2012-03-13 11:18:32

የር.ሊ.ጳ የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (11.03.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፡ የጾመ አርባ 3ኛ እሁድ የዛሬው ቃለ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚተርከው ኢየሱስ በቤተ መቅደስ የሚነግዱትንና ገንዘብ ለዋጮችን እንዳባረረ (ዮሐ 2፡13-25) ነው። ክንዋኔው በሌሎች ወንጌላውያንም የተጻፈ ሲሆን በዓለ ፋሲካ ተቃርቦበት በነበረ ግዜ ስለነበር እዛው በነበሩ ሕዝብም ይሁን በሐዋርያት ታላቅ የመደነቅ ስሜት ፈጥረዋል።፡ ይህንን የኢየሱስ ተግባር ምን ብለን መተርጐም እንችላለ? ያኔ እንደ ነቢያዊ ተግባር ስለታየ በቤተ መቅደሱ በነበረ ሕዝብም ይሁን ጸጥታ አስከባሪዎች ምንም ዓይነት የተቋውሞ ግብረ መልስ አልደተረገም፡፡ ነቢያት ሁል ግዜ ይፈጸሙ የነበሩትን ዓመጾች በእግዚአብሔር ስም ያወግዙ ነበር፡፡ አንዳንዴም ምሳሌአዊ ትርጉም ባላቸው እንቅስቃሴዎች ያደርጉት ነበር።፡ ችግር ያጋጠመ እንደሆነ ሥልጣናቸውን ይጠይቁ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አይሁድ ኢየሱስን “በየትኛው ሥልጣን ይህንን ታደርጋለህ ምን ምልክት ታሳየናለህ” (ዮሐ 2፡18)” ብለው የጠየቁት ማለትም እውነት በእግዚአብሔር ስም የምትሰራ መሆንህን አሳየን ያሉት፡።
ኢየሱስን ያኔ ከነበረው የቀናአን እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝም፡ ይህንን የነጋዴዎችን ከቤተ መቅደስ ማባረር እንደ ፖሎቲካዊ የአብዮት እርምጃ ተርጉሞውት ነበር፡። እነኚህ ለእግዚአብሔር ሕግ ባላቸው ቅንአት የተነሳሱ የቀናእያን እንቅስቃሴ የእግዚአብሔር ሕግን ለማስከበር አስፈላጊ ከሆነ ኃይል ለመጠቀም ዝግጁ ነበሩ፡። በኢየሱስ ግዜ እነኚህ ሰዎች ከሮማውያን የግዛት ቀንበር ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይጠባበቁ ነበር፡። ኢየሱስ ግን እነርሱ እንዳሰቡት ስላልተካሄደ ሐሳባቸው በኖ ቀረ፡፡ ስለዚህም ከተከታዮቹ ብዙዎች ጥለውት ሄዱ አስቆሮታዊው ይሁዳም አሳልፎ ሰጠው፡። ኢየሱስን እንደ አብዮታዊ ዓማጺ አድርጎ መመልከት የማይሆን ነው፡፡ ዓመጽ ከእግዚአብሔር መንግሥት ጋር ይቃረናል፡፡ የክርስቶስ ጠላት መሣርያ ነው፡። ዓመጽ በምንም ተአምር ለሰው ልጅ ጥቅም ውሎ አያውቅም፡ የባሰውኑ ሰውን ኢሰብአዊ ያደርገዋል፡።
ኢየሱስ ነጋዴዎችን ሲያባርር ያለው የሰማን እንደሆነ “ይህን ሁሉ ወዲያ ውሰዱ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት” ይላቸዋል፡ ሐዋርያቱም ያኔ በመዝሙረ ዳዊት “ስለ ቤትህ ያለኝ ቅንአት እንደ እሳት አቃጠለኝ” (69፡10) የሚል ተጽፎ እንደሚገኝ አስታወሱ።፡ ይህ መዝሙር በጠላቶች ጥላቻ ተከበው በብርቱ አደጋ ሲገኙ የሚያሳርጉት ልመና ነው፡፡ ኢየሱስ በሕማማቱ ግዜ ሊኖረው ነው። ለአባቱ ቤት ያለው ቅንአት እስከ በመስቀል ተሰቅሎ መሞት ያደርሰዋል፡ የእርሱ ቅንአት በሕይወቱ የሚከፈለው የፍቅር ቅንአት እንጂ እግዚአብሔርን በዓመጽ የሚያገለግል ቅንአት አይደለም፡። ስለሆነም አይሁድ ምልክት በጠየቁበት ግዜ የሥልጣኑ ማረጋገጭ አድርጎ ያቀረበላቸው ሞቱና ትንሣኤውን ነበር። “ይህንን ቤተ መቅደስ አፍርሱትና እኔ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ” አላቸው፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወዲያውኑ “ኢየሱስ ቤተ መቅደስ ብሎ የተናገረው ስለ ሰውነቱ ነበር ሲል ያመለክታል፡፡
ከኢየሱስ ፋሲካ ጋር አዲስ ሥርዓተ አምልኮ ይጀምራል፡፡ የፍቅር ሥርዓተ አምልኮ፡ ኢየሱስ ራሱ የሆነው ይህ አዲስ ቤተ መቅደስ፡ ከሙታን ተለይቶ በተነሣው ክርስቶስ በዚሁ አዲስ ሥርዓተ አምልኮ አማካኝነት፡ አማኝ ሁሉ በመንፈስና በሐቅ እግዚአብሔር አብን ይሰግዳል ያከብራልም (ዮሐ 4፡23)።
ውዶቼ መንፈስ ቅዱስ ይህንን ኣዲስ ቤተ መቅደስ በእመቤታችን ድንግል ማርያም ማኅጸን አነጸው፡ እያንዳንዱ አማኝ የዚህ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ሕያው ድንጋይ እንድንሆን በእመቤታችን ድንግል ማርያም በመማጠን እንጸልይ።፡
ውድ ወንድሞችና እኅቶች ሃሳቤና ቀልቤ በቅርቡ በብርቱ የተፈጥሮ አደጋ በተጐዱ የማዳጋስካር ሕዝብ ላይ ነው።፡ አደጋው በሰዎች በሕንጻዎችን በእርሻ ላይ ጉዳት አውርደዋል። የዚህ አደጋ ሰለባ ለሆኑት ሁላቸው በጸሎት እንደማስባቸው በመንፈስ እጐናቸው መሆኔን ሳረጋግጥ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በልግሥና እንዲረድዋቸው አደራ እላለሁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.