudioMP3 በኢጣሊያ ኡርቢኖ ከተማ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 25 ቀን እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. መካሄዱ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት እንዳመለከተው በኢጣሊያ የአልባኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ፣ የኢጣልያ ፈደራላዊ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ ማኅበር ሊቀ መንበር አልበርቶ ራቲ የማኅበሩ የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ፍራንቸስካ ሲመዮኒ ወቅታዊት ቤት ክርስትያን፣ ምስክርነትና በመናብርተ ጥበብ በሚል ርእስ ሥር ሰፊ አስተምህሮ በማቅረብ፣ ቤተ ክርስትያን በጉባኤዎችዋ አማካኝነት ወቅታዊነት ላይ በማተኮር ቤተ ክርስትያን እጅግ ወደ ተጎሳቆለው በጠና ድኽነት ወደ ተጠቃው ቅርብ የምታደርግ የእግዚአብሔር ፍቃድ መሆንዋ የተሰመረበት ጉባኤ እንደነበር ያመለክታል።
በመናብርተ ጥበብ የእግዚአብሔር ቃል በጥልቀት ለመገንዘብና ለመኖር የሚያግዝ በመናብርተ ጥበብ በኩል የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ድርገት አማካኝነት የሚሰጠው ድጋፍ፣ እምነትና ምስክርነት በእለታዊ ኑሮ መገለጥ እንዳለበት የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት የሚሰጠው አስተምህሮ ቲዮሎጊያዊ መሠረት ያለው በተሰፋ መኖር፣ ከሌሎች ጋር ለመወያየት የሚያነቃቃ መሆኑ ንግግር ያሰሙት አካላት በተለያየ መልኩ እንዳስገነዘቡት ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ ተጋባእያኑ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ሮማ ፎሪ ለ ሙራ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ጁዘፐ ቶኒይሎ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ባወጀላችላቸው መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሳተፍ ጉባኤው እንዳጠናቀቁ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.