2012-01-23 14:19:26

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ
የክርስትያኖች እንድነት ጥሪ “እግዚአብሔርን መጠማት፣ ፍቱን እና ታማኝ የጋራ መልስ ማቅረብ ግዴታ ነው ይላል።


እ.ኤ.አ. ባለፈው ጥር 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚ ዓላማ ‘የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ውኅደት’፣ የክርስትያኖች ታማኝነት ኅብረት ላይ የጸና መሆን አለበት የሚል እማኔ መሠረት ያደረገ ነው፣ RealAudioMP3 በሚል መርኅ ቃል አማካኝነት ስለ ክርስትያኖች አንድነት የጸሎት ሳምንት በማስጀመር ክርስትያኖች ኅብረት ሲኖራቸው ታማኝ ምስክሮች ይሆናሉ፣ ይህ ውህደት ተራ ልባዊ መቀራረብ እና መተባበር የሚል ሳይሆን፣ ለዘመኑ ሰው ክርስቶስን የማወጅ ጥሪ አንገብጋቢ ምስክርነት በጋራ ጥልቅ የውስጥ ስሜት መገንዘብን የሚጠይቅ መሆኑ እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ሁሌ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ ማእከል በማድረግ በመቀጠል፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ውጤት የሚኖረው ሁሉም ክርስትያኖች በጋራ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌላዊ እውነት በማወጅ እና ለዘመናችን ጥልቅ ጥማት የጋራ መልስ ማቅረብ የሚጠይቅ መሆኑ ቅዱስ አባታችን እንዳሳሰቡ፣ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ጠቅሰው፣ በተለያዩ አቢያተ ክስትያን ለውህደት የሚደረገው ጥረት ተቀዳሚ የኵላዊት ቤተ ርክስትያን እና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተልእኮ መሆኑ በ 2012 ዓ.ም. መከር ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሊካሄድ የጠሩት የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚወያየው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እና ያወጁት የእምነት ዓመት የሚያረጋግጠው እውነት ሲሆን፣ የታወጀው የእምነት ዓመት ምክንያት በማድረግም የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አንቀጸ እምነት ተንከባካቢው ቅዱስ ማኅበር ባወጣው መሪ ሰነድ ሥር የተብራራ ሲሆን፣ ሰነዱ አክሎም የክርስትያኖች አንድነት ይኸው 50 ዓመት በመዘከር ላይ ያለው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተቀዳሚ ዓላማ መሆኑ በመጥቀስ ግፊት የሰጠበት ተልእኮ መሆኑም ይገልጣል።
በዘመናችን የሚታየው የመንፈሳዊነት ጥማት ምንም’ኳ ብዙ ችግር የተጋረጠ ቢሆንም ቅሉ፣ ታማኝ እና ፍቱን የጋራ መልስ የሚያሻው ጉዳይ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅርቡ የአየርላንድ ልኡካንን ተቀብለው ባነጋገሩትበት ዕለት፣ በአሁኑ ወቅት እጅግ አንገብጋቢ የሆነው የሥነ ምግባር ጥያቄ ለተለያዩ ማኀበረ ክርስትያን የሚያገናኝ ነጥብ መሆኑ መግለጣቸውም አባ ሎምባርዲ ጠቅሰው፣ ስለዚህ በሥነ ሰብእ መሠረታዊ ጥያቄዎች በተመለከቱ ጉዳዮች ክርስትያኖች ጥልቅ ስምምነት ሲኖራቸው፣ ኅብረተሰብ እና የፖለቲካው ዓለም ስለ ሰብአዊ ሕይወት ስለ ቤተሰብ እና ስለ ጾታዊ ስሜት በተመለከቱ ጉዳዮች ጥበብ የተካነው በሳል እና ቅን መልስ እንዲሰጡበት ያግዛል፣ ለጋራው እምነት ውህደት፣ ለሰብአዊነት ጉዞ የተወሃደ አገልግሎት ለማቅረብ ያነቃቃል በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.