2012-03-28 14:44:53

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በኩባ


መክሲኮን እና ኩባን የሚያጠቃልለው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 23ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በመክሲኮ ተካሂዶ እስከ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚዘልቀው የኩባው ሐዋርያዊ ጉብኝት ትላትና RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ኩባ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሳንቲያጎ ደ ኩባ የአየር ማረፊያ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ አቀባበል ተደርጎላቸው በይፋ ተጀምረዋል።
ቅዱስነታቸው በአየር ማረፊ ሳንቲያጎ ደ ኩባ እንደደረሱ ለኩባ ሕዝብ የዓቢይ ተስፋ መልእክት በማሰማት፣ የአገሪቱ ሕዝብ ነገን በአመኔታ አተኵሮ እንዲመለከት ያቀረቡት ምዕዳን እዛው ይጠባበቃቸው ከነበረው በብዙ ሺሕ በሚገመተው ሕዝብ አወንታዊ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
የኵባ ሕዝብ የዛሬ 14 ዓመት ለር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዛሬ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሳየው የሞቀ አቀባበል እና ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያለው ፍቅር በማስተጋባት ቅዱስነታቸው ኩባን ለመጎብኝት እዛው መገኘታቸው ሕዝቡ ደስ መሰኘቱ እና ይኸንን የፍቅር ነጋዲ በተሰኘው መርህ ቃል የተሸኘ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኩባው ሐዋርያዊ ጉብኝት በጉጉት ይጠባበቅ ለነበረ ጸጋ መሆኑ ቅዱስነታቸው በደረሱበት የአየር ማረፊያ በሚያልፉበት መንገድ ሁሉ በመገኘት በደስታ እና በጭብጨባ በመቀበል ሕዝቡ መስክሮታል።
በአየር ማረፊ ደርሰው ባሰሙት መልእክት፣ ውድ ወንድሞቼ ኩባ በታሪክዋ አቢይ ሥፍራ የያዘው በአሁኑ ወቅት እየኖረቸው ያለው ተጨባጭ ታሪክ መሠረት፣ ሕዝቧ ነገን በተስፋ አተኩሮ በመመልከት ለኅዳሴ ኃይሉን እና ብቃቱን በማጣመር አድማሱንም በማስፋት በአመኔታ እየተጠባበቀ መሆኑ የሚታይ እውነት ነው። ሕዝቡ በሥራው እና በሕይወቱ የሚገለጠው እውነተኛው መለያው ለሆነው ማንነቱን ቅርጽ ላስያዘው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ጥልቅ መንፈሳዊ እሴቶች እና ግብረ ገብ እንደሚያከብር ያረጋግጠዋል። ይኸ እውነት እንዲኖር መተባበር ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ፣ አክለውም እነዚህ እሴቶች ለማነቃቃት በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቸር እና ደከመኝን በማያውቀው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተልእኮዋ አማካኝነ ውጥኖችዋንም በማደስ ካለ መታከት ሁሉንም ለማገልገል የምታከናውነው ተግባር ትቀጥልበታለች። በኵባ እያከናወኑት ያለው ሐዋርያዊ ጉብኝት ዓላማ ወንድሞችን በእምነት ለማጽናት በተስፋ ለማበረታታት መሆኑ ገልጠዋል።
የሚገኙበት ሥፍራ ሳይለይ የሁሉ ኩባውያን ቅን ምኞትና ተገቢው ፍላጎት ስቃይ እና ደስታ፣ የሚያቀናባቸው የላቀው እና የተከበረው ቅን ጉጉቱ ለየት ባለ መልኩም የወጣቶች የአረጋውያን የሕፃናት የኅሙማን የሠራተኞች የእስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙት ቅን ፍላጎት በልባቸው አቅበው እንደሚጓዙ አረጋግጠው፣ የዛሬ 14 ዓመት በኩባ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ወኔ ያነቃቃው ለብዙዎች የእምነት አስፈላጊነት የሚል ኅሊናዊ ግንዛቤ ያደሰው ሁሉ ልቡን ለክርስቶስ እንዲከፍት ተስፋን ያበራው በትጋት ለበለጠው መጻኢ ሁሉም እንዲጠመድ የሚሻው የሁሉም ፍላጉት ያነቃቃው የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የኩባ ሐዋርያዊ ጉብኝት በላቀ መንፈስ አስታውሰዋል። ያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በኩባ እና በቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት በመተማመን ላይ የጸና በበለጠና ከፍ ባለ የትብብር መንፈስ ተክኖ፣ በአዲስ ምዕራፍ እንዲነቃቃ ማድረጉንም ዘክረው፣ ሆኖም ሃይማኖት በማኅበራዊ ዘርፍ ሊሰጠው የሚገባው አቢይና የተገባ አስተዋጽዖ እርሱም ኩባ ካላት እምነት እና ማርያማዊ መንፈሳዊነት ላይ ጸንቶ የሚረጋገጠው አስተዋጽኦ እውን ለማድረግ የሚያግዝ አጋጣሚ አስፈላጊነቱ ከገለጡ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የኩባ ጠባቂ ቅድስት ፍቅርተ ማርያም ዘ ኮብረ አነስተኛ ቅዱስ ሐወልት የተገኘበት 400ዓው ዓመት የሚከበርበት ወቅት የኩባ ሕዝብ በእምነት ጉዞ ለምትደግፈው እና ሕይወት ያለው ክብር መሠረታዊ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር እንዲነቃቃና ጥበቃ እንዲደረግለትም ለምታበረታታው ለቅድስት ድንግል ማርያም ያለው ፍቅር የሚመሰክርበት ወቅት ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ያለው የዓለም ሕዝብ እጅግ እየነካ መንስኤውም መንፈሳዊ እና ግብረ ገባዊ መቃወስ የሆነው በመታየት ላይ ያለው ያስታወሱት የኤኮኖሚ ቀውስ፣ ቀጥለው ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የእንኳን ደህና መጡ መልእክት ያሰሙት፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ በማስተጋባት፣ ሕዝብን ለድኽነት የሚዳርገው ቁጠባዊ ሥልጣን ነቅፈው የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በኵ ባ ላይ የደነገገው የኤኮኖሚ ማእቀብ ካወገዙ በኋላ አክለውም የኤኮኖሚው ቀውስ በሌላ መልኩም ግብረ ገባዊ መቃወስ መሠረት ያለው መሆኑ ገልጠው፣ የዓለማችን አቢይ ሥቃይ፣ በዓለማችን የሚይታየው ፖለቲካዊ ምግባረ ብልሽትና እውነተኛ ዴሞክራሲ እጥረት መሠረት ያለው ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.