2012-04-20 14:07:29

የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር መልእክት


በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለሚገኙት የተለያዩ የመናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና የገዳማት አለቆች፣ ከኩላዊት ቤተ ክርስትያን የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር እነዚህ ማኅበራት በሥርወ እምነት መሠረት የጸና ኅዳሴ እንዲያረጋግጡ የሚል ዓላማ ያደረገ መልእክት መተላለፉ ሲገለጥ፣ መልእክቱ RealAudioMP3 ትላትና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚገኙት የተለያዩ የመናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና ገዳማት የበላይ አለቆች እዚህ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ሕንፃ ከዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተና የበላይ ተጠሪዎች ጋር በተካሄደው ግኑኝነት ዋና ርእሰ ጉዳይ እንደነበርም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያስተላለፈው መልእክት የደናግል መናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና ገዳማት አለቆች የሚያቅፈው ምክር ቤት የሚያከናውናቸው እንቅስቃሴ፣ በሥርወ እምነት ሥር በመገምገም “ቤተ ክርስትያናዊ ሱታፌ” ለማጎልበት ታልሞ የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚገኙት የደናግል መናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና የገዳማት አለቆች የሚያቅፈው ምክር ቤት እንቅስቃሴው እ.ኤ.አ. እስከ 2008 ዓ.ም. በሥርወ እምነት ሥር ሂደቱን በመገምገም የተጠናቀረ መሆኑ የዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዊሊያም ለቫዳ ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ይህ ከትላትና በስትያን ይፋ የሆነው ሰነድ፣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚገኙት የደናግል ማኅበራት አለቆች የሚያቅፈው ምክር ቤት፣ ታጋሽ እና የተባባሪነት መልካም ፈቃድ መንፈስ የተካነ ብሎም የሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችና ጅማሬዎች በካቶሊክ ሥርወ እምነት ላይ የጸና መሠረት እንዲኖረው የሚያደርግ ኅዳሴ እንዲያረጋግጡ ለመደገፍና ለማበረታታት መሆኑ ብፁዕነታቸው ከገለጡ በኋላ፣ ሰነዱን ማእከል በማድረግ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለሚገኙት የተለያዩ የመናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና የገዳማት አለቆች የሚያቀፈው ምክር ቤትና በካቶሊክ የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር መካከል የተካሄደው ግኑንኘት የእያንዳንዱ የተቀበለው የተልእኮ ኃላፊነት ጥሪ የሚያከብር መተባበር የሚያነቃቃና ሰነዱ ለማስተላለፉ ከተፈለገው ይዞታ ውጭ ሌላ አሻሚ ትርጉም እንዳይሰጠውና አለ መግባባት እንዳያስከትል ተስፋ በማድረግ የተከናወነ መሆኑ ገልጠዋል።
የካቶሊክ ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር የደናግል ማኅበራት አለቆች የሚያቅፈው ምክር ቤትና እንዲሁም የእያንዳንዱ የመናንያን መንፈሳዊ ማኅበርና የገዳም አባል እምነት ለመቆጣጠር ሳይሆን፣ ነገር ግን ብዙ የመናንያን ማኅበራትና ገዳማት የሚነካ ከፍተኛ የሥርወ እምነት ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች በመከሰታቸው ምክንያት፣ የበተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለሚገኙት የተለያዩ የመናንያን መንፈሳዊ ማኅበራትና የገዳማት አለቆች የሚያቅፈው ምክር ቤት የሥርወ እምነት ተከትሎው ምን እንደሚመስል የሚገመግም ሰነድ መሆኑ የሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያሰራጨው መግለጫ ጠቁሞ፣ በተለይ ደግሞ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት ትምህርት የማይታዘዝና ከዚህ ትምህርት ጋር የማይስማማ ሴቶች ለክህነት ምሥጢር የሚል፣ የሶዶማዊ ጾታዊ ስሜት ላላቸው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚሉት ጽንፈኛው የሴቶች ቡድኖች የሚያሰራጩት አመለካከት ለማረጋገጥ ለተቀሰቀሱት ጥያቄዎች መልስ መሆኑ ተምልክተዋል።
በእያንዳንዱ አገር ያለው የመናንያን ማኅበራት እና የገዳማት አለቆች የሚያቅፉ ማኅበሮች በቅድስት መንበር እና በመናንያን ማኅበራትና ገዳማት ጠቅላይ አለቆችና ከእያንዳንዱ አገር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር ያለው ትብብር መግለጫ መሆን ስላለባቸው፣ በቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት የተካነ ጽኑ ኅዳሴ እንዲኖራቸው ወሳኝ መሆኑ የካቶሊክ ሥርወ እምነት ቅዱስ ማኅበር መግለጫ በማሳሰብ፣ በዚህ ምክንያትም የመናንያን ደናግል ማኅበር አለቆች ምክር ቤት ዘንድ የሲያትል ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፐተር ሳርታይን የቅድስት መንበር ወኪል እንዲሆኑ በመሾም፣ ምክር ቤቱ በሥረው እምነት ላይ የጸናው መሠረታዊ ህዳሴውና ሂደቱንም የሚከታተሉ የምክር ቤቱ እንቅስቃሴ የሚገመግሙና ካስፈለገም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይችላሉ የሚል፣ ከሥርወ እምነት ተንከባካቤው ቅዱስ ማኅበር የተሰጠው ሰነድ ገቢራዊነቱ የሚመሩና የሚከታተሉ፣ ግመገምውንም ለካቶሊክ ሥርወ እምነት ቅዱስ ማኅበርና ለመናንያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ጉዳይ የሚከታተል ቅዱስ ማኅበር የማስተላለፍ ሓዋርያዊ ኃላፊነት በማልበስ ከቅድስት መንበር መሾማቸው የካቶሊክ ሥርወ እምነት ተንከባካቢ መግለጫ ያመለክታል። በዚህ መልኩም በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የመናንያንና የገዳማውያን ሕይወት ፍርያማነት እንዲኖረው የሚያደረግ እንደሚሆንም ብፁዕ ካርዲናል ለቫዳ የሰጡት መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.