2012-03-30 14:22:09

ብፁዕ አቡነ ማርቲነሊ፦ የሊቢያ ክርስትያን ማኅበረሰብ ለአገራዊ እርቅ አስፈላጊ ነው


የሊቢያ ማኅበረ ክርስትያን በአገሩ ለሚከናወነው ዘርፈ ብዙ ግንባታ ዋና ተወናያን መሆኑ በዕለታዊ ኑሮው እና በተለያዩ በአገሪቱ በሚካሄዱት ብሔራዊ እቅዶች፣ ለእርቅ የሚበጅ መንገድ እየመሰከረ RealAudioMP3 እንደሚገኝ በሊቢያ ለርእሰ ከተማ ትሪፖሊ ሐዋርያዊ መስተዳዳር ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆቫኒ ኢኖቸንዞ ማርቲነሊ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።
ባለፉት 40 ዓመታት የገዳፊ ሥርዓት ያንን ሥርዓት በመቃወም ተከስቶ በነበረው ግጭት ቀጥሎም አልፎ አልፎ በጎሳዊ ማሕጸን የተጠነሰሰው የእርስ በእር ግጭት የሚታይ መሆኑና ባለፉት ቀናት በዚህ ዓይነት ግጭት ሳቢያ በሰባሕ በሁለት ጎሳዎች መካከል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ 70 ሰዎች ለሞት ሌሎች 150 ለመቁሰል አደጋ መጋለጣቸው ጠቅሰው የዚህ ዓይነት ችግር እንዳይባባስ የሊቢያው ማኅበረ ክርስትያን የዚህ ዓይነት የእርስ በእርስ ግጭት እንዳይዛመት እና ለማስወገድም በተለያዩ ማኅበራዊ ዘርፎች አስተዋጽኦ እየሰጠ ነው ብለዋል።
በሊቢያ የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን በሕክምና መስጫ ጣቢያዎች ተሰማርቶ በሚሰጠው አገልግሎት ክርስትያናዊ መንፈስ በማንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ። የአገሪቱ ማኅበረ ክርስትያን ዘንድ የፊሊፒንስ እንዲሁም ከደቡባዊ የሰሃራ ክልል የመጡ ስደተኞች ጭምር የሚያካትት መሆኑ ገልጠው፣ በአገሪቱ የሚታየው ማኅበራዊ ውጥረት ሳይበግራቸው በተሰማሩበት የአገልግሎት ሙያ አለ ምንም ልዩነት ማኅበራዊ ሰላም በመመስከር፣ የተዋጣለት አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፣ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን በነዚህ ልጆችዋ አማካኝነት ለሊቢያ ማኅበራዊ እርቅ አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጠች ነው።
የሊቢያው ማኅበረ ክርስትያን ለበዓለ ትንሣኤ ተስፋ ለመዝራት በሚያስችሉ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ተግባሮች መሠረት በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ብፁዕነታቸው ገልጠው፣ ሞትን አሸንፎ የዚያ ጥልቅ ፍራት ከሰው ልጅ ልብ እና ሕይወት ነቅሎ ያስወገደው በክፋት መንፈስ ላይ ድል የነሣው የጌታችን ትንሣኤ በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ያለው ጎሳዊ ግጭት ጨርሶ እንዲወገድ ለማድረግ ያለው ኃይል ለመመስከር በሚል መንፈስ በተመራው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ለበዓለ ትንሣሴ እየተዘጋጀ ነው በማለት የሰጡትን ቃል አምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.