2012-02-18 09:19:31

አገረ ቫቲካን፣ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ


የቅድስት መንበር የአደረጃጀት እና የኤኮኖሚ ጉዳይ ለመወያየት የቅድስት መንበር የአደረጃጀት እና የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት በቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ተመርቶ ሲያካሄድ የሰነበተው የጥናት ጉባኤ ትላትና መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ በዚህ በተካሄደው የጥናት RealAudioMP3 ጉባኤ የቅስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ አስተዳዳሪ፣ ከቀድስት መንበር መስተዳድርና አስተዳዳር ኃላፊነት ለየት ያለ መሆኑ የሚያመለክተው እና ይኸንን በተመለከተ የሚከተለው አዲስ መመሪያ መሠረት ያደረገ የቅድስት መንበር የአደረጃጀት እና የኤኮኖሚ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ያለው አዲስ የኃላፊነት ሚናው በስፋት መብራራቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በተካሄደው ዓውደ ጥናት ምክር ቤቱ የቅድስት መንበርና እንዲሁም የቫቲካን መሥተዳድር እ.ኤ.አ. የ2012 ዓ.ም. የኤኮኖሚ ግምታዊ መርሃ ግብሩ በማስደገፍም ውይይት ተካሂዶ እንዳበቃም፣ ተጋባእያን ብፁዓን ካርዲናሎች በቀረበው እቅድ መርካታቸው እና አስተማማኝ መሆኑ በመግለጥ፣ ሆኖም ግን ወቅታዊው የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ቀውስ በሁሉም አገሮች የኤኮኖሚ ችግር ማስከተሉንም በማስታወስ፣ የቅድስት መንበር የኤኮኖሚው ምንጭ ከመላ ዓለም ምእመናን በነጻነት የሚሰጠው ምጽዋት መሆኑ ብፁዓን ካርዲናሎች ዘክረው፣ የኤኮኖሚው ቀውስ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ለተደረገው ጥረት መሠረት በመሆኑም ለመላ ዓለም ካቶሊካውያን ምእመናን ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻውም በአሁኑ ወቅት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመንካት እና ለአደጋ ለማጋለጥ ታልሞ ስማቸውን በማይገልጡት አካላት አማካኝነት በመነዛት ላይ ያሉትን ዜናዎች በማስታወስ፣ ይኽ አሉ ባልታ በእውነቱ የቤተ ክርስትያን እና የመሪዋ ተልእኮ የማያናጋ መሆኑም የኵላዊት ቤተ ክርስትያን መልካሙ ተግባር ምስክር ነው ካሉ በኋላ፣ የቅድስት መንበር ንብረት የማስተዳዳሩ ሂደት በበለጠ እንዲሻሻል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ በማስመር፣ ሁሉም በተሰጠው የአገልግሎት ኃላፊነት እንዲተጋ በሚያሳስብ ጥሪ ዓወደ ጥናቱን እንዳጠናቀቁ የቅስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.