2012-04-23 14:15:27

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ “ፖሊቲካና ኤኮኖሚ ከሥነ ምግባር ጋር ያልተቆራኙ መሆን አይችሉም”


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ፣ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ 21 ቀን ሚያዝያ 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ ካላብሪያ ክፍለ ሃገር የካታንዛሮ አውራጃ ርእሰ ከተማ ካታንዛሮ ከሚገኘው ከማኛ ግረቻ መንበረ ጥበብ በሥነ ሕግ የክብር ሊቅነት ማዕርግ ተቀብለው ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ ከወንጀል RealAudioMP3 ቡድኖች እና ሕገ ወጥነት ከሚያረማምዱት ቡድኖች በሚሰነዝሩት ዛቻ ሳትበገሩ እውነተኛ ሕይወትን የሚዘራውና የሐቅ ኃይል የሆነው የሚደግፍ የእግዚአብሔር ቃል በጽናት ለማስፋፋት እትፍሩ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
የብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ሥልጣናዊ አስተምህሮ ዋና ርእስ “በሜዲትራንያን ክልል የኤውሮጳ መጻኢ ምን ይሆን” የሚል መሆኑ ሲገለጥ፣ በኤውሮጳ የተረጋገጠው ኅብረት፣ የጋራው የኅብረቱ ገንዘብ በኤኮኖሚ እና በቁጠባ ሥር መኖር በርግጥ አስፈላጊ ነው። ሆኖም ግን ኅብረቱ እጅግ ጥልቅ የሆነ የውህደት መሠረት እርሱም ሰብአዊነት ካለው ሰብአዊ መብት እና ክብር ብሎም የማይታበውለ ግዴታና ከነገር ባሻገር የሚያቀናው በኑባሬ የታደለው ባህርዩ ማእከል ያደረገ መሆን አለበት እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ማኅበረ ክርስትያን እና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ሁለቱም ለአዲሲቷ ኤውሮጳ ሰብአዊ ማኅበርሰብ አገልግሎት የሚጠመዱ መሆናቸው ገልጠው፣ ስለዚህ በዚሁ ዘርፍ ማኅበረ ክርስትያን ተቀዳሚውን ሥፍራ በመያዝ ለጋራ ጥቅም አቢይ አስተዋጽኦ ማቅረብ ይጠበቅበታል። በሜዲትራኒያን ክልል የሚገለጠው የኤውሮጳ መጻኢ፣ በመዲትራኒያን የባህር ክልል በመገናኘት በሚከናወነው የንግድ ልውውጥ ብቻ ሳይሆን፣ በባህል በሥልጣኔ በሥነ መግባር ባህል በፖለቲካ ባህል፣ በሃይማኖት ባህል ጭምር የሚገለጥ ነው። ስለዚህ ይኽ መስቀለኛው መንገድ የሆነው የክልሉ ባህልና ሥልጣኔ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲረጋገጥ ለሚያግዝ አገልግሎት አንቀሳቃሽ ሞተር መሆን አለበት። የኤውሮጳ ኅብረት መሠረት ከፖለቲካ እና ከኤኮኖሚ ጋር የተጣመረ ሥነ ምግባርና ሰብአዊ መብት እና ክብር መሆን እንደሚገባው ነው ካሉ በኋላ፣ ኤውሮጳ የሰብአዊ መብት እና ክብር ክፍለ ዓለም ነች፣ ሆኖም የውህደቱ መሠረት ከዚህ መለያ ውጭ የሚታይ ከሆነ ኅብረቱ የመሆን አመክንዮውን ያጣል። የኤውሮጳ ባህላዊ ቅርስ ለሰብአዊ መብት እና ክብር የሰብአዊ እኩለት ሥነ ሃሳብ ምንጭ የሆነው በፈጣሪ እግዚአብሔር ኅላዌ እርግጠኝነት የጸና መሠረት ያለው ነው። ስለዚህ በማንኛውም ዘመን ይኽ ለኤውሮጳ ሥነ ምግባር መሠረት የሆነው ለሚከሰተው ወቅታዊ ተጋርጦ ገጥሞ ለማሸነፍ የሚያበቃ መንገድም ነው በማለት፣ ውህደት መተባበር መደጋገፍ የኅብረተሰብ ማእከል የሆነውን ቤተሰብ የሚያበረታታ ፖለቲካ መረጋገጥ አለበት። በፖለቲካ እና በሃይማኖት መካከል መቀራረብ መወያየት አስፈላጊ ነው። የሚጋረጥብንን እክል በፖለቲካ እና በኤኮኖዊ ዘርፍ ብቻ መመልከቱ መፍትሔ አይሆንም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.