2012-02-07 13:46:22

ወደ ፈውስ እና ተኃድሶ


ሮማ በቫቲካን ራስ ገዛዊ ክልል በሚገኘው ጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ እስከ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚዘልቅ በአንዳንድ ጥቂት የውሉደ ክህነት አባላት በሕፃናት ላይ የተፈጸመው በደል በጥልቀት የሚመረምር፣ ቤተ ክርስትያን ኃላፊነት የተሞላው በሓዋርያዊ ሕግ መሠረት እንዲሁም የሰብአዊ መንፍሳዊ ሕንጸት እቅድ መሠረት የሰጠው ምላሽ የሚያጎላ፣ የሕፃናት ሰብአዊ መብት እና ክብር ለመከላከል ቤተ ክርስትያን በዚህ ዓላማ የምትሰጠው ቀዳሚው ትኵረት በማረጋገጥ ይኽ ኣገልግሎት በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት በደል አማካኝነት እንዳደበዝዝ “ወደ ፈውስ እና ተኃድሶ” በሚል ርእስ ሥር ከተለያዩ 110 አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የተወጣጡ ልኡካን ዓሥር ብፁዓን ካርዲናሎች የ 30 መንፍሳዊ ማኅበራት እና የኃዋርያዊ አገልግሎት ማኅበሮች ጠቅላይ አለቆች እና 40 የሥነ አእምሮ ሊቃውንት እና የሥነ አእምሮ ሕክምና ሊቃውንት የሚሳተፉበት ዓወደ ጥናት ትላንትና እ.ኤ.አ. ከየካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም. መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለክተ።
የኵላዊት ቤተ ክርስትያን የእምነት ዓንቀጽ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር የሕግ ጉዳይ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ስቺሉና በቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በቅድሚያ በደሉን ለይቶ የችግሩ ትርጉም በጥልቀት ከመረዳት የመነጨ መፍትሔ እንዲሰጥበት የሚያግዝ ሆኖ፣ በቀላልሉ በተለያዩ አደጋዎች ሊነኩ የሚችሉትን ሕፃናት እና የወሲብ አመጽ ሰለባ ለሆኑት ሕፃናት የምትሰጠው ጥበቃ፣ የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚ ዓላማ መሆኑ ለማረጋገጥ ያለመ ይህ ዓወደ ጥናት፣ በሕፃናት ላይ ለሚፈጸመው በደል ለይቶ የሕፃናት ሰብአዊ ክብር ጥበቃ ለማሳየል ብሎም በደሉ ለደረሰባቸው ተገቢ መንፈሳዊ ሥነ አእምሮአዊ እና ሰብአዊ ሕንጸት በማቅረብ ረገድ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው የተሟላ ድጋፍ በመመስከር የሚያረጋግጥ መሆኑ አብራርተዋል።
በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክልፍ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የዓወደ ጥናቱ ፍጻሜ ዓወደ ጥናቱ ሳይሆን፣ አሰቃቂው በደል በጥልቀት መርምሮ መፍትሔ እንዲያገኝ ለሚደረገው ጥረት ሥልት ላይ ያነጣጠረ ነው። ይህ የሚካሄደው ዓወደ ጥናት የበደሉ ሰለባ የሆኑት ሕፃናት ማእከል ያደረገ በመሆኑ፣ በሕፃና ላይ በደሉን ያደረሰው የውሉደ ክህነት አባል የፈጸመው ወንጀል ከባድ መሆኑ ለማሳሰብ እና ቅድስት ቤተ ክርስትያን የተሰጣት የመልካም እረኛ የኃላፊነት ተልእኮ ተሳታፊ የሆኑት የውሉደ ክህነት አባላት ያለባቸው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ኃላፊነት ከባድ መሆኑ በጥልቀት የሚያስገነዝብም ነው።
ይኸንን ዓወደ ጥናት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የእምንት ዓንቀጽ ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለቫዳ ባሰሙት ንግግር በይፋ የተጀመረም ሲሆን፣ የዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ለእያንዳንዱ አገር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስለ ጉዳይ የአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ ግምት የሚሰጥ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡበተ የሚያሳስብ ውሳኔ የሠፈረበት ሰነድ ላይ እንዳተኮርም ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ የበደሉ ሰለባ ስለ ሆኑት እና ስለ ተጠያቂዎች የውሉደ ክህነተ አባላት ጉዳይ በተመለከተ ባጠቃላይ በሕፃናት ላይ ስለ ሚፈጸመው የግብረ ሥጋ አመጽ ሥነ አእምሮአዊ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ዘርፉ ላይ ያተኮረ ሰፊ ማብራሪያ የሚሰጡ ሊቃውንት እና ምሁራን የሚሳተፉበት በመሆኑም፣ እነዚህ ሊቃውንት በሰበካዎች እና በተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት ለቤተ ክርስትያን የሚሰጡት አገልግሎት ምን እንደሚመስል ጥልቅ ማብራሪያ የሚሰጥበትም ነው።
ብፁዕ ካርዲናል ለቫዳ በቅርቡ ከጠቅላላ የእስያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በታይላድ ቀጥለውም ከጠቅላላ የላቲን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር በብራዚል ተገናኝተው ስለ ጉዳይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ውሳኔ መሠረት በማድረግ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ስቺሉና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጠው አክለውም በዚህ የሦስት ቀናት ዓወደ ጥናት የእርቅ እና የምኀረት መሠረት የሆነው የንሥኃ ሥርዓተ ጸሎት እንደሚከናወንም አብራርተዋል።
የዚህ ዓወደ ጥናታ አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር በጳጳሳዊ መንበር ጥበብ የሥነ አእምሮ ዘርፈ ጥናት ተጠሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ሃንስ ዞልነር ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የወሲብ አመጽ ሰለባ የሆኑት፣ አመጹ ጥሎባቸው ባለፈው ጠባሳ ተጽእኖ የወሰዱት እርምጃ በደፈናው መፍትሔ ነው ብሎ ለመናገር የማይቻል ነው። ስለዚህ አመጹ ያሳደረባቸው ሥነ አእምሮአዊ ተጽእኖ ላይ በማተኮር ከዚህ ተጽእኖ ነጻ እንዲሆኑ የተሟላ አገልግሎት ማቅረብ፣ በዚህ የልጆችዋ ኃጢኣት ለደማችው ቤተ ክርስትያን ለመደገፍ እና ይህ ዓይነቱ አደገኛው ችግር ለመፍታት በምታደርገው ጥረት ደግፍ ለማቅረብ እነሆኝ ያሉ የቀድሞ አመጹ ሰለባ የሆኑት ለእርቅ እና ምኅረት የተሰማሩም እንዳሉም በአውደ ጥናቱ ተገኝተው ምስክርነት የሚሰጡ አሉ፣ ስለዚህ ችግሩ እንዳለ ተገንዝቦ የመገንዘቡ ሂደት ጥልቅ በማድረግ የጥሪ ጸጋ የሚቀበሉ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የወቅቱ ባህል ግምት የሚሰጥ የተሟላ ሕንጸት በመስጠት ከወዲሁ የሚሰጣቸው ኃላፊነት ከባድ መሆኑ ተገንዝበው እንዲታነጹ ሥነ አእምሮአዊ ዝንባሌያቸው በማጤን ድጋፍ ማቅረብ ለሚለው ዓላማ ትኵረት የሚሰጥ እና የሚያሳብ ዓወደ ጥናት ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.