2012-02-08 16:33:30

መልዕክተ ጦም ር ሊ ጳ በነዲክት 16ኛ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳጳሳት በነዲክት ፡ መልእክተ ጾም አስተላልፈዋል።

ቅድስነታቸው ባስተላለፉት የጾም መልእክት እንዳመለከቱት፡ ሰናየ ሰናይ መኖሩ እና ድል እንደሚቀዳጅ በኀይለ ቃል መነገር አለበት ።

በፍቅር እና በሰናይ ተግባራት ሁሉ እርስ በርሳችን መተባበርና መተጋገዝ አለብን የተሰየመው የበነዲክት የጾም መልእክት ፡ጦም ማለት ከሁሉም እኩይ ነገራት መገታት ማለት እንደሆነ እና ክርስትይናዊ ሕይወት ከልብ ማስተንተን ማለት እንደሆነ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ መሆኑ መልእክቱ አስገንዝበዋል።

ጾም በጸሎት እና ዝምታ ተሸኝቶ ከተደረገ በእርግጥ እምነት ያሳድሳል ደስታ ይፈጥራል ለብርሃነ ትንሳኤውው ፈር ይከፍታል በማለት የቅዱስ አባታችን በነዲክት 16ኛ የጦም መልእክት ያመለክታል።

የወቅቱ ባህል ሰናይ እና እኩይ ነገር ለመለየት ያጣ የራስ ወዳድነት ባህል እየነገሰ በሚሄድበት በአሁኑ ግዜ ክርስትያናዊ እምነታችን የምናሳድስበት ግዜ እንደሆነም የቅድስነታቸው ጾመ መልእክት ይገልጻል ።

የክርስትያኖች ክርስትናዊ መንፈሳዊ አቋም እየደበዘዘ በሚታይበት ወቅት ጦም እና ጸሎት በበለጠ መደረግ ያለበት እንደሆነም ነው የበነዲክት 16ኛ መልእክተ ጾም ማሳሰቡ መልእክት ጾመ ያሰራጨ ክፍለ ማኅተም ቫቲካን ዘግበዋል ።

የአሁኑ ዓለም አቀፍ ሕብረተ ሰብ የሕይወት መንፈሳዊ እና ግብረ ገባዊ አስፈላጊነት ውድቅ እያደረገ እንደሚታይ እና ስለዚም ጸሎት ጾም ምጽዋት መቻር እና አስተንትኖ እንዲደረግ የቅድስነታቸው መልእክተ ጾም ጠይቀዋል።

ይሁን እና የበነዲክት 16ኛ የጦም መልእክት ይፋ እንደሆነ በቅድስት መንበር የኮር ኡኑም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምኽር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ እንዳመልከቱት ፡ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ እና የፋንናስ ቀውስ በተከስተበት በአሁኑ ወቅት የቀውሱ መንስኤ ወደ ጐን በመተው ገንዘብ ለመካበት የሚድረገው እሽቅድድም አስፈሪ መሆኑ እና የሰው ልጅ ሞራል እንዲኖረው እና የመተባበር ባህል እንድያበልጽግ በሚጠበቅበት በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስትያን በጦም እና ጸሎት ትጠመዳለች።

በሌላ በኩል ይላሉ በቅድስት መንበር የኮር ኡኑም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ብጹዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ያለው አለው የሌለው የለውም በሚል ፈሊጥ እየተካሄደ ያለውን ሥርዓተ ኤኮኖሚ እንደምትቅዋም እና በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚላስ የሚበላ አጥቶ የርሃብ ሰለባ ሲሆን ዝም ማለት አትችልም።

ፍትሕ አልባነት እና ራስ ወዳድነት የሚከስተው ከእግዚአብሔር ፈጠሪ ኩሉ ዓለም በመራቅ እና ከሃሌ ኩሉነቱን በመካድ እምንደሆነም ብጽዕነታቸው አክለው አመልክተዋል።

እግዚአብሔርን ከማሕበራዊ እና ኤኮኖምያዊ ሕይወት ማስወገድ እንዳማይቻል የጠቀሱ ብጹዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ ፡ ከመለኮታዊ እና ተፈጥሮአዊ ሕጎች መሸሽ እንደምያቻል አመልልክተው እግዚአብሔር ከሰው ዕውቀት በላይ መሆኑ የሰው ልጆች ልብ ማለት እንደሚጠበቅባቸው አስምረውበታል።

በማያያዝም ብጹዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራህ የቤተ ክርስትያን ተፈጥሮአዊ እና ሐዋርያዊ ተልእኮ የሰው ልጅን በስጋ በነፍስ መንከባከብ በእግዚአብሔር ታግዞ በብርሃኑ ታጅቦ ፍትሕ ሰላም እና ምሕረት እንድያገኝ ነው ብለዋል ።

በሌላ በኩል የኮር ኡኑም ማለትም የተወሃሃደ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጽሐፊ ብጹዕ አቡነ ሰጉንዶ ተጃዶ ሙኞስ ክርስትያኖች ሁሉ በማሕበራዊ ቀውሶች ለተጐዱ ሁሉ ለመርዳት የርዳታ እጃቸው እንዲዘረጉ ተማጥነው ፡

እኤአ በ2010 በመሬት መናወጥ በተጐዳችው ሃዪቲ ደሴት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ በቻሩት ገንዘብ አንድ ትምህርት ቤት እና የቁምስና ማእከል እየተሰራ መሆኑ እና ይህንኑ ለመታዘብ በሳምንቱ መጨረሳ ወደ ሃዪቲ ደሴት እንደምያመሩ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.