2012-03-30 14:17:28

የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት፦ “ቤተ ክርስትያንና የሕጋዊነት ባህል”


ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች መሠረት በአማኞች እና በኢአማኒያን መካከል የሚሰጠው መልስ ለማወያየት ብሎም ግኑንኝነቱን ለማነቃቃት፣ እምነትን እና ባህል RealAudioMP3 የሚያወያይ፣ እምነት እና አልቦ እምነት በአንድ አንገብጋቢ ርእስ ሥር ተገናኘተው እንዲወያዩ በሚል እቅድ ሥር በቦሎኛ በፓሪስ በቡካሬስት በፊረንዘ በሮማና በቲራና ካካሄዳቸው ዓውደ ጥናቶች በመቀጠል እ.ኤ.አ. መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚጠቃለለው በኢጣሊያ ፓለርሞ ከተማ “የሕጋዊነት ባህልና ኅብረሃይማኖተኛ ኅብረተሰብ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ዓውደ ጥናት ትላትና መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ “ቤተ ክርስትያንና የሕጋዊነት ባህል በሚል ርእስ ሥር በሰጡት አስተምህሮ ተጀምረዋል።
ኅብረሰብ ባህል እና እምነት ርእስ ዙሪያ በሞንረያለ ካቴድራል የተከፈው ዓውደ ጥናት ከተለያየ ሥነ ባህል አስተያየት የተንደረደረ አስተምህሮ የሚቀርብበት፣ ሕጋዊነት እና በኅብረሃይማኖት ውይይት ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ሲገለጥ፣ በሲቺሊያ የሞንረያለ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ራስፓንቲ “ቤተ ክርስትያንና የሕጋዊነት ባህል” በሚል ርእስ ሥር የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል እቅድ ሥር ያነቃቃው ዓውደ ጥናት በሲችሊያ ሲያካሂድ አለ ምክንያት አይደለም። ቤተ ክርስትያን የሕጋዊነት ባህል እንዲስፋፋ ሕጋዊነት ክርስትያናዊ ሰብአዊ እና ማኅበራዊ ኃላፊነት መሆኑ እንደምታስተምርና በዚህ ዓላማም የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ ልጆች አሉዋት፣ ማፍያነት ጸረ መንግሥት፣ ጸረ ሰብአዊና ጸረ ማኅበራዊ ሕገ ወጥ ተግባር ነው። ሕገ ወጥነትና ወንጀለኛነት ባህል ሆኖ ሲስፋፋ አደገኛነቱ እጅግ ከፍ እያለ ነው የሚሄደው፣ በተመሳሳይ መልኩም ይኽንን ጸረ ስብአዊ ባህል ከማኅበራዊው ዘርፍ ነቅሎ ለማጥፋት ለሚደረገው ትግል ከባድ እና ረዥም ያደርገዋል። ‘ማፊያ’ የማፍያነት ባህል በፓሌርሞ የሚታጠር ብቻ ሳይሆን ዓለማዊነት ትሥሥር ባህርይ ያለውም ነው። ሕገ ወጥነት የአንድ አገር ባህል ሳይሆን ሕገ ወጥነት በመኖር የሚንጸባረቅ ጸረ ሕጋዊነት ማለት ነው። ይኸንን ሕገ ወጥነት ባህል ለመዋጋት አማኒያን እና ኢአማንያን የሚሰጡት አስተዋጽኦ የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በተሰየመው መድረክ ሥር በማገናኘት ለማወያየት ያቀደ በመሆኑ ለሲችሊያ ለጠቅላላ ኢጣሊያ ያለው አስተዋጽኦ አቢይ ነው። ሕዝብን በሕጋዊነት ባህል ማነጽ ለሰላማዊ እና ለተረጋጋ ኅብረተሰብ መሠረት ነው ብለዋል።
ማፊያነት ጸረ መንግሥትና ጸረ ሕዝብ ከመሆኑ በፊት ጸረ ሰብአዊነት ነው። ቤተ ክርስትያን ይኸንን ባህል በጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ቃል አማካኝነት በመዋጋት፣ ሕጋዊ ሥርዓት ለማስፋፋት፣ በሕግ ፊት የዜጎች ኃላፊነት፣ በሕግ ፊት የሁሉም እኩልነት፣ ግልጽነት እና ሕግ የማክበር ባህል እንዲስፋፋ ታነቃቃለች፣ ስለዚህ በቃል እና በሕይወት የሚኖር እምነት እንዲመሰከር በማነቃቃት የምትሰጠው ሕንጸት የሚያጎላ ዓወደ ጥናትም ነው በማለት የሰጡትን ቃል ምልልስ አጠቃለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የባህል ጉዳይ ተነከባካቢው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በተሰኘው መጠሪያ የሚያካሂደው ባህላዊ መርሃ ግብሮችን ዳብሊው ዳብሊው ዳብሊው ነጥብ ኮርቲለደይጀንቲሊ ነጥብ ኮም (www.cortiledeigentili.com) በተሰየመው ድረ ገጽ በኩል ለመከታተል እንደምትችሉ በዚሁ አጋጣሚ ለማስታወቅ እንወዳለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.