2012-02-20 15:02:27

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “በእምነት እውነት ላይ ጽኑ እማኔ ከሌለን ለሰውን ልጅ ዳግም ወንጌል ለመስበክ አንችልም”።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ትላትና ለ22 ሊቃነ ጳጳሳት ለሢመተ ካርዲናልነት ለመረጡዋቸው በቅዱስ ጴርጥሮስ ባሲሊካ ሢመተ ካርዲናል ከመፈጸማቸው አንድ ቀን ቀደም በማድረግ በአገረ ቫቲካን አዲስ የሲኖዶስ አዳራሽ እንዲከናወን በጠሩት የጸሎትና የአስተንትኖ ቀን ምክንያት “የእምነት እውነት ላይ ጽኑ እማኔ ከሌለን ለሰውን ልጅ ስብከተ ዳግም ወንጌል ፈጽሞ የማይቻል ነው” በሚል ቋኑ ነገር ላይ RealAudioMP3 ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ቃለ አስተንትኖ ከማቅረባቸው ቀደም በማድረግ፣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳሳት ሢመተ ካርዲናል ከሚቀበሉት አንዱ ብፁዕ አቡነ ቲሞቲ ዶላን ትጉ ደስታ እና ጥልቅ መንፈስ የተካነው፣ በመቀጠልም የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሮኖ ፊዚከላ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መሠረት በማድረግ የኢየሱስ ክርስቶስና የእምነት ወቅታዊነት ዳግም በማግኘት በዓለማችን የሚታየው ወቅታዊው የሃይማኖት መሃይምነትን ለማጥፋት በእውነት የታደሰ ትምህርተ ክርስቶስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሲያሳስቡ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቀድመው የቀረቡትን የአስተንትኖ መልእክቶች አንገብጋቢ መሆናቸው በመግለጥ አስተንትኖውን ላቀረቡት በሙሉ ልብ አመስግነው ባሰሙት ሥልጣናዊ ቃለ አስተንትኖ፣ ካለ ምንም መጠራጠር እግዚአብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እውነት ላይ ጽኑ እና ጥልቅ እማኔ ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱም ያለዚያ እውነት ብሶል እንደማይኖርና የትና ወዴት እንደምንሄድም አናውቅም። ይህ እውነት ሲኖር ብቻ ነው፣ ሕይወታችን ሃብታም እና ውብ የሚሆነው። አለዚያ እማኔ በምንም ተአምር ለሕዝበ ዓለም ወንጌልን ዳግም ለመስበክ አንችልም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እውነት በሚሠዋ ፍቅር አማካኝነት ይገለጣል፣ የሚሠዋው ፍቅር በተራውም እውነትን ይገልጣልናል ካሉ በኋላ የእምነት ዓመት ሂደቱ “እውነት በሚሠዋ ፍቅር መንፈስ መኖር” በሚል መሪ ቃል ማጠቃለል የሚቻል ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
በተካሄደው የአስተንትኖ እና የጸሎት ሥነ ሥርዓት 27 ብፁዓን ካርዲላኖች መልእክት ማሰማታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስከተል፣ በተለያየው ክፍለ ዓለም አስፍሆተ ወንጌል የሚገጥሙት እክሎች ላይ በማተኮር፣ ምንም’ኳ ችግር ያለ ቢሆንም በቻይና የክርስትያን ቁጥር ማደግ እንደ አብነት በመዘከር፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ያለው የጋራው ውይይት፣ በህንድ ጸረ ድህነት ያቀናው ትግል እና እክሎቹ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስትያን ያለበት ችግር፣ በላቲን አመሪካ አስፍሆተ ወንጌል የተጋረጠበት ችግር፣ በምዕራቡ ዓለም ከማኅበራዊው ሕይወት ሃይማኖትን የሚነጥል ዓለማዊ/ሥጋዊ ባህርይ ላይ የጸናው ሥነ ምግባርና ትምህርት በሃይማኖት ላይ መመርኰዝ የለበትም የሚለው ኢሃይማኖታዊ ባህል መስፋፋት፣ ለዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ተጋርጦ መሆኑ፣ በጠቅላላ አስፍሆተ ወንጌል የተጋረጠበት ችግር በማብራራት፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝም አስፍሆተ ወንጌል የሚያበረታቱ ትዕይንቶች፣ የተስፋ ምልክቶች የሆኑትን በቤተ ክርስትያን የሚነቃቁ ከተጨባጭ ልምዶች ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዓለም ዓቀፍ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ እንደ አብነት መጠቀሳቸው አስታውቀዋል።
በመጨረሻውም በተካሄደው የአስተንትኖ እና የጸሎት ሥነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን የአዲስ ሕንጸት አንገብጋቢነት፣ የትምህርተ ክርስቶስ ኅዳሴ፣ ለወጣት ትውልድ እምነትን የማስተላለፉ ተግባር፣ የሰባኪ ወንጌል ሕንጸት፣ ወቅታዊው የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ለማመዛዘን በሳል እምነት መሠረት መሆኑ ከተብራ በኋላ ለእምነት ዓመት ማካሄጃ ሃሳቦች ከቀረቡ በኋላም፣ ማኅበረ ክርስትያን ክርስቶስ ማእከል ያደረገው የጋራው እምነት መስካሪዎች እንዲሆኑና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ለሚደረገው የጋራው ውይይት ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቦ፣ የቅዱሳኖች አብነት ቀጣይ ማራኪነቱ በስፋት መብራራቱ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.