2012-03-05 13:15:54

አንድ መቶ ከቫቲካን ውስጣዊ ዝግ መዝገብ ቤት የተወጣጡ ሰነዶች ለትርኢት


የቫቲካን ውስጣዊ ዝግ ቤት መዝገብ የተቋቋመበት 400ኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ከ ስምንተኛው እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ከሚያጠቃልለው ሰነዶች ውስጥ የተወጣጡ 100 ዘነዶች እና መዝገቦች RealAudioMP3 “በሮማ የቫቲካን ውስጣዊ ዝግ መዝገብ ገዛ እራሱን ያቀርባል ያስተዋውቃል” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ሮማ በሚገኘው ካፒቶሊኒ ቤተ መዘክር የሚቀርብ ትርኢት መሆኑም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የሮማ የከተማ ነዋሪዎች ማኅበር ምክር ቤት የባህል ጉዳይ ተጠሪ ኡምበርቶ ብሮኮሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቫቲካን የውስጥ ዝግ ቤተ መዝገብ ከሚያጠቃልላቸው ሰመዝገቦች እና ሰነዶች ውስጥ 100 ሰነዶች ለትርኢት ለማቅረብ የተወጠነው እቅድ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ አስታውሰው፣ ክርስትያናዊት ሮማ በሚያረጋገጠው የሮማ ልደተ ክርስትያናዋን በሚያስታውሰው ሥፍራዎች በሆኑት በካምፒዶሊያ በላተራኖ እና በቅዱስ ጴጥሮስ ሶስት ማእዝኖች ውስጥ በታቀፈው ካፒቶሊኒ ቤተ መዘክር የሚቀርብ በመሆኑም ያለው መልእክት ጥልቅ ነው።
ብራናዎች በጥንት ቀለማት የተጻፉት በጥንት የሥነ ኅትመት አጠቃቀም ለንባብ የበቁት እና ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉት ታሪካዊ እና ጥልቅ የታሪክ መልክት አዘል ሰነዶች በመሆናቸውም፣ ለታሪክ ሊቃውንት ለለምሁራን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ከውስጥ እና ከውጭ ለሚመጡት ጎብኝዎች መስህቦ ነው ካሉ በኋላ ትርኢቱ የእውቀት ብቻ ሳይሆን መንፍሳዊ ገጽታም አለው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.