2012-02-20 15:14:25

ሶማሊያ፦ ታሪካዊ የፖለቲካዊ ተሃድሶ ስምምነት


በፑንትላንድ የተሰበሰበው የተለያዩ የሶማሊያ የበላይ መሪዎች እልባት ያጣው ከ 20 ዓመት በላይ የሆነው የአገሪቱ ውጥረት አና አልቦ ማእከላዊ መንግሥትነት ጉዳይ መፍትሔ RealAudioMP3 ያሰጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. እፊታችን ሓሙስ የካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በሎንደን ስለ መጪው ሶማሊያ ርእሰ ጉዳይ ያደረገ ሊካሄድ ተወስኖ በእቅድ ተይዞ ካለው ጉባኤ አራት ቀን ቀደም በማድረግ በፑንትላንድ የተሰበሰቡት የአገሪቱ የተለያዩ መሪዎች የአገሪቱ ፖለቲካ ኅዳሴ በሚል በአንድ አዲስ ታሪካዊ የጋራ ስምምነት መድረሳቸው ቢቢሲ የራዲዮ ጣቢያ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።
በዚህ የአገሪቱ ማእከላዊ እና ደቡባዊ ክልል በስፋት ከሚቆጣጠረው የአል ሽባብ ኃይል በስተቀረ ከሶማሊያ ርእሰ ብሔር ሸይክ ሻሪፍ ሸዩክ አህመድ በተጨማሪ የመንግሥት ደጋፊ ታጣቂ ኃይሎችና የሌሎች የተለያዩ ኃይሎች መሪዎች፣ የጋልሙዱግ ገሚስ ራስ ገዛዊ ክልል መንግሥት የበላይ አካላት በተሳተፉበት ጉባኤ የተደረሰው፣ የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኅዳሴ ላይ ያነጣጠረው ስምምነት፣ አቢይ ተስፋ የተጣለበት አገሪቱ ፈደራላዊ ቅርጽ የሚያሰጣት ከመሆኑም ባሻገር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ተሳትፎ 30% መሆን አለበት የሚል ውሳኔ ያካተተ መሆኑም ቢቢሲ ከሰጠው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.