2012-02-20 15:03:49

የሮማኒያ ዜጋ አዲስ ብፁዕ ካርዲናል ሉቻን ሙረሳን ቃል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለካርዲናልነት ማዕርግ ከመረጡዋቸው እና ትላትና ከ22 ብፁዓን ካርዲናሎች ሢመቱን ከቅዱስ አባታችን እጅ ከተቀበሉት 80 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በሮማኒያ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አቢይ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕነታቸው ሉቻን ሙራሰን፣ አገራቸው RealAudioMP3 በኮሙኒዝም ሥርዓት ሥር በነበረችበት ወቅት በሥውር ቲዮሎጊያ አጥንተው ካጠናቀቁ በኋላ እ.ኤ.አ. በ1964 ዓ.ም. በሥውር ማዕርገ ክህነት፣ እ.ኤ.አ. በ1990 ዓ.ም. ሢመተ ጵጵስና ተቀብለው፣ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሮማኒያ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አቢይ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ እንደሾሙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያስታውስ፣ አዲሱ ብፁዕ ካርዲናል ሉቻን ሙረሳን ከሢመተ ካርዲናል ሥነ ሥርዓት ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ ማዕርግ ክብር እና ኃላፊነቱ ሳስብ በእውነቱ የበቃሁኝ ነኝ ብየ መድፈር አልችልም፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለው ኃይል ብቻ ነው የሚያስችለው። እኔ ካህን ለመሆን ብቻ የሚያቃጥል ፍቅር ነበረኝ፣ በቤተሰብ 12 ወንድሞች ነበርን እናቴ ከአሥሩ አንዱ ለቤተ ክርስትያን ስትል ትገልጠው የነበረው ምኞትዋ ይኸው በእኔ በጠራኝ እግዚአብሔር መሠረት ተፈጽሟል። በሕይወቴ ከእግዚአብሔር የተቀበልኩት ዓቢይ ጸጋ ማዕርገ ክህነት ነው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለሢመተ ብፁዕ ካርዲናልነት ከመረጥዋቸው አንዱ መሆኔ በቤተ ክርስትያን በይፋ እንደተነገረ በሮማኒያ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ርክስትያን እና ምእመናን አቢይ የደስታ ምክንያት ሆነ፣ ለሢመተ ካርዲናል መቼም ቢሆን አስቤውም አላውቅም፣ በቅድስት ሮማዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በይፋ ብፅዕና እንዲታወጅላቸው በመጠባበቅ ላይ ያለነው የሮማኒያ የእምነት ሰማእታት ካህናት ብፁዓን ጳጳሳት እና ምእመናን አማላጅነት እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ሁሉን እችላለሁ በማለት በእምነት ለማደግ አብነት ሆነው የመሩዋቸው ወላጆቻቸውን ዘክረው፣ አለ እነርሱ አብነት እምነትን ለመቀበል ባልቻልኩ ነበር፣ ቤተ ሰብ ቀዳሜ ቤተ ክርስትያን መሆንዋ ዘርከው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.