2012-04-30 13:57:01

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ
“ለብዙዎችና ለሁሉም” የሚለው የመሥዋዕተ ቅዳሴ ቃለ ትርጉም


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ቅዳሜ 28 ቀን ሚያዝያ 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ባለፉት ቀናት ለጀርመን ብፁዓን RealAudioMP3 ጳጳሳት ምክር ቤት በመሥዋዕተ ቅዳሴ በምልዋጥ ሥነ ሥርዓት ጊዜ እርሱም ካህን ወይኑን ወደ ደመ ክርስቶስ ሲለውጥ የሚገለግልባቸው “ለብዙዎችና ለሁሉም” የሚሉት ቃላቶች ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ትርጉማቸውና ልዩነታቸውን የሚያብራራ ያስተላለፉት መልእክት ርእሰ ጉዳይ በማድረግ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በላቲን ሥርዓት የተከበረው በዓለ ፋሲካ በኋላ ቀጥሎ የዋለው ሳምነት በካስተልጋንደልፎ ባሳለፉበት ወቅት በትውልድ አገር ቋንቋቸው ለጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ልዩና ቀጥተኛ መመሪያ አዘል መልእክት ካህን ወይን ወደ ደመ ክርስቶስ ሲለወጥ ለብዙዎች የሚለው የሚጠቀምበት የቃል ትርጉም ለሁሉም የሚለው ትክክለኛ እና ታማኝ የሆነው ቃለ ትርጉም መጠቀም ያስፈልጋል በማለት በክርስቶስ የተፈጸመው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ኵላዊነት አድማሱን ግልጽ አድርገዋል።
ቅዱስ አባታችን የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሕይወት ግንድ የሆነውን የቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ ለሁሉም ግልጽ መሆን እንዳለበት በመገንዘብ ለብቹዎች የሚለው ነቢይ ኢሳያስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የማንነት አንድነት ለይቶ ሲያቀርብ ለብዙዎች የሚለው ቃል ሲጠቀም፣ እማኔ ያለው ክሌአዊ ገጽታው እርሱም ለኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ታማኝና የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝነት ለቃለ ቅዱስ መጽሓፍ የሚያረጋግጥ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ለማዳን መሞቱን የማያጠራጥር ነው። ይኽ እውነት ለምእመናን በጥልቅ ማስረዳት የትምህርተ ክርስቶስ እቅድ ኃላፊነት ነው። ስለዚህ የቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ ቃላቶች ጥልቅ ትርጉሙ ማስርዳትና ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ለእናንተ እና ለብዙዎች” ገዛ እራሱን ይሰዋል። እንዲህ በሚለው ቃል አማካኝነት በቀጥታ በጉዳዩ ተካፋዮችና ባለ ውለታዎች በመሆን ለሁሉም ቃል ለተገባው የማዳን እቅድ ኃላፊነት እንዳለብን ያስገነዝበናል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ ናዝራዊ በተሰየመው በተከታታይ መጽሐፎቻቸው ዘንድ ተብራርቶ የምናገኘው ጥልቅ ሐሳብ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገዛ እራሱን በመሰዋት፣ ጥልቅና ማራኪ አብነት የትምህርተ ክርስቶስ መሠረት ነው። ቃለ እግዚአብሔር ከመኖር የሚገኝ ፍቅርና የመከባበር ሕንጸት ነው። ይኽ ሕንጸት ቅዱስ ቁርባንን በጥልቀት ለመኖርና የተጠራን መሆናችን የሚያበክር ነው። ቅዱስ አባታችን ይኸንን በጥልቀት ቲዮሎጊያዊ መንፈሳዊ መሠረታዊ ትርጉሙን የሚያብራራ መልክት በማስተላለፍ በታወጀው በእምነት ዓመት ለመገንዘብና ለመኖር መጠራታችን አስምረውበታል በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.