2012-04-23 14:13:33

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ክርስትና የባህል እርሾ ነው”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ 88ኛው ቀን ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት፣ የክርስትናው እምነት የባህል እርሾ፣ ለመግባባትና ለውህደት ብርሃን፣ የእድገት በጠቅላላ RealAudioMP3 ለሁሉም ለሐቀኛው ሰብአዊ ጥቅም መረጋገጥ ለሚያግዘው አወንታዊው እምቅ ኃይል ግፊት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የአንዲት አገር መጻኢ በወጣት ትውልድ ልብ ዘንድ መሆኑ አብራርተው፣ ኃሴት እና ተስፋ የተሰየመው የሁለተኛው ቫቲካን የውሳኔ ሰነድ ዋቢ በማድረግ፣ “የሰብአዊ መጻኢ መቀመጫው ለነገው ሕይወት ተረካቢው ትውልድ የሕይወትና የተስፋ አመክንዮ የማስተላለፍ ብቃት ባላቸው ዜጎች እጅ ነው። በዚህ ራእይ ካቶሊካውያን መናብርተ ጥበብ ለክርስትያናዊ መለያቸው ታማኞች በመሆን፣ የላቀው እውቀት የሚኮተኮትበት፣ ሥነ ምርምር ወደ ሥነ ጥበብ የሚያድግበት ባለ ቤት በእሴቶችና በእወቅት ድረጃ ሳይገነጣጠል የተሟላ የሰብአዊነት አድማስ የሚለው ጽማሬ ሐሳብ ግንዛቤ የሚደረገበት ሥፍራ መሆን አለበት። አንድ መንበረ ጥበብ ካቶሊካዊ የሚያሰኘው የተሟላ ሰብአዊ ሕንጸት የሚሰጥበት ሥፍራ በመሆኑ ነው።
በእምነት አማካኝነት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚደረገው የተጨባጭ ግኑኝነት ገጠመኝ፣ የግል ሕይወት የሚለውጥ እና ሌሎችን ለማገልገልና ለኅብረትሰብ ህዳሴ መሠረታዊ ምክንያት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት አብራርተው፣ ስለዚህ መቼም ቢሆን የክርስትናው እምነት የባህል እርሾ ለመግባባትና ለውህደት ብርሃን፣ የእድገት በጠቅላላ የሁሉም ለሐቀኛው ሰብአዊ ጥቅም መረጋገጥ ለሚለው አወንታዊው እምቅ ኃይል ግፊት ነው። ተጽእኖ ሳይሆን ለሥነ ሰብእ ጥናትና ለሥነ ትምህርት አሰጣጥ መሠረትም ነው። ይኸ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ኃላፊነት በተለያዩ ሰበካዎች የመናብርተ ጥበብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርሃ ግብር እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የሚያሳስብ ነው። ቤተ ክርስትያን የሰው ልጅ በሙያ ዘርፍ በተሰማራበት፣ በሥራ መስክና በሚማርበት ሥፍራ ሁሉ በመገኘት ቃለ ወንጌል ለግላዊ እና ለማኅበራዊ ኅልውና መሠረት መሆኑ ለመመስከር እና ለማበሠር ተጠርታለች። ወንጌል ብርሃንና ለመጻኢው ሰብአዊ ጥያቄ መፍትሄ የሆነው መከተል ያለበት እውነተኛውን መንገድ ለመለየት የሚያበቃ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.