2012-04-02 15:16:56

በዓለ ሆሳዕና እና ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


ቅድስት ቤተ ክርስትያን በላቲን ሥርዓት መሠረት ትላንትና በበዓለ ሆሳዕና በማክበር ወደ በዓለ ትንሣሴ የሚያሸጋግረው ቅዱስ ሳምንት በይፋ የጀመረች መሆንዋ ሲታወቅ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በበዓሉ ምክንያት በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ተኩል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ RealAudioMP3 መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስክበት፣ ይኽ ዕለት ኢየሱስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት የሚከበርበት ሲሆን፣ የዚህ በዓል ምልክት የሆነውን የዘንባባና የወይራ ቅርንጫፍ በመባረክ ዕለቱም 27ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሰበካዎች ደረጃ የሚከበርበተ ዕለት መሆኑም በማስታወስ፣ ይህ በሰበካ ደረጃ በሁሉም አገር በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት “የጌታ በመሆናችሁ ሁሉ ጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜም የምላችሁ ‘ደስ ይበላችሁ’ ነው” (ፊሊ. 4፤4) በሚለው ቃል የተመራ እንደነበርም ለማወቅ ተችለዋል።
በበዓሉ ምክንያት ሁሉንም ወጣቶች፣ በኢየሱስ የሚገኘው እውነተኛው ደስታ ጋር መገናኘታቸው፣ ይኸንን የእምነት ደስታ ለሁሉም እንዲመሰክሩ ቅዱስ አባታችን በማሳሰብ፣ በውስጣችን ያለውን እውነተኛው ደስታ ለሌሎች ለማካፈል ተጥርተናል፣ ብዙውን ጊዜ ክርስትና ነጻነትን የሚወስን የሚዘወተር ደንብ እንደሆነ ተደርጎ ሲቀርብ፣ አልፎ አልፎም ክርስትያናዊ ሕይወትም የደከመ እና የተሰላቸ ሕይወት የሚኖርበት ተመስሎ ይታያል፣ ወንጌል ‘እግዚአብሔር እንደሚያፈቅረን፣ እያንዳንችን ለእርሱ አስፈልጊዎች መሆናችን የሚያረጋግጥልን አዲስ ብሥራት ነው። ይኸንን የእምነት ደስታ እንመሰክረውም ዘንድ ተጠርተናል። ይኸንን ደስታ የሚኖር ደስታውን ለማበሠር የተጠራ ነው ብለዋል።
እውነተኛ ደስታ የሚዛመት ነው። እውነተኛው ክርስትና ቀቢጸ ተስፋና የተከዘ ሕይወት ሳይሆን ምንም’ኳ ዕለታዊ ሕይወት የተለያየ ችግር የሚጋረጥበት ቢሆንም ቅሉ በጽናት እና በታማኝነት የሚኖር ከሆነ በአፋጣኝ ባይሆንም የራሱ ጊዜ በመጠበቅ ወደ ደስታ የሚመራ ነው። ምክንያቱም እውነተኛው ፍቅር በሚያጋጥም ችግር የሚሰናከል ሳይሆን ጽናት ማለት መሆኑ በማብራራት፣ ስለዚህ ችግሩ ሁሉ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ እውነተኛ ደስታ ወደ ሚገኝበት ፍቅር ይለወጣል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያስታውቅ፣ ተስፋ የተደረገበት መሲሕ ጊዜው በደረሰ ጊዜ መጥቶ በሁሉም በደስታ እና በእልልታ የተባረከ መሆኑ ተመስክሮ ይኽ የተባረከው መላውን ሕዝብ ባርከዋል። የኢየሱስ እይታ ቡራኬ ነው። ይኽ ጥበበኛ እና እፍቃሪው እይታ እርፎበት የተባረከው ሰው ምንም’ኳ ፍጹም ባይሆንም በዓለም ዘንድ ያለውን ውበት በመለየት ለማስተናገድ ይበቃል፣ ስለዚህ ቀድሞ በሚያፈቅረው በእግዚአብሔር እይታ ሱታፌ የሚኖር ያንን የእግዚአብሔር እይታን ነው የሚያንጸባርቀው ብለዋል።
በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያለ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ በወደሰው ሰው ልብ ውስጥ ምን ይሆን ያለው? በዚህ በቅዱስ ሳምንት ንጉሣችን የሆነው አፋጣኝና ቀላል ባንዴ በምድራዊ ሕይወት የሚገኝ ደስታ ሳይሆን ያንን ሰማያዊው ደስታ በእግዚአብሔር መቀደስን የሚያረጋግጥልን መሢሕ እንከተል ዘንድ መጠራታችን ተበሥሮልናል፣ እንግዲ የምንጠባበቀው ምንድን ነው በማለት በዚህ ወደ በዓለ ትንሣኤ በሚያሸጋግረው ቅዱስ ሳምንት ለእያንዳንዱ ወጣት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመቀበል እና እስከ ፍጻሜ ድረስ እርሱን ለመከተል የእርሱን ፋሲካ ‘ሞቱ እና ትንሣኤው’ የሕይወቱ ትርጉም በማድረግ እውነተኛውን ደስታ በመኖር ለማካፈል መጠራቱ የሚያሳስብ ዕለት ነው ብለዋል።
ታዲያ ለዚህ ዓይነት አቢይ ጥሪ የተገባ መልስ ለመስጠት እርሱም ገዛ እራሳችንን ግዜአችንን ጸሎታችንን ስለእኛ ብሎ ከሚሰቃየው፣ ከሚሞተው እና ሞትን አሸንፎ ከሚነሣው ከኢየሱስ ጋር ያለን የፍቅር ሱታፌ እነሆኝ በማለት እንደ ስጦታ ማቅረብ ይገባናል። ለርእሱ በእርሱ ጸጋ መሠረትም የሚገባው ስጦታ እኛነታችን ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.