2012-01-27 13:38:17

ቅድስት መንበርና የተባበሩት መንግሥታት የጸረ ወንጀል ውሳኔ


ዓለም አቀፍ የአሸባሪያን የገንዘብ ኃብት ወንጀል ለመዋጋት እ.ኤ.አ. በ 1999 ዓ.ም. በኔው ዮርክ የጸደቀው ውሳኔ፣ በ 2000 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት በኢጣሊያ ፓሌርሞ ከተማ የወንጀል ቡድኖች የገንዘብ ሃብት ዝውውር ለመግታት ያጸደቀው የውሳኔ ሰነድ ከሚያጠቃልላቸው አንዳንድ RealAudioMP3 ውሳኔዎች ቅድስት መንበር ተቀባይነቱ በማረጋገጥ እንደምትከተለውና በቪየና እ.ኤ.አ. በ1988 ዓ.ም. የአደንዛዥ ዕጸዋት እና ሕገ ወጥ የሥነ አእምሮ ዕጸዋት ንግድ ለመቆጣጠር የተደነገገው የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እንዳጸደቀችው ትላትና የቅድስት መንበር የውጭ ግኑንኘት ጉዳይ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዶሚኒክ ማምብርት ገልጠዋል።
በመላ ዓለም የወንጀል ቡድኖች በወንጀል ተግባር የሚያካብቱት የገንዘብ ሃብት ለመቆጣጠር ብሎም ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ሕገ ውጥነቱን ለመሠወር በሕጋዊ የኤኮኖሚ አውታር ለማዋል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ለይቶ ለመቆጣጠር መንግሥታት በሚያደርጉት ጥረት ቅድስት መንበር ባላት የግኑኝነትና የትብብር ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሚፈቅደው ሕግ መሠረት እግብር ላይ በማዋል ተቀዳሚ ሚና እንደምትጫወት ብፁዕ አቡነ ማምብርቲ በሰጡት መግለጫ በማብራራት ቅዱስ አባታችን በጴጥሮሳዊ የሥልጣን መብት መሠረት ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሕግ “የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ድለባ ለመቆጣጠር ብቻ ሳይሆን ይኸንን ሕገ ውጥ ተግባር ቀድሞ ለመቆጣጠር የሚደረገው የአስቀድሞ መጠንቀቅ ጸረ ወንጀል እና ጸረ ወንጀለኛነት ውሳኔ እግብር ላይ ለማዋል የሚደግፍ እያቀረበው ያለው ሕግ በእውነቱ የአሸባሪይን የገንዘብ ሃብት እና ሕገ ወጥ የገንዘብ ሃብት ሕጋዊነት ለማልበስ በጤነኛው የኤኮኖሚው አውታር ማዋል የሚደረገው እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እና ለመግታት በሚያስችሉ ሕጎች ለመታጠቅ የሚያደርገው ጥረት ቅድስት መንበር በመቀበል ይህ መሣሪያ ቅድስት መንበር ተልእኮዋ ለማካሄድ እና የተልእኮውን ኃላፊነት ለመወጣት ለሚያስችለው ዓላማ ታውለዋለች። አሸባሪነት እና የተደራጁት የወንጀል ቡድኖች ጸረ ሰብአዊ ክብር እና ጸረ ማኅበራዊ ጥቅም መሆናቸው በመግለጥ፣ ቅድስት መንበር እነዚህ የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔዎችን በማጽደቅ እና ተከታይነቷም በማረጋገጥ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ያላት ትብብር እና ግኑኝነት ብሎም ባላት የተልእኮዋ ባህርይ መሠረት በቅንነት እና ግልጽ በሆነ መንገድ በዓለም ሰላም እና ፍትህ ለማረጋገጥ ተቀዳሚ ሚና እንደምትጫወት” በማለት ያረጋገጡት ሐሳብ ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ በመጥቀስ በዚህ ዘርፍ በሃገረ ቫቲካን የበላይ ፍርድ ቤት እና በሁሉም አገሮች ፍርድ ቤቶች መካከል ትብብር እንደሚኖር ነው ብለዋል።
ማንኛውም የዓለም አቀፍ ሕግ የማንኛውም አገር ሉአላዊነት የሚጥስ ሳይሆን በአገሮች መካከል ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጥቅም ያቀና ትብብር የሚያነቃቃ መሣሪያ ነው። ይህ ትብብር ለሃይማኖት ነጻነት መከበር የሚያግዝ በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ከግዜ ወደ ጊዜ ከፍ ብሎ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ ለመግታት በቅድስት መንበር እና በተለያዩ አገሮች መካከል ያለው ትብብር የሚያጎለብት ውሳኔ እንደሚሆን ብፁዕነታቸው በሰጡት መግለጫ አብራርተው፣ ፍትህ እና ሰላም ተስማሙ የሚለው መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 85 ጠቅሰው፣ ቅድስት መንበር ለሰው ልጅ ክብር ጥበቃ እና በአሕዛብ መካከል ስምምነት እንዲረጋገጥ እውነትን ለማጽናት አጥብቃ ካላት ተልእኮ አንጻር ተቀዳሚ ሚና እንደምትጫው አረጋግጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.