2012-03-09 13:31:03

በዱብሊን እ.ኤ.አ. ከሰኔ 10 ቀን እስከ ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. 50ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ “ሱታፌ ከእግዚአብሔር ጋር ከሌሎች ለሚኖረው ሱታፌ መሠረት ነው”


በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው ቅዱስ ቁርባን የቤተ ክርስትያን ማሕፀን፣ ወደ ዱብሊን 50ኛው ዓመት የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ በሚል ርእስ ሥር የተደረሰው መጽሐፍ ትላትና እዚህ በቫትካን ረዲዮ ሕንፃ በሚገኘው ማርኮኒ የጉባኤ አዳራሽ ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ የተካሄደው ጉኑኝነት የመሩት ጳጳሳዊ ዓለም አቀፍ ቅዱስ ቁርባን ጉባኤ RealAudioMP3 የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፒየሮ ማሪኒ ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ቁርባን ዙሪያ የሚያሰባስብ ቅዱስ አጋጥሚ መሆኑ በማብራራት፣ ለንባብ የቀረበው መጽሐፍ ከዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ካለው 50ኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ቀድመው የተካሄዱትን ጉባኤዎች ታሪካዊ ገጽታውና ማእከላዊ ሃሳቡንም ጭምር በማካተት የዚሁ ቅዱስ ቁርባን፣ ከክርስቶስ እና በመካከላችን ሱታፌ” የተሰኘው የዱብሊኑ ጉባኤ ርእሰ ጉዳይ በስፋት የሚያብራራ መሆኑ መግለጣቸው የተካሄው ግኑኝነት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አስታውቀዋል።
በዚህ ዓለማዊ መተሳሰር በተረጋገጠበት በምንኖርበት ዓለም የሰው ዘር እርስ በእርሱ እንዲገናኝ ግድ መሆኑም የነበረው እና ያለው የሰው ተገናኝ ባህርዩ የሚያመለክትም ነው። ቅዱስ ቁርባን ይኸንን ጉኑኝነት የሚያስተምረን፣ በክርስቶስ ላይ እምነት ያላቸው የዚህ ግኑኝነት መሠረት ክርስቶስ መሆኑ ተገንዝበው በቅዱስ ቁርባን የሚመሰከር ግኑኑኝነት ይሆናል፣ ክርስትያን አፉን ከፍቶ ቅዱስ ቁርባን ተቀብሎ የሚሄድ ሳይሆን፣ ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት እርሱነቱን በእኛ ውስጥ በማሳደር እኛን የሚለውጥ ሕይወታችንን ከሌሎች ጋር ሱታፌ ለማድረግ የሚያበቃን መሆኑ መታመን ይኖርበታል። የክርስትያን ግኑኝነት ከዚህ ሱታፌ የሚመነጭ እና በዚሁ ሱታፌ የጸና መሆን አለበት፣ ክርስቶሳዊ ሕይወት ለመኖር የሚያበቃን ኃይል ነው። ካሉ በኋላ የዱብሊኑ ጉባኤ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሚያብራራው እና ትርጉም የሰጠበት ሱታፌ በሚለው ሥልጣናዊ የቤተ ክርስትያን ቃለ ማብራሪያ መሠረት የሚያደርግ ነው ካሉ በኋላ፣ የዚህ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ርእሰ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በካናዳ ኪዩበክ የተካሄደው 49ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ መዝጊያ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት ከገለጡት ሃሳብ የተወሰደ ጥቅስ መሆኑ ማብራራታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ገልጠዋል።
የዱብሊን 50ኛው ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ኮሚቴ ዋና ጸሓፊ ክቡር አባ ከቪን ዶራን ይህ የተወሰነው ጉባኤ ለኅዳሴ እና ለለውጥ የሚያነቃቃ ቅዱስ ቁርባን የለወጥ እና ኅዳሴ መሠረት መሆኑ በቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት መሠረት አረጋግጦ የሚያብራራ ነው። ጥንት በኤውሮጳውያን አስፍሆተ ወንጌል የደረሳቸው የተለያዩ ክፍለ አለም ዜጎች ዛሬ ይኽ በእምነቱ የደከመውን ጥንታዊው ክርስትያን ኤውሮጳ ባልተወሳሰበው እምነት ለማጽናት እና ወንጌል ለመመስከር በኤውሮጳ ይገኛሉ፣ በእውነቱ የዚህ ዓይነት ያልተወሳሰበ እምነት በኤውሮጳ ያስፈልጋል፣ የነዚህ ክርስትያን ዜጎች እዚህ መገኘት ለእኛ ያስፈልገናል ሲሉ፣ የዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርባን ኮሚቴ አባል ክቡር አባ ቪቶረ ቦካርዲ፣ ቅዱስ ቁርባን ለሁሉም ሰው ዘር የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ማእከል መሆኑ የሚያበስርና የሚኖር በእግዚአብሔር ፍቅር የተቃጠለ እና ብርቱ ልብ ይሻል እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.