2012-03-09 13:32:57

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፦ “ኢጣሊያ ለራስ ወዳድነት እና ለግለኝነት አደጋ ተጋልጣለች”


ከትላትና በስትያ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ለአምስት ዓመት ያገለገሉት የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ምክር ቤቱን በሊቀ መንበርነት እንዲመሩት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዳግም መሰየማቸው የገለጠው የቅስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ “የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ የሚሰባሰብበት ዕለተ ሰንበት ያለው ክብር” ማእከል በማድረግ ትላትና ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ የጉባኤ አዳራሽ ከአርባ በላይ የሆኑት ለኢጣልያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባሰሙት ንግግር፣ ቤተ ሰብን ማዳከም ኅብረተሰብን ማናጋት ማለት መሆኑ ገልጠው፣ ኢጣሊያ የተጋረጠባት፣ ሕዝባዊ ርእሰ ቅትለት በማለት የገለጡት የወሊድ ቁርጥ ማነስ፣ ኢጣሊያ ወደ ፊት የማትመለከት እና መጻኢ የምትፈራ አገር መሆንዋ ነው የሚያመለክተው። የወሊድ ቁጥር ማነስ በኢጣሊያ ልቅ ራስ ወዳድነት ‘የርእሰ መጥላት መሠረት’ የሆነው እና ግለኝነት መስፋፋቱን የሚያረጋግጥ ነው ካሉ በኋላ በጠቅላላ የሚታየው ምግባረ ብልሽት ሙስና ግድ የለሽነት ‘ለድኾች አለ ማሰብ’ እየፈጠረው ላለው ብቸኝነት በእውነት አጅግ አሳሳቢ ነው።
ቤተ ሰብ እና የቤተሰብ አባላት የሚያሰባስበው ዕለተ ሰንበትም ይሁን አበይት በዓላት ላለው ክብር ግምት አለ መስጠት እና ሕዝብን ይኸንን ክብር መንፈግ ቤተሰብ ማዳከም እና ኅብረተሰብን ማናጋት ይሆናል ካሉ በኋላ፣ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት የሚከተለው መርሃ ግብር ውስጥ አንዱ ባለው የኤኮኖሚ መቃወስ ሳቢያ ለድኽነት ለተጠቃው ዜጋ ድጋፍ ማቅረብ የሚለውን በማስታወስም፣ የኤኮኖሚ መቃወስ እና የሕንጸት ተጋርዶ ጭምር ለመፍታት ምን መደረግ እንዳለበት በኢጣሊያ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን መሪ ሃሳብ ታቀርባለች እንዳሉ የተካሄደው ጉባኤ የተከታተሉት የቫቲካን ራዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጉዋራሺ ካጠናቀሩ ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.