2012-03-09 13:29:09

የደቡባዊ ምሥራቅ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት በስትራስበርግ፦ “እምነት ክፍለ ዓለሚቱን ያጠነክራል”


በኤውሮጳ ኅብረት የቤተ ክርስትያን ኅላዌ ግልጽ እና ጥልቅ ሆኖ እንዲታወቅ ያቀደ የኤወሮጳ ኅብረት መንግሥታዊ መዋቅሩን በሚገባ ለመረዳት ካለው ግንዛቤ በመንደርደር የደቡብ ምሥራቅ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ልኡካን በስትራስበርግ ከባለፈው ሰኞ በህብረቱ ዋና ሕንጻ በኤውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ አልዶ ጆርዳኖ ጥሪ መሠረት ሃሳብ እና መረጃ ላይ ያነጣጠረ ያካሄዱት ግኑኝነት፣ ሃይማኖት ለኤውሮጳ ጣምራነት መሠረተ ምክንያት መሆኑ እንዳስገነዘበ ብፁዕ አቡነ አልዶ ጆርዳኖ ስለ ተካሄደው ግኑኝነት በማስልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በተካሄደው ግኑኝነት በቅድሚያ ውይይት የተደረገበት ርእሰ ጉዳይ የሃይማኖት ሚና በተመለከተ ሲሆን፣ በውይይቱም ኃይማኖት ለማኅበራዊ ጣምራነት እና ለባህሎች የጋራው ውይይት መሠረተ ምክንያት መሆኑ እንደታመነበትና፣ ከዚህ በመንደርደርም የሃይማኖት ነጻነት መከበር RealAudioMP3 በተለይ ደግሞ አሁንም በአንዳንድ የደቡብ ምሥራቅ ኤውሮጳ አገሮች ማኅበረ ሰብ አቢያተ ክርስትያን ሕጋዊነት እውቅና የማይሰጠው በመሆኑ፣ ይኽ ችግር ተወግዶ እውቅና በማረጋገጥም በኃይማኖት ምክንያት የሚከሰተው አድልዎ ማግለል የሚለው ውሳኔ አንገብጋቢነቱ ተሰምሮበታል። በሌላው ረገድም በዚሁ የኤውሮጳ ክልል ያለው ሕዝብ የተያያዘው በሳል ወደ ሆነው ሥርዓተ ዴሞክራሲ ሽግግር ከክልሉ ሕዝብ ጋር ውይይት እና ግኑኝነት አስፈላጊ መሆኑ ግንዛቤ አሳድረዋል። በዚህ የኤወሮጳው ክልል ገና ከተለያዩ ግጭቶች ያልተላቀቁ ዘርፈ ብዙ እክሎች የተጋረጠባቸው አንዳንድ አገሮች መኖራቸው፣ የቄጵሮስ ያለው ሁኔታ እንዲሁም በኮሶቮ፣ በማልዲቭ የትራንስኒስትሪያ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ፣ በሩሲያ እና በጆርጂያ ያለው ውጥረት እንደ አብነት በመጥቅስ ካብራሩ በኋላ፣ ከዚህ አኳያ ሲታይ የተካሄደው ግኑኝነት አንገብጋቢ መሆኑ ለመገንዘቡ አያዳግትም። ስለዚህ ብፁዓን ጳጳሳት የኤውሮጳ ኅብረት መዋቅራዊ ቅዋሜው በሚገባ ቀርበው ሊረዱት ይገባል። እንዲህ በመሆኑም የተካሄደው ግኑኝነት በተጠቀሰው ጉዳይ ሃሳብ እና ተገቢ መረጃ ለማግኘት ያለመ ነበር ብለዋል። በሌላው ረገድም በኅብረት ኤውሮጳ አበይት አካላት እና በግኑኝነት የተሳተፉት ብፁዓን ጳጳሳት መካከል ቀጣይ የሆነ ግኑኝነት እንዲኖር ገፋፍተዋል። የኅብረቱ መዋቅራዊ ቅዋሜው ተገንዝቦ የበላይ አካላቱንም ጭምር በቅርብ አውቆ በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ እንዴት አድርገው ተገቢ ሚና ለመጫወትና አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚችሉ የሚለው ፍላጎት ላይ የጸና ግንዛቤ አሳድሮባቸዋል።
በተካሄደው ግኑኝነትም ምክንያት ብፁዓን ጳጳሳት በኅብረቱ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በቁጥር እጅግ ከፍ ያለው የኅብረቱ የበላይ አካላት በመሳተፋቸውም ብፁዓን ጳጳሳት ለእግዚአብሔር በማኅበራዊ ሥፍራ እንዲሁም ሃይማኖትንም ጭምር ተገቢ ቦታው ሊሰጠው የሚጠይቀው የሰው ልጅ ካለው መንፈሳዊነት ዝንባሌ ለሚገለጠው መሠረታዊ ፍላጎት ማክበር አስፈላጊ መሆኑ የተገለጠበት ወቅት ነበር ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ብፁዕነታቸው ባሰሙት ስብከት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “Caritas in Veritate-ፍቅር በሐቅ” በተሰኘው አዋዲ መልእክት አማካኝነት “እድገት እጃቸውን ወደ ላይ ከፍ የሚያደርጉ ጸላይ ማኅበረ ክርስትያን ያስፈልገዋል” ያሉትን ሃሳብ ማእከል በማረግ፣ የሰው ዘር ከተሞች በመብት እና ግዴታ ላይ በሚጸናው ግኑኝነት የሚመሠረቱ ሳይሆን ምኅረት መደጋገፍ እና ውህደት እንዲሁም በሰው ልጅ ኑባሬ መንፈሳዊ ክብሩ ላይ ጭምር የጸና መሆን አለበተ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.