2012-02-29 13:51:55

ብፁዕ አቡነ ኤተሮቪች፦ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ቤተ ሰብ መሠረት ነው


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 7 ቀን እስከ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን “አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት ሥርጭት (ማስፋፋት)” በሚል ርእስ ሥር የመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ እንዲካሄድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ውሳኔ መሠረት የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጉዳይ የሚከታተለው ጠቅላይ ጽ/ቤት የዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ሲኖዶስ Instrumentum laboris - የውሎ ማስፈጸሚያ ሰነድ ረቂቅ ማእከል RealAudioMP3 በማድረግ በተለያዩ ርእሶች ሥር በማስደገፍ ቅድመ ዝግጅቶች በተለያየ ወቅት ማካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ ባለፉት ቀናት ይህ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽ/ቤት የጠራው 12ኛው መደበኛ ስብሰባ ማካሄዱ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ስለ ተካሄደው ስብሰባ በማስመልከትም የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ኣቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ስብሰባው ከተለያዩ አገሮች ብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤቶች፣ ውስጣዊ የርእሰ መሥተዳድራዊ ሕገ ቀኖና ያላቸው የምሥራቅ ሥርዓት የሚከተሉት በተለያዩ አገሮች የሚገኙት የካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን ሲኖዶሶች የቅድስት መንበር መሥተዳድር እንዲሁም የመላ መንፈሳዊ ማኅበሮች እና ገዳሞች የበላይ አለቆች ኅብረት ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው ሲኖዶስ ርእስ ሥር የቀረበላቸው መጠይቆች በማስደገፍ የሰጡበት መልስ ማእከል በማድረግ ተወያይቶ ጽማሬ ሐሳቡን ለማሳካት እና ሊካሄድ ለተወሰነው የሲኖዶስ ውሎ ማስፈጸሚያ ሰነድ ለማደስ ታልሞ የተካሄደ መሆኑ ከገለጡ በኋላ፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዳግም በጋለ ስሜት መነቃቃት ያለበት በመሆኑ፣ አዲስ የአስፍሆተ ወንጌል ሥልት ማቅረብና በአዲስና በታደሰ አገላለጥ መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ እንዲህ ባለ አዲስ ሥልት አስፍሆተ ወንጌል ክርስትናና ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉትና ያልተቀበሉትን ከቤተ ክርስትያን ርቀው ያሉትን የካቶሊክ እምነት ለማይኖሩት ጭምር እንዲያቀና ለማድረግ ነው ብለዋል። አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስትያን missio ad gentes-ወደ አሕዛብ ተልእኮ እርሱም አይነተኛው እና ልዩ ሓዋርያዊ ተልእኮ እንቅስቃሴ ለማነቃቃትም ነው።
ወቅታዊው አስፍሆተ ወንጌል ብዙውን ጊዜ የማያፈራበት ምክንያት እርሱም በዓለም በመስፋፋት ላይ ያለው ሃይማኖትን እና ከሃይማኖት የሚነጥለው ዓለማዊነት ባህል ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንድ ክርስትያኖች እና በባህርይዋ ቅድስት ለሆነችው ሁላችን ለቅድስና መጠራታችን ለምታስተምረው እና ለምታስገነዝበው ቤተ ክርስትያን አባላት ጭምር የሚሰጡት የክርስትናው ምስክርነት የሚቃረን ምስክርነት ጭምር ነው። ስለዚህ ሁላችን ኃጢአተኞች መሆናችን ታምነን ለውጥ መሻት አለብን። በግልም ይሆኑ በማኅበረ-ሰብኣዊነት ጭምር የመለወጥ አስፈላጊነት ወሳኝ መሆኑ ስብሰባው በማስመር መለወጥ ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ቅድመ ሁኔታ መሆኑ በጥልቀት እንዳሳሰበበትም አብራርተዋል።
በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ እቅድ መሠረት ዘንድሮ ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን፣ በአስፍሆተ ወንጌል ቤተ ሰብ ያለው ልዩ ሥፍራ እና የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መሠረት ነው። ቤተሰብ እምነትን በመኖር እና በማስተላለፉ ተልእኮ የተጠራ ነው። ሆኖም ግን ይህ ጥሪ ብዙውን ጊዜ የተዘነጋ ሆኖ ነው የሚታየው፣ ወላጆች ለልጆቻቸው የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች መሆናቸው ተገንዝበው እምነት በማስተላለፉ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ለመሳተፍ የተጠሩ ናቸው። ስለዚህ ቁምስናዎች ይኸንን የቤተሰብ ጥሪ ማነቃቃት ይኖርባቸዋል፣ ምክንያቱ ቤተ ሰብ የማኅበረ ክርስትያን ማኅበረሰብ ነውና ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ርእሰ ጉዳይ ያደረገ የመላ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ጠቅላይ ሲኖዶስ እንዲካሄድ በጠሩበት ዓመት የሚጀመረው የእምነተ ዓመት ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መሠረት ነው። እምነት አቅጣጫን የምንለይበት የሚያጋጥሙንን ተጋርዶ ጭምር ለመወጣት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ ታዛዥ በመሆን ቅርብና እርቁ ላሉት የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ምሥራች ለማሰማት መሠረት ነው። እምነት ብሶል ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.