2012-04-30 13:55:12

የእውነት ሰማዕት


እ.ኤ.አ. በ 1120 ዓ.ም. በቅዱስ ኖርበርት የተመሠረተው የፕረሞስትራተንሰ ባህታውያን ማኅበር አባል በፈረንሳይ አብዮት ወቅት እውነትን አልክድም በማለታቸው ምክንያት በአንገት መቅያ ለሞት የተዳረጉት የእምነት ሰማዕት አባ ፒየር አድራይን ቱሎርገ (እ.ኤ.አ.1757 ዓ.ም.- 1793 ዓ.ም.) እ.ኤ.አ. ቅዳሜ RealAudioMP3 ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በይፋ ለብፅዕና አዋጅ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ በመሩት የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ አማካኝነት ብፅዕና እንዳወጀችላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 13 ቀን 1793 ዓ.ም. ኣባ ፒየር አድሪየን ቱሎርገ በ 37 ዓመት ዕድሚያቸው፣ በአንደበታቸው ሐጢአተኛ እያለሁ እንዴት ለደም ሰማዕትነት ልበቃ እችላለሁ። የደም ሰምዕትነት በራስ ላይ የእምነት ዘውድ እንደ መድፋት ነው በማለት የተበየነባቸው የሞት ፍርድ በእምነት ጽናት እንደተረጎሙት የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማህደር ይመሰክረዋል። ዓለምን ክጃለሁ ብየ ሳበቃ የሞት ፍርድ ስለ ተበየነብኝ ተመልሼ የከዳሁትን ዓለም ትቼ ለማለፍ እንዴት ሊከብደኝ ይችላልን? በሚል ጽኑ እምነት መሠረት የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ ብፁዕ የቤተ ክርስትያን ልጅ መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ባሰሙት ስብከት ገልጠው፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “ሰማዕት ሁሉም ቅዱሳት ነቢይ ኢሳያስ ምዕ. 5፣ 20 “ክፉውን መልካም መልካሙንም ክፉ ለሚሉ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው” የሚለው ቃለ ትንቢት ዳግም በሕይወታቸው የሚያስተጋቡ ናቸው በማለት የሰጡት ትርጉም ጠቅሰው፣ በፈረንሳይ አብዮት ወቅት፣ ካህናት ደናግል ምእመናን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሠረታት ለሮማዊት ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ታማኝ በመሆን እምነታችንን አንክድም በማለታቸው ምክንያት የደረሰባችው ስደት መከራ እና በአንገት መቅያ ለሞት መዳረጋቸው አስታውሰው፣ በዚያ መራራው የፈረንሳይ የታሪክ ወቅት ለእስር ተዳርገው እ.ኤ.አ. በ 1793 ዓ.ም. ስለ ሐቅ የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ የቤተ ክርስትያን ልጅ ናቸው። ምንም’ኳ ለስቃይ ለመከራ የተጋለጡ ቢሆንም ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ለጸናው ውህደት በትክክለኛ ቅን ሕይወትና በታማኝነት በመኖር የደም ሰማዕትነት ተቀብለው፣ በዘመናችን በተለያየ ፖሊቲካዊ ርእዮተ ዓለም፣ ስነ ምርምርና ስነ ባህል ተደግፎ ለሚነዛው የሞት ባህል የሚቃወም ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ሊጠበቅና ሊከበር የሚገባው ጸጋ መሆኑ በሕይወት ባህል የሚመሰክሩ ናቸው። ይኸንን የሞት ባህል በጸሎት በትጋትና በጽናት የሚያጋጥመውን ፈተና ሁሉ በማሸነፍ መንገድ እውነትና ሕይወት ለሆነው ክርስቶስ የመሰክሩ ናቸው፣ አብነታቸውንም እንከተል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.