2012-03-12 15:47:15

ር ሊ ቃ ጳጳሳት በነዲክት አንገሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ዊልያምስ ተቀብለው አነጋገረዋል፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ትናትና ረፋድ ላይ በታላቅ ብሪታንያ አንገሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ ተቀብለው ማነጋገረቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል ።

በዚሁ መግለጫ መሰረት ቅድስነታቸው እና ሮዋን ዊልያምስ ከቀትር በኃላ በጋራ ሮም ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ጎርጎርዮስ በጋራ ጸሎተ ሰርክ ፈጽመዋል ።

ሁለቱ መንፈሳውያን መሪዎች በዚሁ ጥንታዊ ገዳም በጋራ ጸሎተ ሰርክ ያካሄዱበት ምክንያት ሺሔኛ ዓመት የቅዱስ ኤረሞ ዘ ካመልዶሊ ምክንያት በማድረግ እንደሆነ መግለጫው አያይዞ አብራርተዋል።

በቸልዮ የቅዱስ ጎርዶርዮስ ጥንታዊ ገዳም ከ1573 እኤአ ጀምሮ በኤረሚቲ ዘ ካምልዶሊ እንዲተዳደር በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጎርጎርዮስ 13ኛ መልካም ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን በግርጎርዮ ማኞ የተሠመስረተ እንደሆነ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ታሪክ ያስረዳል።

የዚሁ ጥንታዊ ገዳም የበላይ ሐላፊ አባ ኢኖቸንዞ ጋርጋኖ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና በታላቅ ብሪታንያ የካንተበሪ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ ገዳሙ የጐበኙበት እና በጋራ የጸለዩበት ምኽንያት ሲያስረዱ ፡እኤአ በ597 ዓመተ ምሕረት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ማኞ አርባ የገዳሙ አባላት በታላቅ ብሪታንያ ዜና ሰናየ ቅዱስ ወንጌል እንዲሰብኩ ወደ ሀገሪቱ መላካቸው እና ገዳሙ የብሪታንያ ክርስትያናዊ ምንጭ በመሆኑ ነው በማለት ገልጸዋል ።

በወቅቱ ከሮማ በተላኩ ገዳማውያን እገዛ ክርስትና የተቀበሉ እና ገዳማት ያቋቋሙ የብሪታንያ ገዳማት በበኩላቸው ወደ ኔዘርላንድ ጀርመን ስዊትጸርላንድ ወደ አውስትርያ እስከ ኤልባ ወንዝ ዘልቀው ቃለ ሰናየ በመስበክ ክርስትና እውን እንዲሆን አድርገዋል ያሉት አባ ኢኖቸንጾ ጋርጋኖ የቅዱስ ጎርጎርዮስ ገዳም የበላይ ሐላፊ ይህ እኤአ በ597 ዓመተ ምሕረት የሆነውን መሆኑ ልብ እንበል ማለታቸው ተዘግበዋል።

ሁለት የቀድሞ የካንተበሪ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ ጎርጎርዮስ ገዳም ተመሳሳይ ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሄደ ነበር።

ይሁን እና በታላቅ ብሪታንያ አንገሊካዊ የካንተበሪ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ ከቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ጋር በግል ለበርካታ ሰዓታት ሐሳብ መለዋወጣቸው ታውቆዋል።

ሮዋን ዊልያምስ ለራድዮ ቫቲካን የእንግልዝኛ ፕሮግራም በሰጡት መግለጫ መሠረት ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ጋር በተገኛኙበት ግዜ ሙሉ የክርስትያን አንድነት በሚገኝበት ርእሰ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው አስታውቀዋል።

ከዚህ ባሻገርም የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ እና ይህን በተመለከተ የአባየት ክርስትያናት ምላሽ የክልሉ መጻኢ ዕድል አዲስ ስብክተ ቅዱስ ወንጌል እና የጳጳሳት ጉባኤ ባለፈ ቅርብ ግዜ በስዊትጸርላንድ የተካሄደው ሰብአዊ መብቶች ትኩረት የሰጠ ጉባኤ እና በተለያዩ አብያተ ክርስትያናት እና ዓለም ነክ ጉዳዮች በስፊው መወያየታቸው አስገንዝበዋል።

የብሪታንያ አንገሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊልያምስ እዚህ ሮም ውስጥ ሲያካሄዱት የሰነበቱት ሐዋርያዊ ዑደት ፈጽመው ዛሬ ከቀትር በኃላ ወደ ላንደን ብሪታንያ መመለሳቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.