2012-02-06 14:51:09

ያለውን ክፋት ለማሸነፍ ያለን ብቸኛ መልስ በእግዚአብሔር ፍቅር እምነት ማሳደር ነው፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእኩለ ቀን ከምእመናንና ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮ ነው፣ ቅዱስነታቸው አያይዘውም በዕለቱ ለሚታወሰው የሕይወት ዕለትና እፊታችን ቅዳሜ በሉርድ በተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ጋር በሚዘከረው የሕመምተኞች ቀን በሚመለክትም ተናግረዋል፣
ቅዱስነታቸው ያቀረቡት አስተምህሮ የሚከተለው ነው። ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ የዛሬ እኁድ ወንጌል። ኢየሱስ ሕመምተኞችን እንደፈወሰ ይነግረናል፣ በመጀመርያ የሚያቀርብልን የስምዖን ጴጥሮስ አማችን ነው። የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት። ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው፣ ከዛም በቅፍርናሆም በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ (ማር 1፤34)፣
አራቱ ወንጌላውያን በኅብረት የሚመሰክሩት ጌታ ኢየሱስ ሕዝባዊ ተልእኮውን ያካናውንበት የነበረ አገባብ ከሕመም በመፈወስና ከአጋንንት ነጻ በመውጣት በየቦታውም ትምህርት በማስተማር መሆኑን ነው። ሕመሞቹ የሚያመልክቱት በዓለምና በሰው ልጅ ጸላኤ ሠናያት እየሰራ መሆንን ሲያመለክት ከሕመም መፈወስ ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ራሱ እግዚአብሔር ለሰው ልጅና ለዓለም ቅርብ ሆኖ እየሠራ መሆኑን ያመልክታትል። ጌታ ኢየሱስ ክፋትን ከሥሩ ለማሸነፍ ነው የመጣው፣ ሕመምተኞቹን መፈወሱ ደግሞ ሞትን አሸንፎ በትንሣኤ የተቀዳጀው ድል መጀመርያ ነው።
አንድ ቀን ኢየሱስ “ሕመምተኞች እንጂ ጤናማዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ” (ማር 2፤17) ብለዋል። በዛኛው አጋጣሚ ሊጠራቸውና ሊያድናቸው የመጣላቸው ኃጢኣተኞችን ያመለክታል። ሕመም የሰው ልጅ ዋና ሁኔታ መሆኑንና ራሳችን የማንችል የሌላ እርዳታ እንደሚያስፈልገን ግን ግልጥ ነው። በዚህ አጋጣሚ ተጻራሪ አባባል በመጠቀም ሕመም የሌሎች ቀልብ ለመሳብ የምንጠቀምበት ወይም ስለሌሎች ለመንከባከብ የምናስብበት የጤና አጋጣሚ ነው ለማለት እንችላለን! ያም ሆኖ ይህ ግን የሕመም ግዜ ለረዘም ያለ ግዜ የምቆይና ከባድ የፈተና ግዜ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ከሕመሙ መዳን ተሎ ካልተከናወነ ሥቃዩም የረዘመ እንደሆነ ብቻችን የተተውንና ጫና የበዛብን ሆኖ ሊሰማን ይችላል፣ በዚህም ኑሮአችን ከባድ ሊሆን ይችላል። ለሚሰነዝርብን የክፋት ጥቃት እንዴት አድርገን እርምጃ ለመውሰድ እንችላለን? በእርግጥ ተገቢ ሕክምና በማድረግ፣ እግዚአብሔር ይመስገን በዚሁ ዘመናችን መድኃኒት ጥሩ ግሥጋሴ አድርገ አለና። ሆኖም ግን የእግዚአብሔር ቃል ይህንን የሕመም ጥቃት መቃወም የምንችልበት ወሳኝና ጥልቅ የሆነ መንገድ እንዳለ እርሱም በእግዚአብሔርና በርኅራኄ ማኖር ያለብን እምነት መሆኑን ያስተምረናል። ኢየሱስ ከሕመም ለፈወሳቸው ሰዎች ደጋግሞ ይነግራቸው ነበር፣ “እምነት አዳነችህ” (ማር 5፤34-36) ይላቸው ነበር። እምነት በሰብአዊ አስተሳሰብ የማይቻለውን የሞት ነገር እንኳ ሊያሸንፍ ይችለል። በምን ማመን አለብን? አጠር ያለ መልሱ በእግዚአብሔር ፍቅር ነው። እውነተኛ መልስ ይህ ነው፣ ክፋትን ከሥር ነቅሎ የሚያሸንፍ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ኢየሱስ ክፉ ጠላቱን ሲጋፈጥ ከአባቱ በመጣው የፍቅር ኃይል እንዳሸነፈ እኛም ከሕመም የሚመጣንን ፈተና ልባችንን ለሰፊው የእግዚአብሔር ፍቅር ክፍት በማድረግ ልናሸንፍ እንችላለን። ብዙ ሰዎች ብርቱ ሥቃይ እንዳሸነፉ እናውቃለን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ጥልቅ የሆነ ሰላም ይሰጣቸዋልና። በቅርቡ ብፅዕናዋን ያውጅነው የብፅዕት ክያራ ባዳኖ አብነት ስናስብ ገና በወጣት ዕድሜዋ መውጫ በሌለው ሕመም ተለከፈች፣ ሊጎበኝዋት ይሄዱ የነበር ሁላቸው ከእርስዋ ብርሃንና መተማመን ያገኙ ነበር። በሕመም ግዜ ሕመምተኛውን ለማጽናናት የሌሎች ሰዎች መጠየቅና አጠገባችን መሆን ማለትም ሰላማዊና ንፁሕ የሆነ ቅርበት ከቃላት ይበልጥ ያስፈልገናል።።
ውድ ጓደኞቼ፤ እፊታችን ቅዳሜ እ.አ.አ የካቲት 11 ቀን የሉርድ ብፅዕት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል ዓለም አቀፍ የሕመምተኞች ቀን ነው፣ እኛም በኢየሱስ ዘመን ሕዝቡ ያደርገው እንደነበረ ሕመምተኞችን ኢየሱስ ሊያድናቸው እንደሚፈልግና እንደሚያድናቸው በማመን በመንፈስ ወደ እርሱ እናቅርባቸው። በታላቅ ሥቃይ የሚገኝትንና ምንም ረዳት የሌላቸው ለእመቤታችን ድንግል ማርያም እናማጥናቸው፣ የሕመምተኞች ጤና የሆንሽ ማርያም ለምኚልን፣
ዛሬ በጣልያን አገር ሕይወትን ከፅንስ ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ለመከላከል የሕይወት ቀን ይከበራል። በዚሁ ዓመት የጳጳሳት መልእክት “ወጣቶች ለሕይወት ባህል ክፍት ይሁኑ” የሚል ርእስ መርጠዋል። ከጣልያን አገር የነፍሳት እረኞች ጋር በማበር እውነተኛ ወጣትነት ሕይወትን በመቀበል በማፍቀርና በማገልገል የቆመ ነው። ለማለት እወዳለሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.