2012-03-30 14:13:53

አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፦ የቅዱስ አባታችንና የፊደል ካስትሮ ግኑኝነት


የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ በዚህ 23ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሸኙ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዱስነታቸው ሃቫና በሚገኘው በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሕንፃ ከቀድሞ የኩባ ርእሰ ብሔር ፊደል ካቶሮ ጋር RealAudioMP3 መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ ስለ ተካሄደው ክሌአዊ ግኑኝነት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ግኑኝነቱ አበይት ወቅታዊ ጉዳዮች የዳሰሰ ነበር ካሉ በኋላ፣ ፊደል ካስትሮ የፖለቲካው ሥልጣንም ሆነ ኃላፊነትም የሌላቸው በመሆኑ ከቅዱስነታቸው ጋር ለመገናኘት እና አንዳንድ ጥያቄዎች ለማቅረብ እንደሚሹ አስታውቀው እንደነበር አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጥሪ፣ የእሳቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነት “አገልግሎት”፣ እንዲሁም እምነት እና ሥነ ጥበብ (ምርምር)፣ ምርምር ለሰው ልጅ መሠረታዊ ጥያቄ የተሟላ መልስ የማይሰጥ መሆኑ፣ በተለያዩ ኃይማኖትች መካከል የሚከናወነው የጋራው ውይይት በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ቅዱስነታቸው በዚያ በተካሄደው ግኑኝነት አብራርተው፣ የሰው ልጅ በኑባሬ ያለው ሃይማኖተኛ ዝንባሌው ሲደመጥ፣ በዓለም ለሚጋረጠው እክል መፍትሄ ለመሻት ብርሃን በመሆንና መንገድንም ለመለየት እንደሚያግዝ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ የሰው ልጅ ከዚህ ዝንባሌው ውጭ መመልከቱ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ብለዋል።
የተካሄደው ግኑኝነት የዛሬ 14 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከፊደል ካትሮ ጋር ያካሄዱት ክሌአዊ ግኑኝነት ያስተጋባ፣ ቤተ ክርስትያን በኵባ ተልእኮዋና ተግባርዋንም ጭምር ያነቃቃ መሆኑ ያረጋገጠ እንደነበር አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው፣ በወቅቱ በዓለ ልደት ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያቀረቡት ጥሪ በርእሰ ብሔር ፊደል ካስትሮ አወንታዊ ምላሽ እንዳገኘ አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን ከርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ ጋር ተገናኝተው የአገሪቱ ምእመናን ለበዓለ ትንሣኤ ዘእግዚእነ በበለጠ እንዲዘጋጅ አርብ ሥቅለት በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ እንዲዘከር ጥያቄ ማቅረባቸው ያስታወሱት የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ፣ ቤተ ክስትያን በአገሪቱ ለማኅበራዊ ጥቅም ያቀና የሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት እግብር ላይ እንደምታውል የተመሰከረበት ግኑኝነት ነበር ብለዋል።
የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ከአንድ አገር ሕዝብ በገዛ አገሩ ቀርበው በመገናኘት በአገሪቱ ዕለታዊ ሕይወት ለመሳተፍ በሚፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለመወያየት በተለይ ደግሞ ሥልጣንና ኃላፊነት ለማኅበራዊ ጥቅም ማስፈጸሚያ የሚል የላቀ ክብር ያለው መሆኑ ያነቃቃሉ በማለት አባ ሎምባርዲ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.