2012-01-26 10:19:47

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. ጥር 24 ቀን 2012)
ኢፍትኃዊነት ጥላቻ እና ቀቢጸ ተስፋ ባለበት ሁሉ ሥፍራ ተስፋን አድርሱ


ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጸሎት ዙሪያ የጀመሩት አስተምህሮ በመቀጠል የዛሬው የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ኢየሱስ ‘ሰዓት’ ጸሎት ይኽም የክብሩና የልዕልናው ‘ሰዓት’ በደረሰ ጊዜ ወደ አባቱ ያቀረበው በዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 17 ከቁጥር 1 እስከ 26 የተመለከተው ቃለ ወንጌል ላይ RealAudioMP3 በማስተዋል ትኩረት በማድረግ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ እንደሚያረጋገጠውም “ክርስትያናዊ ትውፊት ይህንን ጸሎት የኢየሱስ ‘ክህነታዊ’ ጸሎት በማለት በትክክል ሲገለጠው ምክንያት አለው። ይህ ሊቀ ካህናችን የሆነው ጸሎት ከመሥዋዕቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ‘ተቀደሰለት’ ወደ አብ ‘ከማለፉ’ (ፋሲካ) ጋር የማይነጣጠል የሊቀ ካህናችን ጸሎት ነው” (ቍ. 2747)።
ይኽ የኢየሱስ ጸሎት ያለው ጥልቅ ክብር ለማስተዋል የሚቻለው የአይሁድ ሥርዓተ ስርየት፦ Yom Kippùr (ዮም ኪፑር) በዓል ጋር በማጣመር ስንመለከተው ነው። በዮም ኪፑር-ሥርዓተ ስርየት ወቅት፣ ሊቀ ካህናት በቅድሚያ የገዛ እራሱ ሥርዓተ ስርየት ይፈጽማል፣ በመቀጠለም ለካህናት በመጨረሻም ለመላው የአሕዛብ ማኅበረሰብ ይፈጽማል። የዚህ በዓል ዓላማውም ለእስራኤል ሕዝብ በአንድ ዓመት ውስጥ ከፈጸመው የሕግ መተላለፍ ኃጢኣት በኋላ መልሶ ዳግም የተመረጠ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ውስጥ “ቅዱስ ሕዝብ” መሆኑ እንዲያስተውል ማድረግ የሚል ነው። የኢየሱስ ጸሎት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 በዮም ኪፑር በዓል የሚፈጸመው ሥርዓት የሚከተል ቅርጽ ያለው ነው። ኢየሱስ በዚያች ሌሊት ገዛ እራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ወደ አባቱ ያቀናል። እርሱ ‘ካህን’ እና ‘መሥዋዕት’ ስለ ገዛ እራሱ፣ ስለ ደቀ መዛሙርቱ፣ በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ፣ ስለ ሁሉም ዘመናት ቤተ ክርስትያን ይጸልያል (ዮሐ. 17፣20 ተመልከተ)።
የኢየሱስ ስለ ገዛ እራሱ የሚያቀርበው ጸሎት ‘ሰዓቱ’ በደረሰ ጊዜ የክብር እና የልዕልና ጥያቄ የሚያቀርብ ነው። በእውነቱ ከሆነ ግን ከጥያቄ በላይና በሞት እና በትንሣኤ የሚጠቃለለው በነጻነት እና በቸርነት ወደ እግዚአብሔር እቅድ ለመግባት ያለው ሙሉ ፍቃደኛነቱን የሚያውጅ ጸሎት ነው። “ሰዓቱ” በይሁዳ ክህደት (ዮሐ. 13፣31 ተመልከት) ተጀምሮ የተነሣው ኢየሱስ ወደ አብ በማረግ (ዮሐ. 20.17 ተመልከተ) የሚጠቃለል ነው። ይሁዳ ከመጨረሻው የእራት ማዕድ ብድግ ብሎ መውጣቱ፣ ኢየሱስ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚአብሔርም በእርሱ ከበረ። (ዮሐ. 13፣31) በማለት ፍቹን ይገልጥልናል። ኢየሱስ ክህነታዊ ጸሎቱን “”ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው” (ዮሐ. 17፣1) በማለት ሲጀምር አለ ምክንያትም አይደለም። ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ስለ ገዛ እራሱ ክብር የሚያቀርበው ጥያቄ ወደ አባቱ በሙላት ወደ መታዘዝ እርሱም ወደ ውሉዳዊ ሁኔታው የሚመራው’፣ “አሁንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ከአነት ጋር በነበረኝ ክብር በአንተ ዘንድ አክብረኝ” (ዮሐ. 15፣5) የሚል ነው። ይኽ አይነቱ ኢየሱስ በይፋ በማስተዋወቅ መርቆ የሚያስጀምረው ፈቃደኝነት እና ጥያቄ የአዲስ ካህን የመጀመሪያ ተግባር ነው።
በሁለተኛው ደረጃ ኢየሱስ ጸሎቱ ሲያቀርብ ከእርሱ ጋር አብረ ስለ ነበሩት ደቀ መዛሙርቱ የሚያቀርበው ጸሎተ ጭምር የሚያጠቃልል ነው። ስለ እነርሱ ለአባቱ “ከዓለም ለይተህ ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁ፥ ያንተ ነበሩ፥ እነርሱንም ለእኔ ሰጥተኸኛል፥ ቃልህን ጠበቁ” (ዮሐ. 17፣6) ሲል የተናገረላቸው ናቸው። “የእግዚአብሔር ስም ለሰው ዘር መግለጥ” በሕዝቦች፣ በሰው ዘር መካከል ሥጋ በሆነው ቃል አማካኝነት የሚረጋገጠው አዲስ የአብ ኅላዌ እውን ማድረግ ማለት ነው። በኢየሱስ እግዚአብሔር በሰው ሥጋ ዘንድ ይገባል፣ በልዩ እና በአዲስ ሁኔታ ቅርብ ይሆናል። በፋሲካው ኢየሱስ በሞቱ እና በትንሣኤው እውን የሚሆን በመሥዋዕቱ የሚደመደም የላቀው የኅልውና ትርጉሙን ያረጋግጥልናል።
የዚህ ስለ ደቀ መዛሙርቱ የሚያቀረበው የምልጃ እና የስርየት ጸሎት ማእከል የቅድስና ጥያቄ መሆኑ ነው የሚያመለክተው። ኢየሱስ ለአባቱ “እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና። በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነውና። አንተ እኔን ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እኔም እነርሱን ወደ ዓለም ላክኋቸው” (ዮሐ. 17፣ 16-19) እንዲህ ሲል ይጠይቃል። ‘ቀድሳቸው’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ‘የተቀደሰ’ እና ‘ቅዱስ’ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ መቀደስ ማለት አንድ ተጨባጭ ነገር ወይንም ሰው ወደ የእግዚአብሔር ንብረትነት መለውጥ ማለት ነው። በዚህ ዘንድ ሁለት ተሟይ የሆኑ ገጽታዎች አሉ፣ በአንድ በኩል ‘የመለየት’፣ ‘ገለል ማድረግ’ የሚል እርሱም፣ ለእግዚአብሔር ለመሰጠት ከግል የሰብአዊ ሕይወት አካባቢ/ዙሪያ መገለልን ሲያመልክት፣ በሌላው ረገድ ‘የተልእኮ’ ሃሳብ ያለው፣ እርሱም ለእግዚአብሔር መሰጠትን፣ የተቀደሰው/ተለይቶ ለእግዚአብሔር የተሰጠው ስለ ዓለም እና ስለ ሰዎች ተልእኮውን መኖርን ያሰማል። ስለዚህ እንደ ኢየሱስ ለአንድ የተልእኮ ዓላማ ምክንያት ከዓለም የሚገለለው እና ለእግዚአብሔር ብቻ የሚለው በሙላት ሁሉንም ለማገልገል ዝግጁ ይሆናል ማለት ነው። የደቀ መዛሙርት ተልእኮ የኢየሱስ ተልእኮን መቀጠል የሚል አገልግሎት ይሆናል። በፋሲካው ሌሊት የተነሣው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በመገለጥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! አብ እኔን እንደ ላከኝ እንዲሁ እኔ እናንተን እልካችኋለሁ” (ዮሐ. 20.21) በማለት ይገልጥላቸዋል።
የኢይሱስ ክህነታዊ ጸሎት በሦስተኛው ደረጃ፣ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ዓለም እይታ ያለው ነው። በዚህ ጸሎት አማካኝነት ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ ተጀምሮ የሚቀጥለው ተልእኮ አማካኝነት እምነት ለሚደርሳቸው ሁሉ “የምለምንህም ስለ እነዚህ ብቻ አይደለም፤ በቃላቸው ስለሚያምኑብኝም ነው እንጂ” (ዮሐ. 17፣20) ሲል ስለ ሁሉም በሚያቀርበው ጸሎት ያረጋግጥልናን። ይኸንን ጸሎት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ “ኢየሱስ የአብ ሥራ ሙሉ በሙሉ ፈጽሟል፤ ጸሎቱ እንደ መሥዋዕቱ እስከ ጊዜ ፍጻሜ ይደርሳል። የዚህ ሰዓት ጸሎት የፍፃሜ ዘመናትን ይሞላል፤ ወደ ፍጻሜአቸውም ያደርሳቸዋል” (ቍ. 2749) በማለት ይተነትነዋል።
የኢየሱስ ሰዓት ጸሎት፣ ስለ ደቀ መዛሙርት በሚያቀርበው የካህን ጸሎቱ፣ በእርሱ ለሚያምኑ ለሁሉም ዘመን ሐዋርያት ውኅደት የሚጠይቅ ነው። ይህ አንድነት የዓለም ውጤት ሳይሆን ከመለኮታዊ አድነት ብቻ ከአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የሚገኝ ነው። ኢየሱስ ከሰማይ የሚወርደው፣ በምድር ውጤት ያለው ተጨባጭ እና የሚስተዋል ጸጋ ይጠይቃል፣ “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እንዳለሁ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም እንደ እኛ በእኛ ዘንድ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ” (ዮሐ. 17.21) ሲል ይጸልያል። የክርስትያኖች አንድነት በእያንዳንዱ አማኝ ልብ ዘንድ ያለ ተጨባጭ ምሥጢር ነው። ሆኖም ግልጽ በሆነ መንገድ ኢየሱስ “እኔም የሰጠኸኝን ክብር ሰጠኹኋቸው፤ እና አንድ እንደሆን እነርሱም አንድ ይሆኑ ዘንድ። እኔ በእነርሱ እኖራለሁ፤ እንተም በእኔ፤ በአንድ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፤ እንተም እንደ ላክኸኝ እንደ ወደድኸኝ እኔም እነርሱን እንደ ወደድኋቸው” (ዮሐ. 17. 22-23) በማለት የጠየቀው ነው። አብ ወደ ዓለም በላከው ኢየሱስ ዘንድ ያለ ኅብረት፣ ለመጪው ሐዋርያት ኅብረት የሚል ሲሆን፣ የክርስትና ተልእኮ በዓለም ውጤታማ የሚያደርገው መሠረታዊ ምንጭ ነው።
በኢየሱስ ክህነታዊ ጸሎት የቤተ ክርስትያን ቅዋሜ ይረጋገጣል። (ኢየሱስ ናዝራዊ ሁለተኛው መጽሐፍ፤ ገጽ. 117 ተመልከት)።
ኢየሱስ ሐዋርያቶቹ አንድ እንዲሆኑ ይጸልያል፣ በዚህ በሚሰጠው እና በሚታቀበው አንድነት ኃይል አማካኝነት ቤተ ክርስትያን “የዓለም” ሳትሆን “በዓለም” (ዮሐ. 17.16 ተመልከት) መጓዝና ዓለም በልጁ እና በላከው አብ እንዲያምን የተሰጣት ተልእኮ መኖር ትችላለች። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን የኢየሱስ የሆነው ‘ዓለም’ የሰው ዘር ለእግዚአብሔርና ለገዛ እራሱ ባይተዋር ከመሆን ውጭ፣ ከኃጢአት ውጭ ሆኖ የእግዚአብሔር ዓለም እንዲሆን የሚል ተልእኮ የሚቀጠልበት ሥፍራ በመሆን ትኖራለች።
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ታላቅ የሆነው የኢየሱስ ክህነታዊ ጸሎት የሚያቀርብልን የተገነዘብነው መሠረታዊው ነገሩ በመከተል ከጌታ ጋር ለመወያየት እንዲመራን ዳግም ታነቡት እና ታስተነትኑት ዘንድ እጋብዛችኋለሁ። እኛም በሙላት እርሱ ለእያንዳንዳችን ወዳለው እቅድ ለመግባት እንድንችል ይረዳንም ዘንድ በጸሎታችን እንተጠይቀው፣ ለእርሱ ‘የተቀደሱና የተለዩ’ እንድንሆን እርሱን እንጠይቀው፣ በበለጠው የእርሱ የተለዩ እየሆንን ሌሎችን ጎሬቤቶቻችንን ሩቅ ያሉትንም በበለጠ መውደድ ላይ እንድናድግም እንለምነው። ጸሎታችንን የገዛ እራሳችን ችግሮች እንዲፈቱ በገዛ እራስ እርዳታ ጥያቄ ላይ የታጠረ ሳይሆን ለዓለም አድማስ ክፍት የመሆን ብቃት ያለው እንዲሆን ለዚህ እንዲያበቃውም እርሱን እንለምነው። ስለ ሌሎች የመለመን ጸሎት ላለው ውበት ገዛ እራሳችንን ክፍት በማድረግ ጎረቤቶቻችንን ወደ ጌታ እናቅረብ። በዚህ የክርስትያኖች አንድንት የጸሎት ሳምንት እየጠየቅነው ያለው በክርስቶስ አማንያን መካከል የተጨባጭ አንድነት ጸጋ እንዲረጋገጥ፣ ዘወትር ስለ ተስፋችን ምክንያት ለሚየይቁን ሁሉ መልስ ለመስጠት ዝግጅዎች ሆነን እንድንገኝ (1ጴጥ. 3፣15 ተመልከት) እንጠይቀው፣ በማለት ለሁሉም ከውጭ እና ከውስጥ ትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመቀበል ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የተሰበሰቡት ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.