2012-02-07 13:47:47

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ታማኝነት እና ግልጽነት”።


ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል ትላትና “ታማኝነት እና ግልጽነት” በሚል ርእስ ሥር፣ በአንዳንድ ጥቂት የወሉደ ክህነት አባላት አማካኝነት በሕፃናት ላይ የተፈጸመው የግብረ ሥጋ ዓመጽ ጨርሶ እንዲወገድ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቆራጥ ውሳኔ እና ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሠረት ኵላዊት ቤተ ክርስትያን የምተፈጽመው ያልታከተ ጥረት እና ትግል “ታማኝነት እና ግልጽነት” ላይ ያነጣጠረ ሰው የቅድስት ሥላሴ አርአያ እና አምሳያ ነው ከሚለው ቲዮሎጊያዊ ሥነ ሰብእ ጥናት እማኔ የመነጨ መሆኑ በማብራራት፣ ምንም’ኳ ከጠቅላይ መነሻ ወደ ልዩ መደምደሚያ የሚከተለው አመለካከት መሠረት አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት በግብረ ሥጋ አመጽ መሠረት በቫቲካን እና በቅድስት መንበር ላይ የተሰነዘረው ወቀሳ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በወንጌላውያን መመዘኛዎች ላይ በጸናው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ መሪነት ሥር ወንጌላውያን መሠርት ያላቸው እሴቶች ላይ ጸንታ የምትሰጠው ምስክርነት ደምቆ እንዲታይ እና ያላት ግብረ ገባዊ ኃላፊነት ለማረጋገጥ እና ለመኖር ያላት ፈቃድ የሚያረጋግጥ ነው።
ቅዱስ አባታችን በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ግልጽነት እና ታማኝነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ውሳኔዎች ከማረጋገጥ ወደ ኋላ እንዳላሉ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ሲያመለክቱ፣ ቅዱስ አባታችን በተለያዩ አገሮች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የግብረ ሥጋ ዓመጽ ለመዋጋት፣ የዓመጹ ሰለባ የሆኑትን የተሟላ ድጋፍ በማቅረብ፣ ተጠያቂዎችንም በውሳኔ ሕግ እና በሥነ አእምሮ ድጋፍ በማቅረብ፣ የዚህ አሰቃቂው ችግር መንስኤ በጥልቀት በመለየት፣ ችግሩን አውቆ የቀድሞ መጠንቀቅ ማስፈጸሚያዎችን በማቅረብ የምታካሄደው ትግል ፈር ያስያዙ ናቸው ብለዋል።
በሌላው ረገድ ቅድስት መንበር የወንጀል ቡድኖች የገንዘብ ሃብት ሕገ ወጣዊ አሻራውን ለመሰወር በተለያየ ጤነኛ የኤክኖሚ አውታር ለማዋል የሚያደርጉት ጥረት ለመቆጣጠር እና የገንዘብ ሃብት በሕገ ወጥ ተግባር እንዳይውል ከየት ወዴት እንቅስቃሴውን ግልጽነት እና ሕጋዊ ክትትል መሠረት ለማሳየል የሚደረገው ጥረት በመደገፍ የወሰደቸው ውሳኔ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ አስታውሰው፣ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴ ግልጽ እና ዋስትና ያለው ታማኝ እና አስተማማኝ ነው፣ ምንም’ኳ የሚካሄደው ጸረ የክፋት መንፈስ ትግል ረዥም እና አስቸጋሪ ቢመስልም፣ በእግዚአብሔር ኃይል ድጋፍ አማካኝነት በግልጽ እና በቆራጥ ፍላጎት የሚቻል ነው። ይህ ደግሞ ለምትጠው ወንጌላዊ ምሥክርነት ዋስትና ነው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.