2012-02-06 09:51:08

የኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ ፡


የዩናይትድ ስቴትስ ካቶሊካውያን ብጹዓን ጳጳሳት እዚህ ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድሊሚና ማለት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን ትናትና በከፊል የሀገሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ጳጳሳት ከቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር መገናኘታቸው የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እና ብጹዓን ጳጳሳቱ የዩኤስ አመሪካ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ወቃታዊ ሁኔታ ትኩረት በሰጠ ርእሰ ጉዳይ መወያየታቸው መገናኛ ብዙኀኑ አመልክተዋል ።

በነዚህ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ መሠረት በነዲክት 16ኛ እና የዩኤስ አመሪካ ብጹዓን ጳጳሳት የዋሺንግቶን አስተዳደር በቅርቡ ካቶሊካውያን ጨምሮ ጠቅላላ የሀገሪቱ የሕክምና ተቋሞች ከፊታችን ዓመት ጀምሮ ጽንስ ማስወረጃ መድኅኒት እንድያቀርቡ ያሳለፈው ውሳኔ በተመለከተ ሐሳብ ተለዋውጠዋል ።

የዩናይትድ ስቴትስ አመሪካ ጳጳሳት የዋሺንግቶን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሕክምና ተቋሞች ያስተላለፈው ውሳኔ እንደተቃወሙት በግዜው ተመልክቶ መኖሩ የሚታወስ ነው ።

ይሁን እና በዩናይትድ ስቴትስ የኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ ስለዚሁ ጉዳይ በቫቲካን ራድዮ የእንግልዝኛ ፕሮግራም ባለሙያ አስተያየታቸው እንዲሰጡ ተጠይቀው ሲመልሱ ፡ የዩኤስ አመሪካ የሕክምና ተቋሞች ጽንስ ማስወረጃ መድኀኒት እንድያቀርቡ ውሳኔ ሲሰጥ ይህ የመጀመርያ ግዜ መሆኑ ነው እና ፡ እኛ እንደ የእግዚአብሔር ሰዎች ከምእምናን አብረን ውሳኔውን መቃወም ይጠብቅብናል መቃወም አለብንም ።

የኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ አያይዘው ፡ እኛ ማለት የዩኤስ አመሪካ ካቶሊካውያን የዩናይትድ ስቴትስ አመሪካ ህዝቦች የገዛ ራስን ዕድል በገዛ ራስ የመወሰን መብት ፡ በፍትሕ እና በነጻነት ላይ የተመሠረቱ ናቸው ብለን ነበር የምናምነው የዋሺንግቶን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሕክምና ተቋሞች ያሳለፈ ውሳኔ ግን ይህን የሚጻረር ሆኖ ተገኝተዋል ይላሉ ።

በፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የሚመራ የዩኤስ አመሪካ መንግስት የሀገሪቱ የሕክምና ተቋሞች የጽንስ ማስወረጃ መድኀኒት ማቅረብ ይችላሉ ብሎ ላስተላለፈው እና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አቋም ተቀባይነት የሌለው አቋም በመሆኑ የዩኤስ አመሪካ ካቶሊካውያን ተቃውሞ ምን ይመስላል በማለት የስራ ባልደረባችን ክሪስቶፈር አልትየሪ ለኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ለብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ ጠይቅዋቸው ሲመለሱ ፡

እኔ ሁል ግዜ እንደሚለው እና እንደማምነው ከመንግስት ጋር መወያየት አለብን በጋርዮሽ መልካም እና ክፉ መለየት መቻል ይኖርብናል እና ደግሞ እንደመነኮሳን እና መነኩስያት መጸለይ ይገባናል ። የዩኤስ አመሪካ ቤተ ክርትስያን አክራሪ የሆነ አቋም አትወስድም ይላሉ ።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ ሕልናችን እንድናጠፋ ልጠይቁን አይችሉም ያሉት የኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ ህልናችን በኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ነው ፡ ሞራል አልባ የሆነ የመንግስት ውሳኔ እንደማንቀበል ላሰምርበት እወዳለሁኝ ማለታቸውም ተዘግበዋል።

የተከሰተው ችግር በተመለከተ ቤተ ክርስትያን ከመንግስት ጋር ለመውያየት ዝግጁ እንደሆነችም አክለው ገልጸዋል ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ ።በማያያዝም የዩኤስ አመሪካ ህዝቦች የኛ አቋም እንዲላበሱ የእምነታችን አጋር እንዲሆኑ እንጠይቅም ይህ የህሊና ጉዳይ ነው ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች እና በየሕክምና ቤቱ ጽንስ ማስወረጃ ይሸጥ ይሰጥ ማለት ግን ስህተት መሆኑ የሚረዱ ሰዎች ግን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የኛ አቋም ይደግፋሉ ማለት እንደሆነ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል ማለታቸው ታውቆዋል።

በቫቲካን ቪሲታ አድ ሊሚና ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ከሚገኙ የዩኤስ አመሪካ ካቶሊካውያን ብጹዓን ጳጳሳት ተሳታፊ የሆኑ የኒው ኦርሊንስ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ግረጎሪ አይሞንድ እንደገለጹት ፡ እምነትህ በቤትህ እና ቤተ ክርስትያን ውስጥ ንሩበት ከዛ ውጭ ግን እንዴት እንደምትኖር መንግስት የሚሰጠውን መምርያ ተከተል ብሎ የለም ተቀባይነትም የለውም ።

ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ በዓለም ዙርያ የሚገኙ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአምስት ዓመታት እንድ ግዜ ቫቲካን እንደሚጐበኙ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምሰሶዎች የቅዱሳን ጰጥሮስ ወ ጳውሎስ መቃብሮች እንደሚሳለሙ አብያተ ክርስትያኖቻቸው በተመለከተ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንደሚወያዩ አይዝነጋም።








All the contents on this site are copyrighted ©.