2012-03-05 13:12:55

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ብዙ ቃላት፣ ብዙ ጽሞና”


በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ትላትና ቅዳሜ ጧት የተጠናቀቀው በኪንሻሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞንሰንግዎ ፓሲንያ የተመራው RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና የቅርብ ተባባሪዎች የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ መሥተዳድር ዓበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎች እና ብፁዓን ጳጳሳት የተሳተፉበት በቫቲካን ለአንድ ሳምንት የተካሄደው ሱባኤ “ብዙ ቃላት፣ ብዙ ጽሞና” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስነታቸው የዚህ የዓቢይ ጾም መግቢያ ምክንያት የኖሩት ሱባኤ አስተንትኖ ስብከት ጸጥታ እና ጽሞና የተፈራረቀበት፣ ብዙ ቃላት ብዙ ጽሞና፣ የተደመጠው ቃል በጽሞና አብሰልስሎ የራስ ገጠመኝ በማድረግ እግብር ላይ ለማዋል የሚያነቃቃ መሆኑ አብራርተው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዓለም አቀፍ የመገናኛ ዝቡኃን ዕለት ምክንያት “ጽሞና እና ቃል” በሚል ርእስ ሥር ያስተላለፉት ዓለም አቀፍ መልእክት አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ አስታውሰው፣ ጽሞት ለማዳመጥ ሥፍራ እና ዕድል የሚሰጥ የውስጣዊ መሆን ቅድመ ሁኔታ መሆኑና ሌሎችን እና እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ሁኔታን የሚያዘጋጅ ዕድል ነው ብለዋል።
መልእክቶች እና ማስታወቂያዎች ከተላለፉ በኋላ ለጽሞና ቦታውን በመተው ለሰው ልጅ የመምረጥ ችሎታ እርሱም አስፈላጊው እና የማያስፈልገውን ለመለየት እንዲችል ያግዘዋል። ሆኖም ግን መልእክት በቀጣይነት መቅረብ በዓለማችን የሚይታየው ፋታ የማይሰጥ የዜና እና መግለጫ ውርጅብኝ ለጽሞናው ዕድል የማይሰጥ እየሆነ የሚታላለፈው መልእክት እንዲስተዋል የሚለው ጉዳይ ሳይጤን ይሮጣል፣ ስለዚህ ጥልቅ መልእክት ተከትሎ የሚኖረው እውነተኛው ጽሞና በሕይወታቸው ሥርዓት ለማኖር የሚያበቃ ሁኔታ ከማረጋገጥ ሌላ ሌሎችን በትክክል ለማዳመጥ ጭምር ያበቃናል፣ ጽሞና የሌለው ሕይወት የምንመራ ከሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሞቶ ከሞት ተነሣ የሚለው እውነት እና ይህ እውነት ያለው ብርሃን እንዴት ለመኖር እንችላለን? በሚለው ጥያቄ ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.