2012-04-25 14:06:12

አርጀንቲና


የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከትላትና በስትያን የጀመረ እ.ኤ.አ. እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚዘለቀው 103ኛው ምሉእ ጠቅላይ ጉባኤው ቦነስ አይረስ በሚገኘው RealAudioMP3 ኤል ሰናኩሎ ተብሎ በሚጠራው ቤተ ሱባኤ ባለው የጉባኤ አዳራሽ እያካሄደ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት ሲገለጥ፣ የጉባኤው ዋናው ርእስ፣ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አባታችን “የእምነት በር” (ግብረ ሐዋርያት ምዕ. 14፣ 27) ርእስ በማድረግ ባላቸው ጴጥሮሳዊ ልዩ ሥልጣን ውሳኔ መሠረት ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት ሥር እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እስክ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም የእምነት ዓመት ዓዋጅ ማእከል በማድረግ እንዲሁም የአርጀንቲና አዲስ ሕገ መንግሥት የጤና ጥበቃና የሕይወት ጥበቃ የሚመለከት አንቀጽ የሚያመለክተው ሐሳብ፣ የሥነ ምኅዳር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ በአገሪቱ ስለ ተካሄደው ብሔራዊ የትምህርተ ክርስቶስ ጉባኤና ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ ርእሰ ጉዳዮች መሠረት እየተወያየ መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.