2012-04-25 14:12:10

ፈረንሳይ


የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የአገሪቱ ክርስትያን ምእመናን የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ አንቀጸ ሃይማኖት ትምህርት መሠረት በማድረግ ተፈጥሮን የመንከባከብ ባህል እንዲያጎለብቱ RealAudioMP3 ጥሪ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ የአገሪት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በሥነ ምኅዳር ዙሪያ ለሁለት ዓመት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት የሚመለከተው አንቀጸ ሃይምኖት መሠረት በማድረግ በትሮየስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርክ ስተንገር የተመራ ጥናት በማካሄድ አካባቢና ሥነ ምኅዳር በሚል ርእስ ሥር ባወጣው ሰነድ፣ በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ሥነ ምኅዳር የሚመለከተው አንገብጋቢ ጥያቄ ፈጽሞ እንዳይነሳ ወይንም እንዲዘነጋ ማድረጉንም ሰነዱን የጠቀሰው አፒክ የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ ማኅበረ ክርስትያን በአካባቢው የሚከሰቱት ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ቀውሶች እንዲሁም የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ክስተቶች በክርስትያናዊ እምነት አመለካከት ሥር ለማንበብ እንዲችል አቅሙና ክርስትያናዊ አመክንዮ የተከተለ አስተያየት የማቅረብ አቅሙም እንዲያጎለብት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን አንቀጸ ሃይማኖት የተደገፈው ስለ ማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት ጠንቅቆ እንዲያውቅ መደገፍ አለበት የሚል ሃሳብ የሰፈረበት መሆኑ ገልጠዋል።
ሥነ ምኅዳር በተመለከተ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በመወጠን ማኅበረ ክርስትያን ሰብአዊ ሥነ ምኅዳር እንዲያስፋፋ ማነቃቃት ሁሉንም የፈጠረው እግዚአብሔር በመጸለይና በማክበር ተፈጥሮን መንከባከብ፣ ፈጣሪን ማክበር ፍጠርት ሁሉ ለመንከባከብ እና ለማክበር የሚያነቃቃና የሚያሳድግ መሆኑ የፈረንሳይ ብፁዓን ጳጳሳታ ሰነድ በማረጋገጥ፣ ክርስትያን ማኅበረሰብ ተቀባይነት ያለው ተፈጥሮና ፍጥረትን የሚያከብር የቤተ ክርስትያን ትምህርት መሠረት ያደረገ የልማት እቅድ ለወጠን በሚካሄደው ጥረት ይተጋ ዘንድ እንዳሳሰቡም አፒክ የዜና አገልግሎት አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.