2012-04-02 15:18:44

የቅድስት መንበር እርካታ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ተጀምሮ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በተጠናቀቀው መክሲኮን እና ኩባን ያጠቃለለው 23ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማካሄዳቸው የሚዘከር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 26 ቀን እስከ መጋቢት 29 ቀን በኩባ RealAudioMP3 ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ከአገሪቱ ርእሰ ብሔር ራውል ካትሮ ጋር በመገናኘት የኩባ ምእመናን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣሴ በሚገባ ለመዘጋጀት እንዲችሉ ዓርብ ሥቅለት እንደ ተራ ቀን ሳይሆን እንደ በዓል ቀን ታስቦ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ እንዲዘከር በማለት ላቀረቡት ጥያቄ፣ የአገሪቱ መንግሥት ሳይውል ሳያድር አወንታዊ ምልስሽ በመስጠቱ ምክንያት ቅድስት መንበር እጅግ ደስ መሰኘትዋ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል አክለውም ይኽ ውሳኔ ሕዝቡ ለበዓለ ትንሣኤ በበለጠ እንዲዘጋጅ የሚያበረታታ ውሳኔ መሆኑ አብራርተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የዛሬ 14 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ1998 ዓ.ም. በኩባ ሐዋርያዊ ጉብኝት ከማካሄዳቸው ቀደም በማድረግ በወቅቱ የኩባ ርእሰ ብሔር ፊደል ካስትሮ ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ክብር በላቲን ሥርዓት የሚከበረው በዓለ ልደት ታህሳስ 25 ቀን ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር በሰጡት ውሳኔ መሠረት በኵባ እ.ኤ.አ. ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ብሔራዊ በዓል ሆኖ መከበሩን እንደ ጀመረና የአገሪቱ መንግሥት የፊደል ካስትሮ ውሳኔ በመከተልም ከዚያ ዓመት ወዲህ በአገሪቱ በዓለ ልደት በየዓመቱ ብሔራዊ በዓል ሆኖ መከበር እንደ ጀመረ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.