2012-03-28 14:48:08

ኅያው ቤተ ክርስትያን በኩባ ኅብረተሰብ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ 23ኛው ዓለም አቀፍ የሐዋርያዊ ጉብኝት እቅድ መሠረት እ.ኤ.አ. መጋቢት 26 ቀን ኩባ ከገቡ በኋላ የኩባው ሐዋርያዊ ጉብኝት ሂደት በማስመልከት በዚሁ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅዱስነታቸው በመሸኘት ላይ የሚገኙት የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ RealAudioMP3 የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፦ ቅዱስ አባታችን ሳንቲያጎ ደ ኩባ አየር ማረፊያ እንደደረሱ የጠበቃቸው አቀባበል ሕዝቡ ያሳየው እውነተኛ ልባዊ ደስታ ከገመቱት በላይ ሆኖ እንዳገኙት ከገለጡ በኋላ ቅዱስነታቸው ከቀድሞ የኩባ ርእሰ ብሔር ፊደል ካስትሮ ጋር መገናኘት የሚቻል ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን በአየር ማረፊያው ለመቀበል እዛው በመገኘትና ቅዱስነታቸውም እንደደረሱም ሕዝቡ ያሳየው ኅያው ደስታ ለሁሉም አስደንቀዋል። ይኽ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለየት የሚያደረገውም የኵባ ሕዝብ የአገሪቱ ጠባቂ ቅድስት ፍቅርተ ማርያም ዘ ኮብረ አነስተኛ ቅዱስ ሐውልት የተገኘበት 400ኛው ዓመት ምክንያት የሚያከብረው በዓል የሚያሰጠው ትርጉም መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ከኩባ ሕዝብ ጋር በመሆን ይህችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለማክበር እዛው የፍቅር ነጋዲ በመሆን እንደሚገኙም ነው። ሆኖም የሐዋርያዊው ጉብኝት ማእከል ወንድሞችን በእምነት ማጽናት የተሰኘው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተልእኮ መሆኑ አስታውሰው፣ በዚህ ጥሪ ሥር ለምተመራው በኵባ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የሚያበረታታ የሚያጸና በኩባ የምትገኘው በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈችው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሕይወት የሚዳስስ ከፍቅር የመነጨ ምስክርነቷ መሠረት በትህትና ገዛ እራሷን ዝቅ በማድረግ በአገሪቱ እና በዜጎች ሕይወት የምትሰጠው አገልግሎት የሚዘረዝር፣ የሚያጋጥማት እክል የሚያጎላ ሆኖም ብሩህና የላቀ መጻኢ ላይ በማተኮር እርሱም የዛሬ 14 ዓመት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በኩባ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ኩባ በሮችዋን ለዓለም ትከፍት ዘንድ ዓለምም በሮቹ ለኩባ ይከፍት ዘንድ በማለት ያቀረቡት ጥሪ ላይ የጸናና ይኸንን የሚያስተጋባ ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው ብለዋል። በዚህ 400ኛው ማርያማዊ በዓል ምክንያት በአገሪቱ እምነት ዳግም ለማነቃቃት በሕዝቧ መካከል እርቅ በማስፋፋት በሰላማዊ የጋራው ሕይወት አማካኝነት በአዲስ መንፈስ መጻኢን አተኵሮ መጠባበቅ ለሚለው ዓለማ ማረጋገጫ የሚሆነው መሪ ቃል ለምእመናን እና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች የሚሰጥበት ሐዋርያዊ ጉብኝትም ነው።
በኩባ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሚያውቁዋት ዘንድ ለአገሪቱ ኅብረተሰብ የምትሰጠው አቢይ አስተዋጽዖ ይመሰከራል። በአገሪቱ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን ካጋጠሙዋት እክሎች አንዱ ማርክሳዊ ርእዮተ ዓለም ዘክረው ያ ርእዮተ ዓለም ማኅበራዊ ባህልዋ ቢያሰናክልም እንድትወድቅ ግን አላደረጋትም፣ ከሁሉም ጋር የምትወያይ መሆንዋ ባላት የላቀው መንፈሳዊ እና ግብረ ገባዊ ኃላፊነት መሠረት ከሕዝብ እና ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ብቃት ያላት መሆንዋ አስመስክራለች ብለው፣ በመጨረሻም በቤተ ክርስትያን እና በመንግሥት መካከል ያለው ግኑኝነት መልካም ነው። ሐዋርያዊ መንበር በተለያዩ አገሮች በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤት ክርስትያን አማካኝነት በእያንዳንዱ ተጨባጭ አገር ኅያው ይሆናል። ስለዚህ በቅድስት መንበር እና በአገረ ኩባ መካከል ያለው ግኑኝነት በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ኅያው ትሁት እና ገንቢ ኅልውናዋ የሚያረጋግጥ ነው። ሆኖም ይኽ ግኑኝነት እድገት ሊያሳይ ስለ ሚጋባውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው አማካኝነት ይኸንን እንደሚያበረታቱ ነው በማለት የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.