2012-04-02 15:21:34

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሪዮ ደ ጃነይሮ፣ ለብራዚል እና ለዓለም አቢይ ጸጋ ነው


እ.ኤ.አ. መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከተለያዩ 98 አገሮች የተወጣጡ 300 የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ ተጠሪዎች ያሳተፈው የዓለማውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ስብሰባ፣ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ RealAudioMP3 ሮማ አቅራቢያ በሚገኘው ሮካ ዲ ፓፓ ከተማ በተካሄደው ጉባኤ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት የዓለማውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ክለመንስ “ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ብዙ ወጣቶች ሌሎች ወጣቶች በእምነት የሚማርኩና የእምነት ታማኝነቱን የሚመሰክሩ መሆናቸው ያረጋግጥልናል’ እንዳሉ ሲገለጥ፣ ይህ ስብሰባ በማድሪድ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በአገረ ስፐይና በቤተ ክርስትያን ያሳደረው አወንታዊ አስተዋጽኦ ለይቶ በማስተንተን ጀምሮ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ከተማ ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ገጽታ ላይ በማተኮር ሰፊ እና ጥልቅ ውይይት መካሄዱ ስለ ስብሰባው አስመልከተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የዓለማውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒዝላው ርይልኮ ገልጠው፣ በዚህ ለእግዚአብሔር ጀርባየ የሚለው ባህል እየተስፋፋ ባለበት፣ ጥልቅ የእምነት መሸርሸር ለሚታይበት ዓለም ለማረም እና የተገባ መልስ ለመስጠት ያነቃቃቸው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጥሎት ያለፈው ገጠመኝ የሰጠው አስተዋጽኦ በመለየት የቅርቡ ትውስት የሆነው ሁለት ሚሊዮን ወጣቶችን ያሰባሰበው በማድሪድ ቆላስያስ ምዕራፍ 2 ቁ. 7 “በእርሱ ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ በተማራችሁት መሠረት በእምነታችሁ ጸንታችሁ ኑሩ፣ በብዙ አመስግኑ”። በሚል ቃል ተመርቶ የተካሄደው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጠቅሰው የላቀው የእምነት ምስክርነት በቃል እና በተግባር የተረጋገጠበት ነበር ሲሉ፣ የሪዮ ደ ጃነይሮ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኦራኒ ዥዋው ተምፐስታ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሪዮ ደ ጃነይሮ ይኸንን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንድታስተናግድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ውሳኔ ደስታና ኃላፊነትም ነው ካሉ በኋላ፣ ለብራዚልና ለዓለምም አቢይ ቡራኬ ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የእግዚአብሔር ጊዜ ለወጣቶች እና ለቤተ ክርስትያን ነው። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በተካሄደባቸው አገሮች የታየው በእምነት መታደስ የወጣቶች ወደ እግዚአብሔር በበለጠ መቅረብ፣ መለወጥ የታየው ጸጋ በብራዚል እንደሚታይ አልጠራጠርም፣ ስለዚህ ወጣቱ ትውልድ የበለጠው ዓለም ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት የሚሰጠው አስተዋጽኦ የሚያጎለብት መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ገጠመኝ የሚረጋገጥበት ይሆናል ብለዋል።
እጆቹን ዘርግቶ የሚቀበለው ክርስቶስ በመከተል ሪዮ ደ ጃነይሮ እጆቸዋን ዘርግታ በዚያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊዎች ለማስተናገድ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነች ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.