2012-04-23 14:17:36

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ
ወደ ስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጴጥሮሳዊ አገልግሎት


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ፈቃድ በኵላዊት ቤተ ርክስትያን የተሾሙበት እ.ኤ.አ. የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ሰባተኛ አመት መታሰቡ፣ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት RealAudioMP3 ማገባደጃ በሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በማስታወስ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን የተሾሙበት ሰባተኛው ዓመት መታሰቢያ ለስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጴጥሮሳዊ አገልግሎት መባቻ ነው በሚል ርእስ ሥር ትላትና ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ፣ ቅዱስነታቸው 85ኛው ዓመተ ልደታቸውን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሶስት ቀን በኋላም የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታዮ እንዲሆኑ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ሰባተኛው ዓመት ምክንያት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለእግዚአብሔር ምስጋና የቀረበበት እና ለቅዱስ አባታችን በሁሉም ሥፍራ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጸሎትና የደስታ መግለጫ መልእክት እና ከተለያዩ አገሮች መንግሥታት የደስታ መግለጫ መልእክት መተላለፉ አስታውሰው፣ ከቅዱስ ፒዮስ 10ኛ ማኅበርሰብ ጋር ለውህደት ያቀናው የጋራው ውይይት እፍጻሜ ያደርሱ ዘንድ እንመኛለን፣ በዚህ ዘንድሮ በሚላኖ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ምክንያት በሚላኖ ከተማ የሚፈጽሙት ሓዋርያዊ ጉብኝት፣ ለቤተ ክርስትያን ኅዳሴ እየሰጡት ያለው ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ በዱብሊን ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ምክንያት በአየር ላንድ የሚፈጽሙት ሓዋርያዊ ጉብኝት ለቤተ ክርስትያን ለውጥና ሕዳሴ መሠረት እንደሚሆን፣ በእቅድ ተይዞ ያለው የሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም መሠረት የሆነው እውነትና ተስፋ የሚነቃቃበት እንደሚሆን የሁላችን እምነት መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ በማስታወስ፣ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በዚህ 50ኛው ዓመት የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ በምታስታውስበት ወቅት፣ ቅዱስ አባታችን የሁለተኛው ጉባኤ ውሳኔዎች በሁሉም ዘንድ በትክክልና በእውነተኛው አገላለጥ መሠረት እንዲሰርጽ የሚሰጡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ለማነቃቃት የሚሰጡት መሪ ቃል ያወጁት የእምነት ዓመት፣ በበዓል ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ማኅበረ ክርስትያን በግልም ሆነ በማኅበር ከእግዚአብሔርና ከእግዚአብሔር አንዳይ ልጅ ከሆነው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላቸው ግኑኝነት በመኖር የሚመሰክሩበት ወቅት መሆን እንዳለበት እየሰጡት ያለው ሥልጣናዊ አስተምህሮ ጭምር በማስታወስ፣ ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር የደረሱዋቸው የሁለቱ ተከታታይ መጽሓፎቻቸው ማጠቃለያ ሶስተኛው ተከታታይ መጽሓፍ እንዲሚለግሱን ተስፋችን ነው። ዓለም አቀፍ የሪዮ ደ ጃነይሮ የወጣቶች ቀን ቅዱስነታቸን ለማስተናገድ ከወዲሁ በመካሄድ ላይ ያለው ቅድመ ዝግጅት አባ ሎምባርዲ አስታውሰው እግዚአብሔር የቅዱስ አባታችን ስምንተኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዓመት አገልግሎታቸው ይባርክ በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.