2012-04-06 12:20:48

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (05042012)።


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ በዛሬው ዕለት ጉባኤ የደስታው ስሜት ገና በአእምሮየ ሕያው ሆኖ ስለሚገኘው በቅርቡ በመክሲኮ እና በክዩባ ስላደረግሁት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንመለከታለን፣ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሐዋርያዊ ዑደቶች ማይረሳ ትውስት ባላቸው በእነዚህ አገሮች ለመጀመርያ ግዜ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ያስቻለኝ እግዚአብሔር በአሳቢነቱ ነው፣ ለዚህም ከልቤ ለእግዚአብሔር ግብታዊ ምስጋና እየመነጨ ነው፣ የጉብኝቱ ምክንያት የመክሲኮ እና የብዙ ደቡብ አመሪካ ሃገሮች 200ኛ የነጻነት በዓል እና በቅድስት መንበርና በመክሲኮ መካከል ዲፕሎማስያዊ ግኑኝነት ከጀመረ 20 ዓመት ማክበሩ፡ በክዩባ ደግሞ የፍቅር ድንግል ማርያም ዘኮብረ ምስል መገኘት 400ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንደ መንፈሳዊ ነጋዲ ለመሳተፍ ዕድል የፈጠረልኝ አጋጣሚዎች ነበሩ፣ በዚሁ ሐዋርያዊ ጉብኝት መላው የአህጉሩ ሕዝብ አብረው በተስፋ እንዲኖሩና፡ ለበለጠ መጻኢ ሕይወት ተግተው እንዲሠሩ በማሳሰብ በሃሳቤ መላውን አህጉር በልቤ አኖርኩት፣ ለመክሲኮና ለክዩባ ርእሰ ብሔሮች እና ሌሎች ባለሥልጣኖች በክብርና በትሕትና ስላቀረቡልኝ የእንኳን ደህና መጡ መግለጫ አመሰግናችዋለሁ፣ የልዮን፡ የሳንትያጎ ደ ኩባ፡ እና የሃቫና ሊቃነ ጳጳሳት ከተባባሪዎቻችው እንዲሁም ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ስኬታም እንዲሆን በልግስና ላበረከቱ ሁሉ በልብ አመሰግናለሁ፣ ያሳላፈክዋቸው ቀኖች የማይረሳ ደስታና ተስፋ የሞላቸው ቀኖች ነበሩ፡ በልቤ ታትመው ይኖራሉ፣
የመጀመርያ ምዕራፌ፡ የመክሲኮ ጂኦግራፊካዊ ማእከል በሆነች በጉዋናኽዋቶ ግዛት የምትገኝ የልዮን ከተማ ነበረች፣ በዚህ ከተማ ጠቅላላውን የመክሲኮ ሕዝብ በመወከል ብዙ ሰዎች እጅግ ደስ የሚያሰኝ ልዩና የሞቀ አቀባበል አደረጉልኛ፣ ከእንኳን ደህና መጡ ሥርዓት እስከ የጉብኝቱ ፍጻሜ፡ የካህናቱ የመንኮሳቱና የምእመናኑ እምነትና ብርታት አየሁ፣ ብዙ ተቅዋማት፡ ጳጳሳት እና የኅብረተሰቡ ተወካዮች በተገኙባቸው ስብሰባዎች የእምነት ነጻነት ምንጭ የሆኑ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችን ማወቅና መንከባከብ የግድ መሆኑን አሳሰብኩ፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ኑሮ ቍስሎች ማለትም በጥንታዊና አዳዲስ ግጭቶች፡ በሙስና እና በዓመጽ ለሚሰቃዩት ቅርበቴን ገለጥሁ፣ መጨረሻ ያልነበረው የሰዎች ሰልፍ በሄድኩባቸው መንገዶች በታላቅ ደስታ የሸኙን ትእይንት ሁሌ በሃሳቤ አስታውሰዋለሁ፣ በሰልፉ ይታዩ የነበሩ ሰላምና ፍቅር ለመግለጥ ይወዛወዙ የነበሩ እጆች፡ በደስታ የፈኩ ፊቶች፡ የደስታ ጩኸት፡ የመክሲኮ ክርስትያኖች ጽኑ ተስፋን በልቤ አኖረ፣ በተለያዩ ንግግሮቼ በተለይ የዓመጽ ሰለባ ለሆኑ ወግኖች ሳነጋግርና ሳጽናና ያወገዝክዋቸው ዓመጾች ውስጥ ሳሉም ይህ ተስፋ በመክሲካውያን ልብ በርቶ ኖሮዋል፣ መክሲኮ በደረስኩበት ቀን የአገርዋና የቤተ ክርስትያን ፍሬ የሆኑ ብዙ ሕጻናት እና ወጣቶች አገኘሁ፣ በተለያዩ ዜማዎችና ሙዚቃ የተሸኘው የማይጨርሽ ደስታቸው፡ በደስታ የፈካ ፊቶቻቸውና የእጅ ውዝዋዜአቸው የመላዋ መክሲኮ፡ ደቡብ አመሪካና ካሪብያን ወጣቶች ታላቅ ፍላጎት፡ በሰላም በጸጥታ እና በውኅደት ፍትሕ በሞላበትና በታረቀች ማኅበረሰብ መገንባት መሆኑ ይገለጣሉ፣
የጌታ ሐዋርያት፡ ክርስትያንና የቤተ ክርስትያኑ አባል የመሆን ደስታን ማሳደግ አለባቸው፣ ከዚህ ደስታ ክርስቶስን በችግርና ሥቃይ ግዜም ይሁን የማገልገል ኃይል ይወደልዳል፣ ይህንን እውነት ባለፈው ሰንበት በልዮን 200ኛ ዓመት ፓርክ ላይ ለተሰበሰቡ እልፈ አእላፋት ሕዝብ ለመሥዋተ ቅዳሴ ተሳታፊዎች ገለጥኩት፣ ለሁሉም እጅግ አስቸጋሪና የጨለሙ ሁኔታዎች ከውስጥ ወይንም ከልብ ሊለውጥ በሚችለው በሁሉ ቻይ እግዚአብሔር በጎነት እንዲተማመመኑ ተማጠንኩዋቸው፣ የመክሲኮ ሕዝብ ባላቸው ኃያል እምነትና በወንጌል ተማምኖ በመታዘዝ ለጌታ መልሰዋል፣ በዚሁ ክፍለዓለም ለአህጉሩ የሚሆን አጽናኝ የተስፋ ምልክቶች ለማየት ቻልኩኝ፣ በመክሲኮ ሐዋርያዊ ጉዞ በመጨረሻ ያደረግሁት ጉብኝት በልዮን የእመቤታችን እመብርሃን ካተድራል ላይ፡ ከመክሲኮ ጳጳሳትና የአመሪካ ጳጳሳት ተወካዮች ጋር ያሳረግነው የጸሎተ ሰርክ ማኅሌት ነው፣ ጳጳሳቱን፡ ቀናእተኞች እረኞች፡ እርግጠኞች መሪዎች፡ ሆነው ከቤተ ክርስትያን ትምህርት ጋር ቅን ውህደትና ልባዊ መታዘዝ እንዲቀሰቅሱ አበራታትኋቸው፣ ለክርስቶስ ተወካይ ያላቸውን አክብሮትና ፍቅር አጣጥሜ ፍቁር የመክሲኮ ምድርን ትቼ ከመሄዴ በፊት በመክሲኮ ሕዝብ ክርስትያናዊ ባህል በተመሠረቱት ልማዶቻቸው እንደወትሮው ለጌታና ለቤተ ክርስትያን ታማኝ ሆነው እንዲኖሩ አደራ አልክዋቸው፣
ቀጣዩ ቀን የሐዋርያዊ ጉዞየ ሁለተኛ ክፍል፡ በⷍዩባ ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሃይማኖት መፈሳዊና ትምህርታዊ አገልግሎት መስጠት ስላለበት፡ የክዩባ ቤተ ክርስትያን በብዙ ችግሮች ሥር ሆና ካለ በቂ መሣርያ ወንጌልን በደስታ ለመስበክ በሙሉ ኃይልዋ እየሰራች ነው፡ ይህንን የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ተልእኮን ለመደገፍ ያለመ ጉብኝትን ለማከናወን ⷍዩባ በመድረስ ጀመረ፣ የደሴቲቱ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው በሳንትያጎ ደ ኩባ በደረስኩ ግዜ በቅድስት መንበርና በክዩባ መንግሥት ያለውን መልካም ግኑኝነትና የአገሪቱ ቤተ ክርስትያን አገልግሎት ለማበርከት ሕያውና ገንቢ በሆነ መንገድ በማኅበረ ሰቡ መገኘትዋን ሳልክድ እላይ የገለጥኩትን ሃሳብ አሰመርኩበት፣ ር.ሊ.ጳ ጠቅላላው የክዩባ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ነጻነታቸው የተወሰነ በመሆኑ የሚሰቃዩ ሰዎች ጭንቀቶችና ፍላጎቶችን ሁሉ በልቡ ይዟል ብየ ቅርበትየን አረጋገጥኩላቸው፣
በክዩባ መሬት የመጀመርያ መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ ደስታ ያገኘሁበት የክዩባ ጠባቂ የሆነች የፍቅር ድንግል ዘኮብረ ምስል የተገኘበት 400ኛ ዓመት ለማክበር በተደረገው አጋጣሚ ነው፣ ቀላል ካልሆነ ሁኔታ የመጣች ቤተ ክርስትያን ነገር ግን በሕያው ፍቅርና በአካል የሕዝቡን ሕይወት በመሳተፍ ላይ ያለች ቤተ ክርስትያን ምልክት የሆኑ፡ ኃያልና የጦፈ መንፈሳውነት፡ የአእላፍ ሕዝቦች በልዩ ትኩረትና ጸሎት ሱታፌ የታየበት ሁኔታ ነበር፣ መጻኢ ሕይወታቸው የበለጠ እንዲሆን በተስፋ ለሚጠባበቁ የክዩባ ካቶሊካውያን ምእመናንና ለመላው የክዩባ ሕዝብ ለእምነታቸው አዲስ ኃይል አልብሰው፡ በምሕረትና ርኅራኄ ብርታት፡ ክፍትና የታደሰ ለእግዚአብሔር ሰፊ ቦታ የሚሰጥ ኅብረተሰብ ለማነጽ አበርክቶ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረብኩላቸው፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከሕይወታችን ያወጣን እንደሆነ ዓለም ሰው ሊኖረው የማይቻል ይሆናልና፣ ሳንትያጎ ደ ኩባን ከመልቀቄ በፊት በክዩባ ሕዝብ እጅግ ተወዳች በሆነችው በፍቅር ድንግል ዘኮብረ እመቤታችን ቤተ ጸሎት ተሳለምኩ፣ የዚሁ የእመቤታችን የፍቅር ድንግል ዘኮብረ ምስል በደሴቲቱ ቤተ ሰቦች ባደረገው ዑደት የአዲስ ስብከተ ወንጌል እና የእምነት እንደገና የማግኘት አጋጣሚ ትርጉም በማቅረብ ለቤተ ሰቦቹ ብዙ መንፈሳዊ መልካም ፍላጎት ፈጥረዋል፡፡ ለሁሉም የⷍዩባ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ለሚሰቃዩና ወጣቶችን ለቅድስት ድንግል ማርያም አማጠንክዋቸው፣
የⷍዩባ ሁለተኛ ምዕራፍ በደሴቲቱ ዋና ከተማ በሃቫና ነበር፣ በዚሁ አጋጣሚ እስከ የእኔ እንደራሴ መኖርያ ቤት በተደረገው ጉዞ ለቀረበው እጅግ አስደናቂ አቀበባል በተለይ ወጣቶች የፍጻሜው ዋናዎች ነበሩ፣ በዚሁ ቦታ ከአገሪቱ ጳጳሳት ጋር ተገናኝቼ የⷍዩባ ቤተ ክርስትያንን ስለሚያጋጥሙ ፍልምያዎች እና ሕዝቡ ይህንን ሁሉ አውቆ ቤተ ክርስትያንን በታላቅ መተማመን እየተመለከተ ስላለው ሁኔታ ተወያይተናል፣ ተከታዩን ቀን በሕዝብ ተሰግስጎ በነበረው በዋናው የሃቫና አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳረግኩ፣ ⷍዩባና መላው ዓለም ለውጦች እንደሚያስፈልጋቸው ሆኖም ግን እነኚህ ለውጦች እውን የሚሆኑት እያንዳንዳችን ስለ ሰው ልጅ ያለውን እውነት ለመቀበል ክፍት ስንሆንና ወደ ነጻነት ለመድረስ የተዘጋጅን በመሆን በአከባቢያችን የዕርቅና የወንድማማችነት ዘር ለመሥራት በመወሰን የገዛ ራስን ሕይወት በኢየሱስ ክርስቶስ በመምሥረት ምክንያቱም ክፋትንና የሚጮቅነን ሁሉን ለማሸነፍ እየረዳን የስሕተት ጨለማን ሊያውገደው የሚችል እርሱ ብቻ መሆኑን ለሁላቸው አሳሰብክዋቸው፣ አያይዤም ቤተ ክርስትያን ክብር እንደማትጠይቅ ነገር ግን የተስፋን የሰላም ወንጌል መልእክት በሁሉም የኅብረተሰብ አከባቢ ለማዳረስ እምነትዋን በይፋ ለማወጅና ሥርዓተ አምልኮን በማኅበር ለመፈጸም ነጻ እንድትሆን ትጠይቃለች፣ እነኚህን በተመለከተ የⷍዩባ መንሥት ባለሥልጣናት ላደረጉልን መልካም ነገር እመስግኜ ገና እስከ ሙሉ ነጻነት በዚህ ጐዳና እንዲገሰግሱ አሰመርኩበት፣
ከⷍዩባ ለመሄድ ስነሳ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ የⷍዩባ ሕዝብ ብርቱ ዝናም ቢኖርም ሰላምታቸውን ለማቅረብ በመገድ ተሰልፈው ሸኙኝ፣ በስንብት ንግግሬ ለአገሪቱ በጎ ነገር የተለያዩ የⷍዩባ ኅብረተሰብ አባሎች ቅን መተባበርና ትዕግሥት የተሞላበት ውይይት ለማካሄድ አሁኑኑ ይጠራሉ በማለት አሳሰብኋቸው፣ በዚህ አመለካከት እንደ ክርስቶስ ምስክር የእኔ በⷉዩባ ደሴት መገኘት የልቦቻቸውን በሮች የተስፋ ምንጭና መልካም ነገር ለማሳደግ ኃይል ለሚሆነው ለክርስቶስ መበራታቻ ሆነዋል፣ ስለዚህም ⷍዩባውያንን የአባቶቻቸው እምነት እንደገና እንዲኖሩና የተሻለ መጻኢ እንዲገነቡ ተማጠንክዋቸው፣
እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰውና፡ ይህ የመክሲኮና የⷍዩባ ሐዋርያዊ ጉዞ የተፈለገውን የግብረ ተልእኮ ዓላማ አሳካ፣ የመክሲኮና የⷍዩባ ሕዝብ በቤተ ክርስትያን ኅብረትና በወንጌል ብርታት የሰላምና የወንድማማችነት መጻኢ እንዲገነቡ ከዚህ ፍጻሜ አመርቂ ፍሬ እንዲሰብስቡ ይሁን፣
ውዶቼ፤ ነገ ሓሙስ ማታ የጌታ እራት የምናስታውስበት ቅዳሴ በማሳረግ የክርስቶስ ሕማማት ሞትና ትንሣኤ የሆነውን የእምነት ምሥጢራችን ለመግለጥ፡ የሥርዓተ አምልኮአችን አንኳር የሆነው የፋሲካ ጸሎተ ሳልስት እንጀምራለን፣ በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ይህ የኢየሱስ ተልእኮ የሚፈጸምበት ወቅት የእርሱ ሰዓት መድረሱ በመጨረሻ እራት ትጀምራለች፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ እንዲህ በማለት መግቢያ ያደርግላታል፡ “ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው” (13፡1) ጠቅላላው የኢየሱስ ሕይወት ወደዚች ሰዓት የሚያመራ ነበር፣ ይህች ሰዓት እርስ በእርሳቸው በሚገላለጡ ሁለት ጠባዮች ተመልክታለች፡ ሰዓቱ ደረሰ ሲል የማለፉን ሲገልጥ ሁለተኛ ደግሞ የፍቅር ሰዓት ያመለከክታል እስከ መጨረሻ ወደዳቸው እንደማለት፣ እንደእውነቱም ይህ መለኮታዊ ፍቅር ኢየሱስን የሞላው መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ኢየሱስን የክፋትና የሞት ሸሎቆን ተሻግሮ ወደ አዲስ ቦታ የትንሣኤ ቦታ ያሻግረዋል፣ ይህንን ሁሉ የሚያደርግ ደግሞ ፍቅር ነው፣ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ኢየሱስ በኃጢአት የተደነገጉት ሰብአዊ ሁኔታዎች ጥሶ የተወሰነ የመሆን ድንበሮችን ይሻገራል፡ የሰው ልጅን ከእግዚአብሔርና ከዘለዓለማዊ ሕይወት እስረኛ በማድረግ የለያየውን መከላከያ ተሻግሮታል፣ በፋሲካ ጸሎተ ሳልስት የሥርዓተ አምልኮ አፈጻጸም በእምነት በመሳተፍ ይህንን የፍቅር መሸጋገር ለመጣጣም የተጠራን ነን፣ እያንዳንዳችን በኢየሱስ እስከ መጨረሻ የተወደድን ነን፡ ሕይወቱ በመስቀል ላይ ሰቕሎ ገዛ ራሱን በሙላት ሰጠን ለዚህም ነው በመስቀል ላይ ሲሞት “ተፈጸመ” (ዮሐ 19:30) ያለው፣ ምሥጢረ ትንሣኤ በእኛ ላይ እውን እንዲሆን ዘንድ፡ ይህ ፍቅር እንዲነካን ይሁን፡ ይህ ፍቅር እንዲለውጠን ይሁን፣ እያንዳንዳችሁ ይህንን የፋሲካ ጸሎተ ሳልስት ጥልቅ በሆነ መንፈሳውነት እንድትጠቀሙበት እማጠናለሁ፡ ለሁላችሁም መልካም ቅድስት ፋሲካ እመኝላችኋለሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.