2012-03-28 14:49:32

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለብሔራዊ አቀፍ የወጣቶች ቀን መልእክት አስተላለፉ


እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ከተማ የሚከናወነው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ያተኮረ በላቲን ሥርዓት ከሚከበረው በዓለ ሆሳዕና ቀን ጋር ተያይዞ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ለሚከበረው ለወጣቶ ቀን “ክርስትያን ስለ እርሱ ብሎ ሕይወቱ ከሰጠው ክርስቶስ ጋር የተገናኘ በመሆኑ የተከዘ ሕይወት RealAudioMP3 አይኖርም በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት ትላትና ይፋ ሆነዋል።
በዚህ ወጣቶች የደስተኛ ሕይወት ልኡካን እንዲሆኑ በሚያሳስበው ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፦ ክርስትያን ለብቻው ደስተኛ መሆን አይችልም፣ ሌሎች ደስተኞች ካልሆኑ ምንም’ኳ የተቀበልከው የእምነት ጸጋ ደስተኛ የሚያደርግህ ቢሆንም፣ የሌሎች አለ መደሰት ለተቀበልከው ደስታ ልኡክ መሆንህ ነው የሚያሳስበው። በዚህ በተዋከበው እና ባልተረጋጋ መንፈስ በሚኖረው ዓለም እውነተኛ ክርስትያን ደስታውን አቅቦ በአካባቢው የሚኖረው ክርስትያናዊ ደስታውን ማስፋፋት ይገባዋል።
ቅዱስ አባታችን በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ አንድ ቀን 2012 ዓ.ም. ከሚከበረው በዓለ ሆሳዕና ጋር ተያይዞ በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ የሚከበረው የወጣቶች ቀን በገዛ እራሱ የሚታጠር ሳይሆን ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የሚያነቃቃ፣ ክርስትያናዊ መልእክት የደስታ እና የተስፋ መልእክት መሆኑ የሚመሰክር ነው። ስለዚህ ክርስትያን የተከዘ ሕይወት እንዴት ሊኖር ይችላልን? ክርስትና ለሕይወት ለቤተሰብ ለጋደኝነት መንፈስ ክብር የሚሰጥ እውነተኛው ትርጉሙን በመኖር እና በማረጋገጥ በመመስከር፣ የእውነተኛው ቅን ፍቅር መስካሪ ለመሆን የሚያነቃው የደስታ መክንያት በመኖር አካባቢያውን በዚህ ደስታ የታወደ እንዲሆን የክርስትያናዊ ደስታ አብሳሪያን ለመሆን የጠራ ነው። ድል አድራጊው የክፋት መንፈስ ሳይሆን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት፣ ድል አድራጊው የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ ያረጋግጥልናል ካሉ በኋላ፣ ውዶቼ ወጣቶች በክርስቶስ ላይ ታምናችሁ በእርሱ ላይ ጸንታችሁ በሁሉም መስክ ንቁ ተሳታፊዎች ለመሆን አትፍሩ ካሉ በኋላ አንድ ካቶሊክ ደስተኛ አለ መሆን የሚቻለው አይደለም ያለው ብፁዕ ፒየር ጆርጆ ፍራሳቲና፣ በእርሱ ፍቅር ተለውጬ በደስታ ለሚያውደው የሕይወት ምሥጢር መኖሪያ ልሁን ስትል የተናገረቸው ገና በ18 ዓመት እድሜዋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው ቤተ ክርስትያን ብፅዕና ያወጀችላት ብፅዕት ኪያራ ባዳኖን ዘክረው፣ ክርስትያን ነጻነት እንጂ ነጻነታችንን የሚሰርዝ አይደለም፣ ነጻነታችንን እውነተኛ ነጻነት እንዲሆን ያደርጋል በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.