2012-01-27 13:40:55

የኤወሮጳ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት፥ “ስለ እግዚአብሔር ጥያቄ ለወቅታዊው ኅብረተሰብ መልስ መስጠት”


በዚህ ለቤተ ክርስትያን እና ለማኅበረሰብ ዘርፈ ብዙ ቀውስ ተጋርጦበት ባለው በአሁኑ ወቅት የኦርቶዶክስ የፕሮተስታንት እና የአንግሊካን አቢያተ ክርስትያን የሚያቅፈው የመላ ኤውሮጳ RealAudioMP3 አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ኮሚቴ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ትላትና እ.ኤ.አ. ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በጀነቭ “ስለ እግዚአብሔር ጥያቄ ለወቅታዊው ኅብረተሰብ መልስ መስጠት” በሚል ርእስ ሥር ዓመታዊ ጉባኤ መጀመሩ ሲገለጥ፣ የመላ ኤውሮጳ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አዲስ ዋና ጸሐፍ ኣባ ዱአርተ ኑኖ ኲየርዞ ደ ባርሶስ ዳ ኩኛ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት ዓለማችን የተጋረጠበት የኤኮኖሚ ቀውስ ብቻ ሳይሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንዳሉትም የእምነት ቀውስ ብሎም የባህል ቀውስ ጭምር ነው ያሉትን ህሳብ የኤውሮጳ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ጉባኤ እና የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት አቢይ ግምት በመስጠት በዚህ በእግዚአብሔር መጠማት እጅግ በተጠቃው ለዚህ ክርስቶስ እጅግ ለሚያስፈልገው ዓለም የክርስቶስ ወንጌል ለማበሠር የሚያስችለው መንገድ በጋራ ለመቀየስ ታቅዶ የተዘጋጀ ስብሰባ ነው። በእግዚአብሔር ዙሪያ የሚቀርበው ጥያቄ፣ ስለ ሰው ልጅ እና ስለ ኅልውና ለሚቀርበው ጥያቄ መልስ በመሆኑም ከእግዚአብሔር ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ እንዲቻል በዓለም የሚከሰተው ዘርፈ ብዙ ቀውስ በጠባቡ መመልከት ሳይሆን፣ መሠረቱ በትክክል መለየት ያስፈልጋል። ስለዚህ “ስለ እግዚአብሔር ጥያቄ ለወቅታዊው ኅብረተሰብ መልስ መስጠት” መፍትሔ መሆኑ በተለያየ መልኩ የሚያረጋግጥ ስብሰባ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.