2012-03-22 09:43:43

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. 23ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት
መክሲኮ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 23 ቀን እስከ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም.
ኵባ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 26 ቀን እስከ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም.


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመክሲኮ ለማካሄድ ስለ ወሰኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት በሮማ ለጳጳስዊ የመክሲኮ ተቋም ዋና አስተዳዳሪ አባ አርማንዶ ፍሎረስ ናቫሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስነታቸው በዚያች መጪው ሕይወት በአመኔታ እና በተስፋ በምትመለከተው ዘመናዊነት እና ትውፊት የሚገናኙባት እና የሚነጻጸሩባት ጥንታዊት አገር የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ር.ሊ.ጳ. የምታፈቅር እና በር.ሊ.ጳ. የምትፈቀር ሃገረ መክሲኮ በእምነት ብሎም በሱታፌ እና በፍቅር ለማጽናት ነው ካሉ በኋላ፣ መክሲኮ ለሐዋርያዊ መንበር ማለትም ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያላት ፍቅር ለማንም የተሰወረ አይደለም። በርግጥ በዚያች አገር ክርስትያናዊ እሴቶች የምንላቸው፣ ቤተሰብ የሕይወት ባህል የመሳሰሉትን በመጥቀስ የሚሰጣቸው ትኵረት የላቀ ቢሆንም እሴቶችን የሚቀናቀን ተጋርጦ አለ፣ ስለዚህ ቤተ ሰብ ያለው ባህላዊ እና ክርስትያናዊ ትርጉሙ ለአደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ይታያሉ፣ ድኽነት ያልተስተካከለ ማኅበራዊ ሕይወት፣ አመጽ፣ የተደራጁ የወንጀል ቡድኖች የመሳሰሉት በጠቅላላ አገሪቱ ለምትከተለው ክርስትያናዊ እሴቶች እጅግ ከባድ ተጋርጦ ናቸው። ቤተ ክርስትያን እና መንግሥት መካከል ያለው ታሪካዊ መሠረት አለ መግባባት በተመለከተ ብዙ ውይይት ይካሄዳል ሆኖም ይኸ ቅራኔ ለማግለል ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸው አስታውሰው፣ የዚያች አገር ሕዝብ የጦፈ አማኝ ነው። እምነቱ በትክክል ለመኖር የሚጥር ሕዝብ ነው። ይኽ ደግሞ ካለው ክርስትያናዊ እና ሃይማኖታዊ ባህል አንጻር የሚኖረው ሲሆን፣ ይኸንን ሃይማኖተኛውን ባህል በቁምስናዎች በመደራጀት፣ ኵላዊነቱን፣ በኵላዊት ቤት ክርስትያን ሥር በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ሥር በመገስኘት ይኖረዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመክሲኮ የሚደረግላቸው አቀባበል የሞቀ እንደሚሆን አልጠራጠርም ካሉ በኋላ ቅድስነታቸውን ለማየት ከእሳቸው ጋር ለመገናኘት በሳቸው ፊት ተገኝቶ የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት ለመቀበል የቤተ ክርስትያን አሳቢነት ለማጣጣም ሕዝቡ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው። የመክሲኮ ሕዝብ ተስፋ የሚያነቃቃ የሚመራ በመክሲኮ ላለቸው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚህ ተስፈኛው ሂደት ልትከተለው የሚገባት መንገድ የሚያመለክት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.