2012-04-26 17:30:26

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (25.4.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ባለፈው ትምህርተ ክርስቶስ፣ ቤተ ክርስትያን ከመጀመርያ ጉዞዋ ጀምራ ከተለያዩ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች፣ አዲስ ጥያቄዎችና አደጋዎች ባጋጠምዋት ቍጥር መጋፈጥ እንደነበራትና መንፈስ ቅዱስ እዲመራት በመተው ለእነዚህ ሁኔታዎች በእምነት ብርሃን መልስ ለመስጠት ትታገል ነበር። ዛሬ ከእነዚህ ሁኔታዎች ስላንዱ ለመጀመርያዋ የኢየሩሳሌም ማኅበረ ክርስትያን ያጋጠማት አሳሳቢ ሁኔታ መናገር እወዳለሁ። ቅዱስ ሉቃስ በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ ስድስት እንደሚተርከው፣ ማለት ለብቸኞችና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው መደረግ ስለነበረው የግብረ ሠናይ ተል እኮ ነው። ጥያቄው በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ አልነበረም፣ ያኔ በቤተ ክርስትያን ውስጥ መከፋፈልን ሊያስከትል ይችል ነበር፣ የተከታዮቹ ቁጥር እያደገ መጣ ሆኖም ግን የግሪክ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዕብራዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ያጕረመርሙ ነበር፣ ምክንያቱም ጋለሞታቸው በዕለታዊ የምግብ እደላ ስለተጓደለባቸው ነው (ግሐ 6፡1 ተመልከት)። በዚሁ በማኅበሩ ሕይወት አንጻር መሠረታዊ የሆነው አፋጣኝ ሁኔታ ማለትም ለአቅመ ደካሞች ድሆችና ተንከባካቢ አልባዎች ይደረግ የነበረው ምግብረ ሠናይ እና ፍትሓዊነት፣ ሐዋርያት መላውን የተከታዮቻቸው ቡድን ይሰብስባሉ። በዚሁ የግብረ ተል እኮ አስቸኳይ ስብሰባ የሐዋርያት አስተዋይነት ይታያል። ከጌታ የተሰጣቸው ዋነኛ ተልእኮ ቃለ እግዚአብሔር መስበክ ሲሆን የምግባረ ሠናይ አስፈላጊነትም ተቀዳሚ ተል እኮ ሆኖ ያገኙታል፣ ስለዚህ የምግባረ ሠናይ እና የፍትሕ ተለእኮን ማለት ጓለሞትች ድሆችን የመርዳት ግዴታ እንዲሁም “እኔ እንደወደድክዋችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ” (ዮሐ 15፡12.17) የሚለውን የኢየሱስ ትእዛዝ ለማክበር፡ ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸውን ለማግኘት የሚመጡ ችግረኞችን በፍቅር የመንከባከብ ግዳጆችን ረጋ ብለው በአስተዋይነት ይመረምሩታል። ስለዚህ በቤተ ክርስትያን መኖር ያለባቸው ሁለቱ ነገሮች፣ ለእግዚአብሔር ቅድሚያ የሚሰጥ ስብከተ ወንጌልና ፍትሕ የሚያመለከት ተጨባጭ ምግባረ ሠናይ ችግር እየፈጠሩ ናቸው፣ እያንዳንዳቸው ተገቢ ቦታቸው እንዲይዙና አስፈላጊ ግኑኝነት እንዲኖራቸው ደግሞ መፍትሔ ሊገኝባቸው ይገባል። የሐዋርያቱ ንግግር ጥርት ያለ ነበር፣ እንዲህም ይላሉ፣ “አሥራ ሁለቱም ደቀ መዚሙርት ሁለን ጠርተው እንዲህ አልዋቸው። የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገገልግል ዘንዴ የሚገባ ነገር አይደልም። ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” (ግሐ 6፡2-4) ሁለት ነገሮች ይከሠታሉ፡ አንደኛው በቤተ ክርስትያን ከዛ ዕለት ጀምሮ የምግባረ ሠናይ ተል እኮ ይመሠረታል። ቤተ ክርስትያን ቃለ እግዚአብሔርን ብቻ መስበክ የለባትም፣ ነገር ግን እውነትና ፍቅር የሆነውን ይህን ቃል እተግባር ላይ መዋል አለባት። ሁለትኛ ነጥብ ደግሞ፣ እንኚህ ሰዎች በመልካም ብቻ የተመሰከረላቸው መሆን የለባቸውም፣ መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላቸው ሰዎች መሆን አለባቸው። ይህም ማለት የተግባር ሰዎች በመሆን አቀናባሪዎች ሆነው ጥሩ ዝና ያላቸው ብቻ መሆን ሳይሆን፣ ይህንን ነገር በእምነት መንፈስ በእግዚአብሔር ብርሃን እና በልብ ጥበብ ሊያደርጉት ይገባል፣ በዚህም ተልእኮአቸው የተግባር ሳይሆን ከሁሉ በላይ መንፈሳዊ አገልግሎት ይሆናል። ምግባረ ሠናይና ፍትሐዊነት ኅብረተሰብአዊ አገልግሎቶች ብቻ አይደሉም፣ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን የሚፈጸሙ መንፈሳዊ ተግባሮች ናቸው።

ስለዚህ ሐዋርያት ይህንን ሁኔታ በታላቅ ኃላፊነትና ጥንቃቄ ተመለክተው ይህንን ውሳኔ አጸደቁ ለማለት እንችላለን፣ ሰባት ሰዎች ይመርጣሉ፣ ሐዋርያትም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከለመኑ በኋላ ሰዎቹ በልዩ መንገድ ለምግባረ ሠናይ ድያቆናዊ አገልግሎት ብቻ እንዲሆኑ እጆቻቸውን ያኑሩላቸዋል። እንዲህ ባለ ሁኔታ በቤተ ክርስትያን የመጀመርያ እርምጃዎች ልክ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ዘመን በማርያምና ማርታ ቤት ሳለ እንዳጋጠመ ይሆናል፣ ያኔ ኢየሱስ በማርያምና ማርታ ቤት በተገኘበት ወቅት ማርታ ኢየሱስንና ሐዋርያትን እንድታስተናግድ አገልግሎት ሲበዛት ማያም ግን ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር ተቀምጣ ነበረች (ሉቃ 10፡38-32)። በሁለቱም ሁኔታዎች የጸሎትና ቃለ እግዚአብሔር የማዳመጥ ጊዜ እና በዕልታዊ ተግባር ምግባረ ሠናይ ማድረግ እንደተቃራኒ አልታዩም። ኢየሱስን ማርታን “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዘ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” (ሉቃ 10፡41-42) የሐዋርያት አስተያየትም ተመሳሳይ ነው “እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” (ግሐ 6፡4) አሉ፣ ሁለቱም ለእግዚአብሔር ቅድምያ መስጠት እንዳለብን ያመለክታሉ። የማርታና ማርያ ታሪክ አንድምታ ውስጥ ለመግባት አልፈልግም፣ ያም ሆኖ ይህ የሚያመለክተው እንግዳን ማስተናገድ ከነጭራሹ ማውገዝ ሳይሆን አገልግሎቱ ሲደረግ በኅሊናዊ የአስተንትኖ መንፈስ መሸኘት እንዳለበት ያመለክታል። በሌላ በኩል ቅዱስ አጎስጢኖስ ስለዚሁ የማርያም ጉዳይ ሲተረጕመው በሰማያት የሚምንሆነውን ሁኔታ ይገልጣል፣ እዚህ መሬት እያለን በሙላት ልናገኘው አንችልም ሆኖም በመላው ተግባራችን የዚሁ ሰማያዊ ነገር ቅድመ መጣጣም እንዲኖረን ስለ እግዚአብሔር ማስተንተንም አለብን ይላል። በሕይወታችን በተግባር ብቻ ጠልቀን መቅረት የለብንም፣ ግን ዘወትር በተግባራችን ወስጥ የቃለ እግዚአብሔር ብርሃን እንዲገባ እንፍቀድለት፣ በዚህም ብዙ ነገሮች የማያስፈልገው እውነተኛ ምግባረ ሠናይን እንማር፣ እርግጥ ነው አንዳንድ ነገሮች ያስፈልጉታል ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ የሚያስፈልገው የልባችን ፍቅር እንዲሁም የእግዚአብሔር ብርሃን ያስፈልገዋል።
ቅዱስ አምብሮዝዮስ የማርታና የማርያም ታሪክ ሲተነትን ለም እመናኑ “እኛም የእግዚአብሔር ቃልን ልብ ብለን በጥሞና በማዳመጥ ማንም ሊወሰድብን የማይቻለውን ነገር እንዲኖረን ይሁን፣ በመንገድ ላይ የወደቁ እንደሆነ የሰማያዊ ዘር ቃላት ሊነጠቁ ስለሚቻል፣ አንተም እንግዲህ እንደ ማርያም ትልቁና ፍጹም ተግባር የሆነውን ቃሉን የመስማት ጉጉትህን አንሳሳ፣” ካለ በኋል “ሰውን የመርዳት አገልግሎት ሰማያዊ ቃልን ከማወቅ እንዳያሳንክል ተጠንቀቅ” በማለት ከጸሎት ከሚያሰናክል ነገር መጠንቀቅ እንዳለብን ያስተምራል። ስለዚህ ቅዱሳን በጸሎትና በሥራ መካከል እንዲሁም በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ፍቅርና የወንድማሞች ያለውን ጥልቅ አንድነት አጣጥመዋል። በአስተንትኖና በሥራ መካከል ለሚኖር አንድነት ምሳሌ የሆነ ቅዱስ በርናርዶስ ለር.ሊ.ጳ ኢኖቸንዞ 2ኛ በጻፈው ደ ኮንሲደራዝዮነ መጽሓፉ ውስጥ ስለ ተል እኮው ሲያብራራ፣ የምንገኝበት ሁኔታ እና መፈጸም ያለብን ግዳጅ የሆነ ይሁን፣ መጠን በሌለው ሥራ ከመጥለቅ አደጋ ለመዳን የኅሊና ምርመራ እና የጸሎት አስፈላጊነት ያስምርበታል፣ በብዙ ነገር የተያዝን እንደሆነና ዕረፍት የሌልበት ሕይወት ያለን እንደሆነ ብዙውን ጊዜ ልባችን በመደንደንና መንፈስን በማሳቃየት እንቀራለን” ይላል።
ሁሉን ነገር በምርትና በብቃት ለመምዘን ለምንሻ ለኛ፡ ይህ ሁኔታ፡ ክቡር ማስታወሻ ነው፣ እላይ ያየነው የግብረ ሐዋርያት ጥቅስ የሥራ አስፈላጊነትን ያሳስበናል፣ አለምንም ጥርጣሬ ይህ ሁኔታ ልዩ ተል እኮ ይፈጥራል፣ የግብረ ዲቍና ግብረ ተል እኮ፣ ይህም ዕለታዊ ተግባሮች በኃላፊነትና በመስዋዕትነት መደረግ እንዳለባቸው ሲያመልከት በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልገን ማለት ኃይልና ተስፋ የሚሰጡን የእርሱ መሪነት የእርሱ ብርሃን እንደሚያፈልጉን ያመለክታል፣ በእምነት ከሚደረግ ዕለታዊ ጸሎት ሥራችን ሁሉ ባዶሽ ነው፣ ጥልቅ መንፈሱን ያጠፋል፣ ወደ ትርጉም አልቦ እንቅቃሴ ይወርዳል፣ በመጨረሻም እርካታ ቢስ ሆነን እንቀራለን፣ በክርስትያን ባህል ማንኛውም ሥራ ከመጀመራችን በፊት መድገም ያለብን አንድ ጥሩ ጸሎት አለች እንዲህም ትላለች፣ “ጌታ ሆይ! እያንዳንዱ ንግግራችንና ተግባራችን በአንተ እንዲጀምርና በአንተ እንዲፈጸም ተግባሮቻችንን ሁሉ በመንፈስህ ቀስቅስ በእርዳታህም ዐጅባቸው፣” እያንዳንዱ የሕይወታችን እርምጃ፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የቤተ ክርስትያንም ሳይቀር በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን በእርሱ ፊት መደረግ አለበት፣
ባለፈው ዕለተ ሮብ ባቀረብኩት ትምህርተ ክርስቶስ የመጀመርያዋ ማኅበረ ክርስትያን በፊታቸው የተደቀነ ፈተናን ለማጋፈጥ ያቀረቡት በቅዱስ መጽሐፍ አስተንትኖ የተዋሃደ ጸሎት የሚሆኑትን ነገራት ለመረዳት እንዳስቻላቸው አይተናል፣ ጸሎታችን በእግዚአብሔር ቃል የተሸኘ እንደሆነ ነገሮችን በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለሚፈጸሙ ነገሮች አዲስ ብርሃን በሚሰጥ የጌታ ዓይን በአዲስ ዓይን ለማየት እንችላለን፣ እኛ በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ኃይል እናምናለን፣ ቤተ ክርስትያን በምታደርጋቸው አገልግሎቶች ምግባረ ሠናይ በሚመለከት ድኆችን ለማገልግለ የምትጋፈጣቸው ችግሮችን ሳይቀር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ማለትም በእግዚአብሔር ብርሃን በጸሎት ነው የምታሸንፈው፣ ሐዋርያት የእስጢፋኖስና የሌሎቹ ሰዎች መመረጥ ለማጽደቅ ብቻ አይወሰኑም፣ ሆኖም ግን በግብረ ሐዋርያት እንደሚያመለክተው “ከጸለዩ በኋላ እጆቻቸውን አኖሩላቸው” (ግሐ 6፡6) ይላል፣ ወንጌላዊው ሉቃስ እነዚህን የእጅ ማኖር ሁኔታ በጳውሎስና በባርናባ ምርጫ ግዜ “ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን በማኖር አሰናበትዋቸዋል” (ግሐ 13፡3) ይላል፣ ይህ ሁኔታ የሚያረጋግጠው ነገር ያለ እንደሆነ የምግባረ ሠናይ አገልግሎት መንፈሳዊ አገልግሎት መሆኑና ሁለቱም ነገሮች አብረው መሄድ እንዳለባቸው ያመለክታል፣
ሐዋርያት እጅ በማኖር እግዚአብሔር ለሰባቱ ሰዎች ለተመረጡት አገልግሎት የሚገባ ጸጋ እንዲሰጣቸው ይማጠናሉ፣ “ከጸለዩ በኋላ” የሚለው ሐረግን ያሰመሩበት ምክንያት የተግባሩን መንፈሳዊ ጎን ለመግለጽ ወይንም የሆነ መንፈሳዊ ሥልጣን ለመስጠት ብቻ የተጠቀሙት ተግባር ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስያትን በተመሩጡት ሰባት ሰዎች ላይ የሚያድርና እውነት በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የሚቀባቸው እርሱ ራሱ በሐዋርያቱ እጅ ማኖር በጸጥታ በውስጣቸው ሆኖ እንደሚሠራና ለሚገጥምዋቸው ፈተናዎች የሐዋርያዊ አገልግሎት ትግሎች ለመጋፈጥ እንዲችሉ ዘንድ በሥልጣኑ እንዲለወጡና እንዲቀደሱ ያደርጋቸዋል፣ ይህ የጸሎት ማስመር የሚያሳስበን ነገር ካለ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር ብምናደርገው ጥልቅ ግኑኝነት በቤተ ክርስትያን አማካኝነት ለሚሰጠን አገልግሎት እና በጌታ ለሚቀርብልን ጥሪ መልስ ይወለዳል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ሐዋርያት በጸሎትና ቃለ እግዚአብሔርን ለመስበክ ብቻ እንዲሰማሩ፣ ሰባት ሰዎች እንዲመርጡና ለምግባረ ሠናይ አገልግሎት እጃቸውን እንዲያኖሩላቸው ያደረገው ግብረ ተልእኮአዊ ችግር ለእኛም ዘወትር ይህንን ተግባር በሚያመንጨው ጸሎትና ቃለ እግዚአብሔር ቅድምያ እንድንሰጥ ያመለክትልናል፣ ለነፍሳት እረኞች ይህ ተግባር ተቀዳሚ እና ከሁሉ በላይ የሆነ አቋም ነው፣ እንደ ሳንባዎች ልናያቸው የምንችል የጸሎትና የቃለ እግዚአብሔር አስተንትኖ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ተገቢ እስትንፋስን ካልሰጡት በየዕለቱ በሚያገጥሙን ስፍር ቍጥር የሌላቸው ተግባሮች ትወጠን እንዳንቀር የሚያዳግት ነው፣ ጸሎት የመንፈሳዊ ሕይወታችን እስትንፋስ ነው፣ ሌላ ላስምርበት የምፈልገው ነገር አለ፡ ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ግኑኝነት የእግዚአብሔር ቃል በምናዳምጥበት ጊዜ እንዲሆም ከእግዚአብሔር ጋር ስንወያይ በባዶ ቤተ ክርስትያን ወይንም በቤታችን ውስጥ በጸጥታ ስንጸልይ ከእግዚአብሔር እና በእምነት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጋር አንድ እንሆናለን፣ ሁላችው በቅኝት እንደተወሃሃዱ መሣርያዎች በየግላቸውም ይሁን አንድ ትልቅ የተወሃሃደ የጸሎት ቅኝት የምስጋናም ይሁን የክብር ስባሔ ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣









All the contents on this site are copyrighted ©.