2012-03-30 14:11:06

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ፦ “በእምነት ወንድሞችን ማጽናት”።


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በመክሲኮ ጀምሮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. በኩባ 23ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ከማጠናቀቃቸው አንድ ቀን ቀደም በማድረግ በኩባ ርእሰ ከተማ ሃቫና በሚገኘው አብዮት አደባባይ እ.ኤ.አ. 1998 ዓ.ም. RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እና ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከተ ብቻ ሳይሆን የዛሬ እሩቅ 53 ዓመት ቤተ ክርስትያን በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ በቫቲካን ራዲዮ አማካኝነት በኩባ አንደኛ ብሔራዊ የካቶሊካውያን ጉባኤና ለዓለማውያን ምእመናን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ጠቅላይ ጉባኤ ተሳታፊዎች ምእመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያስተላለፉት መልእክት የሚያስተጋባ መሆኑ ሲነገር፣ እ.ኤ.አ. ህዳር 29 ቀን 1953 ዓ.ም. ዕለተ ሰንበት በፊደል ካስትሮ የተመራው የአገሪቱ አብዮት ድል ባደረገበት ልክ በአንደኛ ወሩ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ በቫቲካን ረዲዮ በኩል አንደኛው የአገሪቱ የካቶሊካውያን ጉባኤ ለመባረክ እና ለተጋባእያን ምእመናን የሚያስተላልፉት መልእክት ለማዳመጥ በአብዮት አደባባይ ለተሰበሰበው የአገሪቱ ምእመናን፣ ያ በስቃይ በመከራ በሐዘን ከሚገኘው ጋር የሚያስተባብረው እና አንድ የሚያደርገው እውነተኛው ደስታ እና ድኅነት የሆነው እውነተኛው ፍቅር ከነገሠ በእውነት የዓለማችን ገጽ እንደሚታደስ የማያጠራጥር ነው በማለት፣ ክርትስያናዊ ፍቅር የአገር ሃብት ለሁሉም የሁሉም ሆኖ ለማኅበራዊ እርባና የሚያነቃቃ ነው። ይኽ ደግሞ አማራጭ ደግነት ሳይሆን የሁሉም ኃላፊነት እና ግዴታም ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ጥላቻ እና ቂም በቀል የሞት መራራው ፍሬ የሚሰጥ ከሆነ ባንጻሩ ክርስትያናዊ ፍቅር ብቸኛው ክፋትንና መራራውን ሁሉ በማስተካከል ሥቃይንም በመለወጥ ተስፋና ውኅደት የሚያረጋግጥ ማኅበራዊ ሰላም የሚያነቃቃና እውን የሚያደርግ ነው። ስለዚህ ሁሉም መንግሥታውያን መዋቅሮች ይኸንን ትብብርና መደጋገፍ የሚለው ፍቅር እንዲያነቃቁ በማሳሰብ፣ ክርስትያናዊ ፍቅር ሁሉም በአንድ አባት ሥር የአንድ አቢይ ቤተሰብ አባል የሚያደረግ ነው። እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የኩባው ሐዋርያዊ ጉብኝት ይኸንን ክላዊው መልእክት ያስተጋባ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.