2012-04-06 15:38:21

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ብቻ ነው ቤተ ክርስትያንን በእውነት ለማደስ የሚቻለው


የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ወደ በዓለ ትንሣሴ ዘእግዚእነ የሚያሸጋግረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰሙነ ሕማማት እየተከበረ ሲሆን፣ ትላትና በተከበረው ጸሎተ ሐሙስ RealAudioMP3 አማካኝነትም የጸሎተ ሳልስት ሊጡርጊያ በይፋ ተጀምረዋል።
ጸሎተ ሐሙስ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የቅብአ ቅዱስ ሥርዓት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚፈጸምበት ዕለት ሲሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ቁርባን እና ምሥጢረ ክህነት ቅዋሜ በማረጋገጥ ለደቀ መዛሙርቱ “እርስ በእርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ” (ዮሐ. 13፣ 34)። በማለት አዲስ ትእዛዝ የሰጠበትና የሚኖር ሥርዓተ ሊጡርጊያ የሚፈጸምበተ ዕለት ሲሆን። በዚህ የቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ ማረጋገጫ የሆነው የጌታ የመጨረሻ እራት ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ጌታችን ለአርድእቱ የፈጸመው ሥርዓተ ሕጽበተ እግር ምልክት በተለየ በተራ ምሳሌ የሚፈጸምበት ዕለት ምክንያት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእውነተኛው ተሃድሶ ኃይል የሚል ሃሳብ ማእከል በማድረግ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በጸሎተ ሓሙስ የቅብአ ቅዱስ ሥርዓት ፈጽመው ባሰሙት ስብከት ካኃን ግላዊው ርእሰ ክንዋኔ በመካድ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመዋሃድ የተጠራ መሆኑ በማሳሰብ፣ ምእመናን በተለይ ደግሞ የእምነተ ዓመት ጸጋ አማካኝነት በማኅበርሰባችን የሚይታየው ሃይማኖታዊ መሃይማነት እንዲዋጉ አበረታተዋል።
እንዲሁም ከቀትር በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ዘ ላተራኖ ጳጳሳዊ ባሲሊካ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጌታ እራት ሥርዓተ ሊጡርጊያ እርሱም የቅዱስ ቁርባን ቅዋሜ ሥርዓተ ሊጡርጊያ እንደፈጸሙ የቅዱስ መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ቅዱስነታቸው ጧት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ የቅብአ ቅዱስ ሥርዓተ ሊጡርጊያ ፈጽመው ባሰሙት ስብከት፣ ካህን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሱታፌ ያለው እና ከእግዚኣብሔር የሚጀምር ተግባር የሚያከናውን መሆን አለበት። በምሥጢረ ክህነት አማካኝነት ለእግዚኣብሔር የተለየው ካህን፣ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የጠለቀ ግኑኝነት ያለው፣ ክርስቶስን በጥልቀት ለመምሰል የተጠራ መሆኑ በመገንዘብ፣ በዚህ ክርስቶስ ተመስሎ በሚኖር ሕይወት አማካኝነትም የግል ምኞት እና ጉጉት ሁሉ በመካድ (በፈቃዱ በመተው) አዛዥ ሳይሆን አገልጋይ ሆኖ መኖር አለበት። ይህ ጥሪ ከክርስቶስ ጋር ጥልቅ መተሳሰር የሚጠይቅ እንዳውም እርሱን መምሰል ከእርሱ ጋር መወሃድ የሚል ከገዛ እርስ በልጦ ብዙውን ጊዜ ከሚሰበከው ገዛ እርስን ማረጋገጥ ከሚባለውን አነጋገር እና ተግባር ርቆ የእኔ የሚለውን ሁሉ የሚክድ ገዛ ሕይወትን ለገዛ እራስ ምርጫ መጠቀሚያ ሳይሆን ለክርስቶስ የሚያቀርብ ነው።
ያንን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሠራው ምሥጢረ ክህነት በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን በሚጋረጥዋት ፈተናዎች ምክንያት ለአደጋ ሲጋለጥ ይታያልን፣ ለዚህ እንደ አብነትም በቅርቡ በአንዳንድ ጥቂት የኤወሮጳ አገሮች ካህናት የክህነት ምሥጢር ለሴቶች እንዲፈቀድ ያቀረቡት የጥያቄ ጥሪ “ተአዝዞን የሚጻረር” የቤተ ክስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት የሚያገል መሆኑ ቅዱስነታቸው በመግለጥ፣ አለ መታዘዝ መንገድ ሊሆን ይችላልን? በመታዘዝ እንጂ ባለ መታዘዝ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን ተሃድሶ አይረጋገጥም። ስለዚህ ቤተ ክርስያን በእኛ ፍላጎት እና አስተሳሰብ አማካኝነት መለወጥ ሳይሆን፣ ለቤተ ክርስያን በመታዘዝ ብቻ ነው ቤተ ክርስትያንን በእውነት ለማደስ የሚቻለው ብለዋል።
ቤተ ክርስትያን ለወቅታዊው ሁኔታ የበቃች ሆና እንድትገኝ የማያግዙዋት ጉዳዮች አሉ፣ እውነት ነው ክርስቶስ የእዚአብሔር ቃል እና ፈቃድ ለማፈን ሥጋት የሆነውን ሰብአዊ ባህል አድሰዋል፣ በማረምም አስተካክሎታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህ በማድረግ ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ፈቃድ መታዘዝ ዳግም አነቃቅተዋል። እጅግ ያተኮረበት እና በልቡም ያለው ጥልቅ ፍላጎት እውነተኛ ተአዝዞ የሚል የሰው ልጅ ርእሰ ብቸኛ ዳኝነቱን የሚጻረር ነው ብለዋል። ኢየሱስ ተልእኮውን በፍጹም ተአዝዞ እና እስከ መሰቀል ድረስ ገዛ እርሱን ዝቅ በሚይደርግ ትህትና አማካኝነት የተሰጠው የተልእኮ ጥሪ በመፈጸም፣ ለተልእኮው ታማኝ በመሆን የተልእኮው ታማኝነቱን አረጋግጠዋል። እየሱስ የአብ አንድ ልጅ ሕይወቱ የኔ ሳይሆን ያንተ ፈቃድ በማድረግ በኖረው ፍጹም ተአዛዞና ለአብ መታዘዝ የሚሰጠው ጸጋ ነው የገለጠው የኖረው። የእየሱስ ትህትናው ከመለኮታዊነቱ ጋር እውነተኛውን መንገድ ያመለክተናል።
ይኽንን መሠረት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ይላሉ፣ ካህናት የግላቸው ርእዮተ ዓለም እና አስተሳሰብ ሳይሆን ‘የቤተ ክርስትያን እምነት’ እንዲያበሥሩ የተጠሩ ናቸው። ብዙዎች ይኸንን አነጋገር ጸረ ለውጥ፣ ወግ አጥባቂነት የሚል ትችት ሲሰነዝሩበት ይታያል። ሆኖም ድኅረ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በቤተ ክርስትያን የተወለዱት የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎች የቤተ ክርስትያን ኅያውነት ንቁ ሕይወት ባለችበት ዘመን ተጨባጭ እና ንቁ ተሳታፊ የሚያደርጋጥ እውነተኛው አዳሽ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመስክረዋል። በተአዝዞ ላይ የጸናው እምነት ያለው ፍርያማነት የፍቅር እና የተስፋ ንቁ ኃይል መሠረት መሆኑ እየተመሰከረ ነው።
ቅዱሳት ተኃድሶ እንዴት እንደሚረጋገጥ እና እንደሚሠራ ለዚህ ሕይወት እንዴት ልንታዘዘውም እንደሚገባን በቃል እና በሕይወት እግዚአብሔር በቁጥር ብዛትና በጊዚያዊ እርካታ ሳይሆን በተናንሽ እና ትሁታን በሆኑት ተግባሮች አማካኝት እንደዚያች ከሁሉም ያነሰች የሰናፍጭ ዘር ነገር ግን ከሁሉም አትክልቶች በልጣ የምተገኘውን በማስታወስ በትህትና እና እራስ ዝቅ በማድረግ የሚረጋገጠው የላቀው ድል ያረጋግጥሉናል ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ቀጠለውም እምነታችንን ሃይማኖታችንን ለመኖር እና እግዚአብሔርን ለማፍቀር ማለትም በትክክል እና በተገባ እርሱን ማዳመጥ የበቁ ለመሆን እርሱ እንደሚለውም ልባችን እና አእምሮአችን በቃሉ የተነካ መሆን እንዳለበት ገልጠው፣ በዓለማችን የሚታየው የሃይማኖታዊ መኃይምነት በመጥቀስ፣ ሃይማኖታዊው መሃይምነት ልባም ተመስሎ በመስፋፋት ላይ ነው። የእምነት ዓመት እምነታችንን በአዲስ ቀናተኛ መንፈስ እና በአዲስ ኃሴት አማካኝነት እንድንኖረው እና እንድንመሰክረው የሚያነቃቃን ቅዱስ አጋጣሚ ነው። ስለ ነፍስ መናገር የሚጠላ እንዳውም ማስታወስንም ፈጽሞ እንዳይቻል የሚያደርግ ነፍስን የሚክድ ባህል በመስፋፋት ላይ ቢሆም ቅሉ፣ ይኽንን በሥጋ እና አካል ብቃት ላይ ያተኮረውን ባህል፣ የሰው ልጅ ሙሉ ድህነት ላይ በማተኮር ብቃት ተአለውጦ እንዲኖረው ማድረግ ይገባናል፣ ስለዚህ ካህናት የአገልግሎት ጥሪያቸው ተራ ሥራ አድርገው ከመኖር ፈተና ተቆጥበው ተልእኮ መሆኑ እንዲመሰክሩ አደራ በማለት፣ ካህን ሕይወቱ የገዛ እራሱ ሳይሆን የጌታ በመሆን ለሌሎች እርሱ በሚሰጠው የወንጌል ታማኝነትን የሚያበክር ከእውነተኛው ቀናተኛ መንፈስ የመነጨ ምስክርነት የሚያቀርብ የአገልግሎት ሕይወት መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል በማለት ያሰሙት ስብከት አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.