2012-02-24 13:51:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ስለ ሞት የሚብሰለሰል አስተሳሰብ በትንሣሴ ላይ ስላለው እምነት ያጎለብታል”።


በላቲን ሥርዓት እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ዕለተ ረቡዕ በራስ ላይ ዓመድ በመነስነስ የሊጡርጊያ ሥርዓት አማካኝነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዘንድሮ ዓቢይ ጾም በይፋ ማስጀመራቸው ሲገለጥ፣ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ.3 ቁ. 19 እግዚአብሔር ለአዳም “…አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና” RealAudioMP3 ሲል የተናገረው ቃል እና የነነዌ ሕዝብ በራስ ላይ አመድ በመነስነስ በጾም እና በጸሎት በግብር የገለጠው የመለወጥ ተግባር ላይ ያነጣጠረ መንፈሳዊነት ለመኖር ቅድመ ሁኔታ የሚፈጥረው የዓቢይ ጾም መግቢያ አብሣሪ ሥነ ሥርዓት ሮማ በሚገኘው በቅዱስት ሳቢና ባሲሊካ በማቅረብ፣ ወደ በዓለ ፋሲካ የሚያሸጋግረን መንፈሳዊ ጉዞ በይፋ አስጀምረዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሳንታ ሳቢና ባሲሊካ ሥዩም ሊቀ ጳጳስት ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ አማካኝነት በራሳቸው ላይ አመድ ከተነሰነሰ በኋላ ቅዱስ አባታችን በሥነ ሥርዓቱ በተሳተፉት ብፁዓን ካርዲናሎች ካህናት እና መናንያን ገዳማውያን ራስ ላይ “አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና” የሚለው ቃል በመድገም ከነሰነሱ በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን እግዚአብሔር አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህ ሲል ለአዳም የተናገረው ቃል፣ አዳም የዘር ኃጢአት ከፈጸመ በኋላ የተናገረው ቃል ሲሆን፣ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የዓቢይ ጾም መግቢያ በራስ ላይ ዓመድ የመነስነስ ሥነ ሥርዓት የሚፈጸምበት ዕለተ ረቡዕ ይኸንን የእግዚብሔር ቃል የሚያስታውስና እግዚአብሔር መርገጫው ከሆነው ከምድር አፈረ ሰውን እንደሠራው የሚያስታውሰን ዓቢይ ቀን መሆኑ አብራርተዋል።
“አመድ የሥነ ፍጥረት ምልክት ነው” በኃጢአት ምክንያት አሉታዊ ለውጥ እንዲያጋጥም ካደረገው ኃጢአት ከመከሰቱ በፊት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የፈጠረበት የሁሉ ማቆሚያ የሆነው መሬት፣ ፍሬው የሚሰጠው የድካም እና የወዝ ክፍያ በመጠየቅ ይሆናል። በአዳም ኃጢአት አምካኝነትም ምድርም ሳትቀር ተነክታለች፣ ምርቷ እና ሃብቷ በነጻ ከመስጠት ተቆጥባ የድካም እና የወዝ ክፍያ የምትጠይቅ ሆና ተለውጣለች፣ ሆኖም ሁሉም ለሕይወት የተከፈተ ቢሆንም የሞት ዕጣ ዕድል ተደቅኖበታል።
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ነጻነትና ነጻነቱ የሚያስከትለውንም ሁሉ የሚያከብር በመሆኑ፣ በሰው ልጅ ኃጢአት አማካኝነት የተጋባው እርግማን፣ የእግዚአብሔር እርግማን በመሆኑ በኃጢአት ሳይሆን የእግዚአብሔር የሆነው በጥልቅ መድኅናዊ ባህርይ አዘል ነው። መድኃኒታዊ ዓላማ አለው በመሆኑም፣ የእግዚአብሔር አሳቢነትና ችሮት የሚያስከትል ነው። እግዚአብሔር ለአዳም “…አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና…” በማለት ፍትኃዊ ቅጣት ሲበይንበት በዚሁ ቅጣት ዘንድ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ በሚለው ቃል የተነገረው ሁኔታ የሚያልፈው የሰው ልጅ ሁኔታ ሥጋ በሚሆነው ቃል አማካኝነት በገዛ እራሱ እንደሚቀበል በማረጋገጥ የድኅነት መንገድ ጭምር ያበሥራል”።
ስለዚህ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በኦሪት ዘፍጥረት የተነገረ መሆኑ የዓቢይ ጾም መግቢያ በራስ ላይ ዓመድ የሚነሰነስበት ሥርዓተ ሊጡርጊያ በሚፈጸምበት ዕለተ ረቡዕ አለ ምክንያት አይደለም የሚያሳስበው። “ለንሥኃ፣ ለትህትና ማቾች መሆናችን በጥልቀት እንድናስተውል የምንጠራበት ዕለት ነው። ሆኖም ይህ ጥሪ ለተስፋ ቀቢጽነት የሚዳርግ ሳይሆን፣ በሟችነታችን ምክንያት ለመገመት እና ለማሰብም የማይቻለንን ከሞት ወዲያ የትንሣኤ በር ለሚከፍትልን ዳግም መንግሥተ ሰማይ ለሚከፍትልን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ቅርበት የምናስተናግድበት ወቅት ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት መለኮታዊ ምህረት በእኛ ሊደርስ ይችላል፣ በሚለው ሃሳብ ላይ በማነጣጠር፣ ነገር ግን በእኛ እንደሚቻል ያደረገው እግዚአብሔር ካለ ኃጢአት በስተቀረ ሰብአዊነታችን በሙላት በተካፈለው በልጁ አማካኝነት፣ መለኮታዊ ምህረቱን ሊያካፍለን ስለ ፈለገ ብቻ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር ገዛ እራሱ የጎላበት ሁኔታ መሆኑ “ያ ከመንግሥተ ሰማያት ቀዳሜ ወላጆቻችን የሆኑትን ያባረረው እግዚአብሔር፣ በኃጢአታችን እጅግ በተጎሳቆለው እና በወደመው ወደ ምንኖርባት መሬት አንድ ልጁን በመላክ እኛ የጠፉት ልጆቹን በንስኃ እና በምኅረቱ ድነን ወደ እውነተኛይቱ አገራችን እንመለስ ዘንድ አንድ ልጁን ልኮልናል” በማለት በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ዳግም የሚሠራው የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በጥልቀት በማብራራት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.